Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 3: ማሳደግና ሽግግር • 71

ትምህርት 8 መሪዎችን ማሳደግ 1

ደቀ መዝሙር የማድረግ ሂደት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በብዙ ደረጃዎች ይገለጠል። ከዚህ ቀደም በነበረው ትምህርት እንደተብራራው ቤተ ክርስቲያን ደቀ መዛሙርት የማፍራትን ተግባር ከመፈጸም ባሻገር እያንዳንዷ ቤተ ክርስቲያን መሪዎችን የማሳደጊያ ስልት ያስፈልጋታል። በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ ለአመራርነት ተሰጥዎ ያላቸውን ሰዎች ለይቶ ለማወቅና ለማስታጠቅ የመሪነትን መስመር ለመዘርጋት ቤተ ክርስቲያን ረዥም ዕድሜ እንድትኖር እንዲሁም ለቀጣዩ ትውልድም እጅግ አስፈላጊ ነው። ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው ቢጋር መሪዎችን ለይቶ ለማወቅ፣ ለማስታጠቅና እግዚአብሔር እንዲሠሩ ለጠራቸው ዓላማ ለመሾም የሚረዳ ነው። I. ተልእኮ • ትርጉም፦ የእግዚአብሔርን ጥሪ ማወቅ፣ መረዳት እናም ለመሪነቱ እና ለጌትነቱ ምላሽ መስጠት። • ልብ ሊባሉ የሚገቡ ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 2ጢሞቴዎስ 1፥6-14፣ 1ጢሞቴዎስ 4፥14፣ ሐዋርያት ሥራ 1፥8፣ ማቴዎስ 28፥18-20 • ወሳኝ ሐሳብ፦ በእግዚአብሔር ሥልጣን ላይ - ከእግዚአብሔር የሆነ መሪ ከእግዚአብሔር ዕውቅና ያለው ጥሪ እና ሥልጣን ላይ ርምጃ ይወስዳል፣ ከእግዚአብሔር ከሆኑ መሪዎች እና ቅዱሳን ዘንድ ዕውቅናን ያገኛል። • ዋና ዋና ነጥቦች በከተማ ያሉ የቤተ ክርስቲያን ተካይ መሪዎችን ማሳደግ፦ ከተልእኮ ወደ ማኅበረ ሰብ

1 Adapted from a seminar by Rev. Dr. Don L. Davis in Ripe for Harvest , pp. 377-381.

Made with FlippingBook - Share PDF online