Church PLANT Manual, Amharic Edition

24 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ሐ. ኢየሱስ ለማረፍና ለመጸለይ ዘወትር ከሕዝቡ ገለል ብሎ ለብቻው ይሆን ነበረ። ሲጾም፣ ሲጸልይ እንዲሁም ገለል ሲል የሚያሳዩ ምሳሌዎችን እንመለከታለን። የሚሰቀልበት ጊዜ ሲቃረብ ጊዜውን በጸሎት ያሳለፈ ሲሆን ደቀ መዛሙርቱ ሸክሙን እንዲካፈሉት ጠይቋቸው ነበረ። ፍሬ ለማፍራትም ከእግዚአብሔር ጋራ የማያቋርጥ ግንኙነት ሊኖረን እንደሚገባ በምሳሌ አስረድቷል (ማቴዎስ 14፥13፤ ሉቃስ 22፥39-46፤ ማቴዎስ 4፥1፤ ዮሐንስ 15፥1-4)። መ. ጳውሎስ ከሌሎች ተለይቶ ለብቻ አገልግሎቱን አገልግሎ አያውቅም፤ ሁልጊዜም ዐብረውት የሚሠሩ ባልደረቦች አሉት። በደረሱበት በርካታ መከራዎች ውስጥ ያለማቋረጥ በእግዚአብሔር ላይ የታመነ ሲሆን የሌሎችንም ድጋፍ አግኝቷል። የተሰጠውን አገልግሎት ለመፈጸም በመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሥራ በጥልቀት መታመን እንዳለበት ተረድቷል (2ቆሮንቶስ 1፥8-11፤ ሐዋርያት ሥራ 16፥1-5)። II. ተግዳሮቶችን የመቋቋም ችሎታን የሚያጐለብቱ ነገሮችን ማዳበር 1. ለልባችሁና ለማኅበረ ሰባችሁ ለውጥ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ታመኑ። ዘሮችን ዝሩ ነገር ግን የተዘሩትን ዘሮች እንደሚያሳድግ በእግዚአብሔር ታመኑ። በታማኝነት እናገለግላለን ነገር ግን ለሥራችን ፍሬ በእግዚአብሔር እንታመናለን (1ቆሮንቶስ 3፥5-9፤ 1 ቆሮንቶስ 2፥1-5)። 2. ሌሎችን መወከል በድጋሚ ሌሎችን መወከል። እናንተ በማስተማሩና በእረኝነቱ ተግባር ላይ ማተኮር እንድትችሉ እንዲሁም ሌሎች የመሪነቱን ሸክም እንዲጋሯችሁ ማሠልጠንና ኀላፊነት መስጠት አለባችሁ (ሐዋርያት ሥራ 6፥1-4፤ ኤፌሶን 4፥11-13)። 3. በሕይወትና በአገልግሎት ልምድ ከእናንተ ቀደም ያለ ሰው ፈልጉና በምታገለግሉ ጊዜ እናንተን ደቀ መዝሙር እንዳየደርጓችሁና እረኛ እንዲሆኗችሁ ፍቀዱላቸው። እያንዳንዱ መሪ የሚመክረውና መጋቢ የሚሆነው ሰው ያስፈልገዋል (ማቴዎስ 10፤ ቲቶ 2፥1-8፤ 2ጢሞቴዎስ 1፥1-8)። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገጥሟችሁን

Made with FlippingBook - Share PDF online