Church PLANT Manual, Amharic Edition

126 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

በመድረስ እግዚአብሔርን እንዲያውቁና ርሱን እንዲያሳውቁ በማድረግ እግዚአብሔርን ማክበራ በርሱም መደሰት ነው። ለእኛ፥ በተከማ የሚኖሩትን ድኾች ማኅበረ ሰብ በፍጥነትና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመለወጥና አስሚታ ለመፍጠር የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት የሚታወጅባትና የሚታይባት ክርስቶስን ማእከል ያደረገች ቤተ ክርስታየን መትከል ነው ብለን እናምናለን። በድኾች መካከል ጤናማ ቤተ ክርስቲያን በመትከል በአካባቢዎቹ ባሉ ሰዎች ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ የመለወጥ ኀይል እንደሚገለጥ እምነታችን ነው። ይህ ናሙና (www.tumientree.com) ድረ ገጽ ላይ የሚገኙ ጽሑፎችንና ተጨማሪ ግብዓቶችን የማየት ፍላጎት ይቀሰቅስባችኋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። እነዚህ ልዩ ልዩ መርጃ መሣሪያዎች ታላቁ ተልእኮ በከተማ ድኾች መካከል ሲፈጸም ለማየት ያለንን ቊርጠኛነት እንደሚያሳያችሁ ተስፋ እንዳርጋለን፤ ያመንነውም ሊፈጸም ይገባዋል። ብቁ ወኪል መሆን፦ የደቀ መዛሙርት ጉባኤ ራእይ ክርስቶስንና መንግሥቱን ለመወከል ብቁ ናችሁ? የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅ ተልእኮ ደቀ መዛሙርት እንድናደርግ የተሰጠ ትእዛዝ ነው፤ ይህም ደግሞ ሰዎች ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ የሚደረግ ነው። ይህን ታላቅ ትእዛዝ ከግብ ለማድረስ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመምህራችን ኢየሱሰስ ክርስቶስ ተከታይ ወይም ደቀ መዝሙር መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት አለብን። የደቀ መዛመርት ጉባኤ ራእይ የከተማ አገልግሎት ተቋም ሲሆን የክርስቶስን መንግሥት በታላቅ ተነሣሽነትና ፍላጎት የሚያስቀጥል በመንፈሳዊ ረገድ ብዙ የሆነ ትውልድ ማስነሣት ነው። ይህ መጽሐፍ በጉባኤው ተሳታፊዎች ዘንድ የነበረውን ውይይት የያዘ ጽሑፍ ነው። እነዚህ መንፈሳዊና ፈታች የትምህርት ጊዜያት ደቀ መዛሙርት አድራጊዎች በሆን ለክርስቶስ ጥሪ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡ የሚሞግቱ ናቸው። ከዚህም የተነሣ ወርልድ ኢምፓክት በአሜሪካና በመላው ዓለም ካሉ ኀይላት ጋራ ትብብር በመፍጠር መንፈሳዊ መነቃቃት እንዲሆን ይናፍቃል። ይህ የደቀ መዛሙርት ጉባኤ ራእይ መምሪያ መጽሐፍ ሕይወታችሁን ለሌሎች በማካፈል ለክርስቶስ ፍሬ እንድታፈሩ የሚረዳችሁ ይሁን።

Made with FlippingBook - Share PDF online