Church PLANT Manual, Amharic Edition
ድኅረ ቃል • 125
በከተማ ድኾች መካከል ቤተ ክርስቲያን መትከል፥ የከተማ ቤተ ክርስቲያን ተከላ ነገረ ሰብ ቅጽ ሁለት፦ ግብዓቶችና ለአሠልጣኞችና ለቡድኖች የሚሆኑ መሣሪያዎች ቅጽ ሁለት ለቤtተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን አሠልጣኞች ወይም ቡድን መሪዎች የሚሆኑ የተለያዩ ግብዓቶችን አካትቶ ይዟል። በተጨማሪም ይህ ቅጽ ተካዮችና ቡድኖቻቸው በቤተ ክርስቲያን ተከላ በሚጠመዱበት ወቅት የሚያስፈልጓቸውን ጠቃሚ መርጃዎች ይዟል። በዚህ ስብስብ ውስጥ የቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኖችን ለሚያሠለጥኑ ወይም ለሚያማክሩ ቡድኖች የሥራው ሂደት የሚያሳዩ መጣጥፎችን ታጋኛላችሁ። የተለያዩ ጉዳዮችን የሚመለከቱ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን የሚያግዙ እንዲሁም የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች የሚያመላክቱ ጽሑፎችን ታገኛላችሁ። በተጨማሪም ለቤተ ክርስቲያን ተከላ የሚጠቅሙ ሰነዶችን፣ ሠንጠረዦችን፣ መጻጽፎችን እንዲሁም የአመራር ሁኔታን፣ ከመንግሥት ጋራ የሚያያዙ ጉዳዮችን፣ የፋይናን ጉዳዮችን፣ ማስታጠቅንና ማጎልበትን የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎችን አካትቶ ይዟል። በዚህ ክፍል ውስጥ ለተካዮች፣ ለአሠልጣኞችና ተባባሪ ማኅበራት የሚጠቅሙ በርካታ ባህር ዘለል ሰነዶችን ታገኛላችሁ። እነዚህ በርካታ መርጃዎች በግለሰብ ደረጃ እንኳ ስለ ቤተ ክርስቲያን ተከላ፣ የጤናማ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴና መዋቅሮች ስለመመሥረት፣ ስለ መብዛት እንዲሁም በከተማ ውስጥ ባሉ ድኾች መካከል የእግዚአብሔርን መንግሥት ስለማስፋት ጥሩ ግንዛቤ የሚያስጨብጡና አመለካከትን የሚያሰፉ ናቸው።
ሌሎች ተጨማሪ ግብዓቶች በዚህ ዐለት ላይ፦ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ናሙና
ይህ ናሙና ላለፉት አርባ ኣመታት በላይ በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ከተሞች ውስጥ ሲያገለግል የቆየ ክርስቲያናዊ ሚስዮን ድርጅት የሆነው የወርልድ ኢምፓክት (www.worldimpact.org) የማሠልጠኛ ሰነድን የሚወክል ነው። የቤተ ክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴዎች በወንጌል ስብከት፣ በማስታጠቅና በማብቃት በወንጌል ያልተደረሱ የከተማ ድኾች ነዋሪዎችን ለመድረስ የተቻለንን ሁሉ ለማድረግ ቍርተኞች ነን። የወርልድ ኢምፓክት ዐላማ በከተማ ውስጥ የሚኖሩ በወንጌል ያልተደረሱ ድኾችን በወንጌል
Made with FlippingBook - Share PDF online