Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ • 41

ትምህርት 4 የወንጌል አንቀሳቃሽ ኀይል መጋቢ ሎሬንዞ ኤሊዞንዶ

ወንጌል ሙሉ በሙሉ ስለ ኢየሱስ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የሚጠቁሙት ወደ ኢየሱስ ስለሆነ ወንጌል ቅዱሳት መጻሕፍት ማእከላዊ ጭብጥ ነው። ወንጌል፥ ታላቁ አምላካችን የወደቀውን ሰው በርኅራኄ የተመለከተበት፤ እና ልንኖረው ያልቻለውን ሕይወት ይኖረው ዘንድ ልጁን ኢየሱስን የላከበት፤ እንዲሁም እኛ ልንከፍለው ያልቻልነውን ዋጋ ሊከፍል፣ ከሙታን በመነሣት፣ ሰይጣንን፣ ኀጢአትንና ሞትን ድል በመንሣት እንዲሁም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የነበረውን መለያየት ያስወገደበት ምሥራች ነው። ያዳነን ብስራት ይህ ነው። ወንጌል የሚያድነን ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን ተልእኮ እንድንፈጽምም ይልከናል። እንደ አለመታዳል ሆኖ ዛሬ ላይ ብዙ ክርስቲያኖች ወንጌልን እንደ ለመለወጥ እንደሚተቅም መሣሪያ ብቻ አድርገው ይመለከቱታል። ነገር ግን ወንጌል ከክርስትና ሀ ሁ የበለጠና የክርስትና እምነት ከ ሀ እስከ ፐ ነው። ሐዋርያ ጳውሎስ በሮሜ 1፥16 እንዲ በማለት ያስታውሰናል “በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ ይህም በመጀመሪያ ለአይሁድ፣ ቀጥሎም ለአሕዛብ ነው።” ወንጌል የሚያድነንና የሚልከን ብቻ ሳይሆን እንደ ቤተ ክርስቲያን ቅርጽ የሚሰጠንም ነው። በሌላ አገላለጽ፥ ቤተ ክርስቲያን የቆመችው በወንጌሉና ለወንጌሉ ነው። ቤተ ክርስቲያን እንደ ልብ ናት። ልብ ደም የሚረጨው ወደ ራሱ ብቻ ቢሆን ሰውነት ይሞታል። ልብ ደምን ወደ ሰውነት መርጨት ብቻ ቢሆን ሥራው አሁንም ሰውነት ይሞታል። ሰውነት በሕይወት እንዲኖር ልብ ወደ ውስጥም ወደ ውጭም ደም መርጨት አለበት። በተመሳሳይ መልኩ ቤተ ክርስቲያን ሕያው ለመሆን ያለ ማቋረጥ ወደ ወንጌሉ መምጣት አለባት እንዲሁም ሕያው ሆና ለመዝለቅ ወደ ሌሎች መላክ አለባት። ልክ እንደ ልብ ኢየሱስም በተመሳሳይ ስልተ ምት እንድንኖር ፈጥሮናል። እግዚአብሔርን፣ ባልንደራችንን እንድንወድድ እና ርስ በርሳችን (ቤተ ክርስቲያን) እንድንዋደድ ነግሮናል።

Made with FlippingBook - Share PDF online