Church PLANT Manual, Amharic Edition
ክፍል 3: ማሳደግና ሽግግር • 69
1. ቤተ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ የእግዚአብሔር ዋናው ዐሳብና ዓላማ ያለባት ስፍራ ናት። የርሱ ፍላጎት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዐዲስን ሰው መሥራት ነው። 2. ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ዓለምን ከርሱ ጋራ የማስታረቅ ተልእኮ ውስጥ ወኪል ናት። 3. ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት፣ ለወደቀው ትውልድ የክርስቶስ መገለጥ ናት። 4. ደቀ መዝሙር ማድረግ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ፣ በቤተ ክርስቲያን በኩልና ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም የሚደረግ ተግባር ነው። • የደቀ መዝሙር አድራጊነት አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ምንድን ናቸው? 1. ሙሴ እና ኢያሱ፦ ዘኊልቍ 27፡፥5-20፣ ኢያሱ 1፥1-2 2. ኤልያስ እና ኤልሳዕ፦ 1 ነገሥት 19፣ 2ነገሥት 3. ዳዊት እና የርሱ “ኀያላን”፦ 1ዜና 12 4. ኑኀሚን እና ሩት፦ ሩት 1 5. ኢየሱስ እና ዐሥራ ሁለቱ፦ ማርቆስ 3፡14 6. ጳውሎስ እና ጢሞቴዎስ (የአገልግሎት ቡድኑ)፦ ሐዋርያት ሥራ 20፥4 እና ፊልጵስዩስ 2፥20-22 በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰዎችን ደቀ መዛሙርት ማድረግ አርአያ የመሆን፣ የመምከር፣ ክርስቶስን ይመስሉ ዘንድ በክርስቶስ አካል ውስጥ እንዲጨመሩ የማድረግ ሂደት ነው። ይህም ጓደኛ በመሆን በእምነትን እንዲጸኑ፣ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በክርስቶስ አካል ውስጥ ሆነው ቤተ ክርስቲያንንና ዓለምን ለማገልገል እንዲችሉ የማስታጠቅ ሂደት ነው።
Made with FlippingBook - Share PDF online