Church PLANT Manual, Amharic Edition
68 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
2. ወደ አሕዛብ ሁሉ የመሄድ፣ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ የማጥመቅና ደቀ መዛሙርት የማድረግ ሥልጣን። 3. ትእዛዙ፦ የክርስቶስን ትምህርት እንዲታዘዙ ማስተማር። • የእግዚአብሔር መንግሥት፦ ማቴዎስ 6፥33፣ ማርቆስ 1፥14-15፣ ራእይ 11፥15፣ ሮሜ 14፥17 1. የእግዚአብሔር መንግሥት = በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ የእግዚአብሔር ንግሥናና አገዛዝ። 2. የጨለማው መንግሥት = የጠላታችን መንግሥትና አገዛዝ፣ ሰይጣን፣ ጠላት፣ ዲያብሎስና ጭፍሮቹ፣ የጨለማው ኀይላት፣ ኤፌሶን 6፥12 • የክርስቶሰ ቤተ ክርስቲያን = የክርስቶስ አካል፣ በዛሬ ዓለም ላይ የሚታይ የሕያው ክርስቶስ መገለጫ ማሳያ፣ የእግዚአብሔር ጥበብ መገለጥ፣ በምድር ሁሉ ላይ ዕርቅን የሚያውጅ የእግዚአብሔር ወኪል፣ ማቴዎስ 16፥18፣ ኤፌሶን 1፥22-23፣ 1ጢሞቴዎስ 3፥15፣ ኤፌሶን 3፥8-12፣ 2ቆሮንቶስ 5፥18-21።
ደቀ መዝሙር አድራጊነት፥ እግዚአብሔር አገዛዙን በምድር ላይ መልሶ ለማስፈን የጀመረው ዕቅድ ፍጻሜ ሲሆን ይህም በቤተ ክርስቲያን በኩል ከሕዝቦች ሁሉ ሰዎችን ለክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በማድረግ የሚፈጸም ነው። ደቀ መዛሙርት ማድረግ የትንሣኤው ኢየሱስ ዳግም እስኪመጣ ድረስ የሰጠውን ትእዛዝ መፈጸም ነው።
II. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ደቀ መዛሙርት የማድረግ ምክንያቶችና ምንድንነቶች • በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ደቀ መዛሙርት ማድረግ ለምን አስፈለገ?
Made with FlippingBook - Share PDF online