Church PLANT Manual, Amharic Edition
70 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
III.የደቀ መዝሙር አድራጊ ሚና፣ ምሳሌ መሆን፣ አማካሪ፣ እና ጓደኛ • ምሳሌ የመሆን ኀላፊነት (ደቀ መዝሙር አድራጊው ማን ነው) • አማካሪ የመሆን ኀላፊነት (ደቀመዝሙር አድራጊው ተግባሩ ምንድን ነው) • ጓደኛ የመሆን ኀላፊነት (ደቀመዝሙር አድራጊው እንዴት ነው የሚዛመደው) IV.ለውጤታማ ደቀመዝሙርነት የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሚና • ቤተ ክርስቲያን ዐዲስ የዳኑ ሰዎችን ወደ አካሉ እንዲካተቱ በማድረግ ታግዛለች። • ቤተ ክርስቲያን ዐዳዲስ ክርስቲያኖች መሠረት እንዲይዙ “የእምነትን ትክክለኛነት በማረጋገጥ” ረገድ ወሳኝ ናት • ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳንን ለማገልገል አገልጋዮችን ታስታጥቃለች፥ ኤፌሶን 4፥9-15
ክርስቶስን መምሰል፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ደቀ መዛሙርት የማድረግ ዋነኘው ግብ ክርስቲያኖች በርሱ ላይ ካላቸው እምነት የተነሣ በክርስቶስ አንድ ናቸው። የእግዚአብሔር ዋነኛ ፍላጎት እያንዳንዱን የቤተ ክርስቲያን አባል ከክርስቶስ ውበት እና ክብር ጋራ ማስማማት እንደሆነ ከተረዳን ብቻ ነው ደቀ መዝሙርነትን በተገቢው ዐውድ ውስጥ ማስቀመጥ የምንችለው። ክርስቲያን በሕይወቱ እና በአገልግሎቱ በሁሉም አቅጣጫ በክርስቶስ አንድ ነው። ስለዚህ ደቀ መዝሙር አድራጊነት እግዚአብሔር በክርስቶስ ያደረገልንን በህይወታችን ለማሳየት ውጤታማ ጥረት ማድረግ ማለት ነው (ሮሜ 8፥29፣ 1ዮሐንስ 3፥2-3፣ 2ቆሮንቶስ 3፥18፣ ፊልጵስዩስ 3፥4-12)።
Made with FlippingBook - Share PDF online