Church PLANT Manual, Amharic Edition

124 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

መምሪያው፥ በጸሎት፣ በማሰላሰል እና በጥበብ ላይ ትኩር በማድረግ እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን ተካይ ግለሰብና ቡድን ውስጥ የእግዚአብሔር ጥሪ ጥበብ እንዲያገኙ ይመራል። በደርዘን በሚቈጠሩ ሥዕላዊ መግለጫዎችና ጽሑፎች ተሞላው ይህ የቤተ ክርስቲያን ተከላ መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኖችን በማስታጠቅ ረገድ ጉልሕ ሚና እንዲኖረው ታስቦ የተሰናዳ ነው። ከእግዚአብሔር መንግሥት ራእይ ጋራ የሚስማማ ትምህርት እንዲያዘጋጁ፣ ቤተ ክርስቲያን እንዲተክሉ፣ ለተጨቈኑት ስለ ፍትሕ የሚሟገቱ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል። ብዙ አብያተ ክርስቲያናትና ቤተ እምነቶች በየማኅበረ ሰቡ ውስጥ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማስፋት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ስንመለከት እንደሰታለን። ይህ መጽሐፍ ለዚህ ክቡር ራእይ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጸሎታችን ነው። በከተማ ድኾች መካከል ቤተ ክርስቲያን መትከል፥ የከተማ ቤተ ክርስቲያን ተከላ ነገረ ሰብ፥ ቅጽ አንድ፦ ቤተ ክርስቲያን ተካዮችን በተመለከተ ነገረ መለኮታዊና ሚስዮናዊ ምልከታ። ቅጽ አንድ፥ የቤተ ክርስቲያን ተከላና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተልእኮ አስፈላጊነትና ምንነትን በተመለከተ በተለይም ይህ ነገረ መለኮት የከተማ ተልእኮን፣ ቤተ ክርስቲያን ተከላ፣ እንዲሁም የጤናማ ጉባኤ ዕድገትና እንቅስቃሴን የሚዳስስ ነው። በዚህ ስብስብ ውስጥ በከተማ ድኾች መካከል ቤተ ክርስቲያን ለመትከል ያደረግነውን ተግባር፣ ያሳወቅነውን ጽሑፍ፣ መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስና ነገረ መለኮታዊ ጽሑፍ ታገኛለችሁ። በተጨማሪም ለከተማ ሚስዮን ተግባር የሚጠቅሙ ነገረ መለኮታዊና ሚስዮናዊ ግብዓቶችን ታገኛላችሁ። ድኾችን በሚያገለግሉ አብያተ ክርስቲያናት መካከል በቀለም፣ በዘር፣ በመደብ፣ ልዩነት ሳይኖር ሁሉንም ደቀ መዛሙር የማድረግ ታላቁን ትውፊት ማነሣሣት ያስችላል። በተጨማሪም፥ እነዚህ ግብዓቶች በከተማ ውስጥ ያሉ ድኾችን ለመድረስ ቤተ ክርስቲያን የመትከልን ሂደት ከጥንስሱ ምን እንደሚመስል አካትቶ ይዟል። በቤተ ክርስቲያን ተከላ ሂደት ጥሪ፡ ባሕርይና ብቃት ላይ ትኩረት በማድረግ በከተማ ውስጥ ባሉ ድኾችና ለችግር ተጋላጭ ማኅበረ ሰቦች መካከል ቤተ ክርስቲያንን መትከል ይቻላል።

Made with FlippingBook - Share PDF online