Church PLANT Manual, Amharic Edition
የቡድን መልመጃዎች፥ መጀመርና መሰባሰብ • 59
መልመጃ 5 የወንጌል አንቀሳቃሽ ኀይል
ቡድናችሁ የወንጌልን ማእከላዊነት መረዳትና ወንጌልን ለማወጅ፣ ዐውዳዊ ለማድረግና ቤተ ክርስቲያን በማኅበረሰቡ ውስጥ የእግዚአብሔር ኤምባሲ ሆና ልትሠራ የምትችልበትን ስልት መቀየስ ያስፈልገዋል።
መመሪያ ቀጥሎ የቀረቡትን ጥያቄዎች በቡድን ተወያዩባቸውና መዝግባችሁ ያዙ
የመልመጃ ጥያቄዎች 1. ወንጌል ሕይወታችንን የሚያድነውና የሚለውጠው እንዴት ነው? 2. በሕይወታችሁ እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የወንጌልን የመለወጥ ኀይል ያያችሁባቸውን አንዳንድ ጉዳዮች ጥቀሱ። 3. ወንጌልና ቅዱሳት መጻሕፍት በሙሉ የሚናገሩት ስለ ኢየሱስ መሆኑን መረዳት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 4. ይህን የተረዳችሁትና ብሐይወታችሁ፣ በቤተ ክርስታየንና በአገልግሎታችሁ ያለውን ጠቀሜታ ያያችሁት እንዴት ነው? 5. ለወንጌል እናንተን መላክ ማለት ምን ማለት ነው? ተልእኳችሁ ምንድን ነው? 6. ላባችሁበት ማኅበረ ሰብ ውስጥ ይህን ተልእኮ ለመፈጸም እንዴት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ትችላላችሁ? 7. ቤተ ክርስቲያን በምድር ላይ የእግዚአብሔር አምባሲ ተብላ የምትጠራው ለምንድን ነው? ቤተ ክርስቲያናችሁ ወንጌልን የምታውጀውና የምታሳየው እንዴት ነው? 8. ዐውዳዊነት ምንድን ነው? ወንጌልን ለማካፈልስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
Made with FlippingBook - Share PDF online