Church PLANT Manual, Amharic Edition
ክፍል 1፥ ዝግጅት • 25
የሚረዳችሁና በቤተ ክርስቲያን ተከላ ተግባራችሁ ዐብሯችሁ የሚሆን አማካሪ ወይም እረኛ ለማግኘት ከፈለጋችሁ የኢቫንጀል መስክ አሠልጣኛችሁ ለእናንተ ፍላጐትና ዐውድ ጋራ ተስማሚ የሆነ ሰው በመፈለግ ሊያግዛችሁ ይችላል። 4. ቤተ ሰባችሁ ቅድሚያ ልትሰጡት የሚገባ የመጀመሪያ አገልግሎታችሁ ነውና ጠብቁት። ቤተ ሰቦቻችሁ እንደተተዉና እንደማትንከባከቧቸው እንዲሰማቸው ፈጽሞ አትፍቀዱ፤ እንዲሁም ለአገልግሎታችሁም ዕንቅፋት አድርጋችሁ አትመልከቷቸው። በቤተ ሰቦቻችሁ ለመደሰትና በእነርሱም ሕይወት አሻራችሁን ለማኖር ቅርብ ሁኗቸው (1 ጢሞቴዎስ 3፥2-5፣ 12፤ ምሳሌ 3፥1-8፤ ኤፌሶን 6፥4፤ ቆላስይስ 3፥18-21)። 5. በየወቅቱ ዕረፍት የማድረግ ልማድ ይኑራችሁ። ሆነ ብላችሁ ለዕረፍት፥ ለጸሎት የምትመድቡት የዕረፍ ጊዜ ይኑራችሁ፤ ከዚያም በዐዲስ ጉልበት ወደ አገልግሎታችሁ ትመለሳላችሁ። ለጥቂት ጊዜ ከሥራ በማረፍ በእግዚአብሔር ላይ በመታመን ልባችንና ሐሳባችንን ዳግም መቃኘት እንችላለን (ዘፍጥረት 2፥1-3፤ መክብብ 3፤1-8፤ ዕብራውያን 4፥6-10፤ ማርቆስ 6፥40-47)። 6. ፍሬ ማፍራት ትችሉ ዘንድ ከወይኑ ግንድ ጋራ ተጣበቁ። ለጸሎትና ለቃሉ ጊዜ መስጠትን ችላ ካልን አገልግሎታችን ከባዶ ማሰሮ እንደ መቅዳት ይሆናል። ሌሎችን የምናገለግለው እግዚአብሔር በልባችን ሞልቶ ካትረፈረፈው መሆን አለበት (መዝሙር 1፥1-4፤ ዮሐንስ 15፥1-5)። III.በግንኙነቶች መካከል ከሚገጥሙ ስብራቶችና ጉዳቶች መፈወስ 1. ሐዘናችሁን በደንብ እዘኑ፤ ሕመማችሁን ለማስታመም ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋራ ጊዜ ውሰዱ። በአገልግሎት ውስጥ ሥራ ወደሚበዛበት ቀጣዩ ምዕራፍ ወዳየውኑ የመሻገር ፈተና አለ። በሚያሳዝኑ አስቸጋሪ ሁኔታዎችንና ተመክሮዎች ውስጥ ስታልፉ ለማዘን ጊዜ ይኑራችሁ (2 ቆሮንቶስ 7፥6-7፤ ኢሳይያስ 38፥14፤ ሮሜ 12፥15)።
Made with FlippingBook - Share PDF online