Church PLANT Manual, Amharic Edition
26 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
2. ራሳችሁን ከሰዎች አታርቁ ይልቁንም በዙሪያችሁ የምታምኗቸውና ለእናንተ ግድ የሚላቸው ሰዎች ይኑሯችሁ። ጉዳት ወይም የልብ ስብራት ሲገጥመን ራሳችንን ከሰዎች ማግለል የተለመደ ነገር ነው፤ ነገር ግን ይህ ተግባር ጤናማ ወዳልሆነ ልማድና የአገልግሎት መልክ ይመራናል። ራሳችንን ከሰዎች አግልለን መኖር ሥቃያችንን የሚያባብስና ሕመማችንን ማንም እንዳያውቀው የምንንሸፋፍን እንድንሆን ያደርገናል፤ ውሸትንም እንለምዳለን (1ነገሥት 19፥9 18፤ 2ቆሮንቶስ 1፥3-11)። 3. ጥሪያችሁን በመረዳት የምታልፉበት መከራ የተለመደ የመሆኑን እውነታ ተቀበሉ። የጥሪና የዐላማ ሸክም በአገልግሎት ውስጥ የሚገጥሙንን መከራዎች እውነታነት እንድንቀበል ያስችለናል። ጥሪያችን እንደሆነ ማወቃችን ከገጠመን አሁናዊ ኹኔታ አሻግረን እንድንመለከትና በሩጫው መም ላይ ሩጫችንን ሳናቋርጥ እንድንቀጥል ይረዳናል (2ተሰሎንቄ 1፥11፤ ዕብራውያን 12፥1-3)።
Made with FlippingBook - Share PDF online