Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 3: ማሳደግና ሽግግር • 67

ትምህርት 7 ውጤታማ ደቀ መዝሙር አድራጊነት 1

ስብከተ ወንጌል እና ዐዳዲስ አማኞችን በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ማካተት ለውጤታማነትና ለእድገት ጅማሬን ጥሩ መመዘኛ ነው፡፡ መንፈሳዊ እድገትን በሰዎች ቍጥር መጨመር (ዕድገት) ማስላት ምናልባት አታላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሚተክሉ ብዙዎቹ እድገታቸውን በቍጥሮች በማስላት ይጠመዳሉ። አንድ ቤተ ክርስቲያንን የሚተክል ሰው ትኩረቱ ሁሉ በቍጥሮች ከተወሰደ እና ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋራ የቍጥር ውድድር ውስጥ የሚገባ ከሆነ በፍጥነት ሊወድቅና በጥፋተኛነትና በሃፍረት ስሜት ውስጥ ሊወድቅ ይችላል። ቤተ ክርስቲያን ተካዮች ማወቅ እና መገንዘብ ያለባቸው ነገር የቍጥር መጨመር የደቀ መዝሙር አድራጊነት አመልካች አለመሆኑን ነው፡፡ ብዙ ቤተ ክርስቲያን ተካዮች ይህንን እውነት አስቸጋሪ ሁኔታ በማለፍ የሚማሩት ትምህርት ነው፡፡ ምናልባት ለማንበብ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ሰዎችን በወንጌል መድረስ የመጀመሪያው እንጂ የመጨረሻው ግብ አይደለም። ለታላቁ ተልእኮ ምላሽ በመስጠት ረገድ የቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ሥራ ደቀ መዝሙር ማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ደቀ መዝሙር ለማፍራት የሚረዳ ስልት ያስፈልጋታል። ቀጥሎ የቀረበው ቢጋር ቡድናችሁ የደቀ መዝሙርነትን ዐሳብና ምንነት እንዲረዳ እና በኋላም ቤተ ክርስቲያንን ስታስታጥቁ እንዲተቅማችሁ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። I. ታላቁ ተልእኮ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት፣ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን • ታላቁ ተልእኮ፣ ማቴዎስ 28፥18-20፣ ማርቆስ 16፥15-16፣ ሉቃስ 24፥46-49፣ ሐዋርያት ሥራ 1፥8፣ ዮሐንስ 20፥21 1. የኢየሱስ ክርስቶስ ሥልጣን

1 Adapted from a seminar by Rev. Dr. Don L. Davis in Ripe for Harvest , pp. 359-367.

Made with FlippingBook - Share PDF online