Church PLANT Manual, Amharic Edition
ክፍል 1፥ ዝግጅት • 23
ትምህርት 3 ተግዳሮቶችን የመቋቋም ዐቅምን ማጐልበት ሬቨረንድ ጆርዳን ኪንግ
ችግሮችን የመቋቋም ችሎታ ማጐልበት መሪዎች ወይም እረኞች ይዘውት የሚወለዱት ባሕርይ ወይም ለእነርሱ ብቻ የተሰጠ ስጦታ አይደለም። ይልቍንም ችግሮችን የመቋቋም ዐቅም የሚዳብረው በተመክሮ፣ መጐዳት እንዲሁም መንፈሳዊና ስሜታዊ ፍላጐቶቻችንን እንዲያሟላልን በእግዚአብሔር ላይ በመታመን ውስጥ ነው። እያንዳንዱ መሪ ከአገልግሎቱ ጋራ ተያይዘው የሚመጡ ተግዳሮቶችን የመቋቋም እና ከዚያም የማገገም ችሎታ ማዳበር አለበት። ለአገልግሎታችሁና ለቤተ ሰባችሁ ጤናማ የሆነ ልማድ ለማዳበር “ድካም ሁላችንንም ፈሪዎች ያደርገናል” በማለት የመቋቋም ችሎታን ለማዳበርና የድካም ስሜትን ለመከላከል ቍልፍ ነው። 1 I. ተግዳሮቶችን የመቋቋም ችሎታ ያጐለበቱ መሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች ሀ. ሙሴ በሥራ ብዛት ደክሞ ነበረ ስለዚህም ሌሎችን መወከልና በአመራሩ ውስጥ ሌሎችንም ማሳተፍ ነበረበት ለዚህም በሕይወቱ ውስጥ ከሚያምናቸው ሰዎች ድጋፍ ማግኘትና በእነርሱም መደገፍ ነበረበት። ግትርና አስቸጋሪ የነበሩ ሰዎችን የመምራት ፈተናዎች ቢገጥሙትም ርሱ ግን ጉልበትን ከሚሰጠው ከእግዚአብሔር ጋራ የጠበቀ ግንኙነት ነበረው (ዘፀአት 18፥13-23፣ 17፥8-13) ለ. ዳዊት ፍትሓዊ ባልሆነ መንገድ ለዓመታት ንጉሥ ሳኦል ያሳድደው ነበረ ይሁን እንጂ በዚህ ሁሉ ውስጥ ርሱ ግን በእግዚአብሔር ላይ በመታመን ዘልቋል። የገዛ ልጁ እንኳ ሊገድለው በሞከረ ጊዜ በጓደኞቹ ታምኖ ሕይወቱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ ሰጠ። በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን በሠራ ጊዜ ስለ ተጸጸተ ፈውስን ፍለጋ ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ (መዝሙር 18፥1-6፣ 51፥7-12፤ 2ሳሙኤል 15፥18-23)።
1 This quote is attributed to Vince Lombardi.
Made with FlippingBook - Share PDF online