Church PLANT Manual, Amharic Edition
ክፍል 3: ማሳደግና ሽግግር • 81
ኢምፓክት ኢቫንጀል ትምህርት ቤትና ስለሚሰጠው የተማሪዎች ኀላፊ ሥልጠና የበለጠ ለማወቅ ፍላጎት ካላችሁ የኢቫንጀል አሠልጣኛችሁን ጠይቁ እና ዕድሉን እንድታገኝ ይመራችኋል። እንቅስቃሴዎች ተፈጥሯዊና ተለዋዋጭ እንደ መሆናቸው፣ እንዲሁም አንድ ዐይነት አስተሳሰብና እይታ ካላቸው ሰዎች ስለሚመነጩ በአብዛኛው በፍጥነት የሚሠራጩ ናቸው። አንድ እንቅስቃሴ ስለመጀመር ለመናገር ሊገደዱ ይችላሉ። ስለ ቤተ ክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴዎች ስልትና ዕቅድ ማሰብና መነጋገር ምንም ችግር የለውም። በተለይ ቤተ ክርስቲያን እስከ ምድር ዳርቻ ትሰፋ ዘንድ ያለውን የጌታን ልብ ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው። የቤተ ክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴ መነሻ ምንጩ ጌታችን የሰጠው ታላቁ ተልእኮ ነው። 2 ስለዚህ እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴ የዚህ አካል ሲሆን ለርሱ ክብር የሚውሉ ናቸው። ይህንን ሁሉ ካልን፣ የምትመርጡት መንገድ ምንም ይሁን ምን፣ እንደ ቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን የማብዛት እይታችሁን ለመወሰንና ይህን ዓላማ ለመጀመር በጸሎት፣ በጥልቀትና ለዚህ ታስቦ የተመደበ ጊዜ በመስጠት መትጋት ይጠበቅባችኋል። በሚገባ ካላሰባችሁበት የማብዛት ዕቅዳችሁ ላይሰምርና ተሰነካክሎ የመውደቅ ዕድሉ የሰፋ ይሆናል። ለዚህም ዐላማ፣ መሪዎች፣ ቤተ ክርስቲያንን ሊተክሉ የሚችሉ ሰዎችን የመለየት፣ የማስታቅና የመሪነት ሥልጠና የመስጠት ሥራ አስፈላጊ ነው። በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ የመብዛት ራእይን ለመገንባት በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ ያሉት እያንዳንዱ መሪዎች የቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድን አባል ሊሆን የሚችልበትን ሁኔታ በማየትና ጌታም በዐዲስ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ጥረት ውስጥ ለማገልገል ሊጠቀምበት እንደሚችል ለማየት ይረዳችኋል።
2 See Matthew 28:18-20.
Made with FlippingBook - Share PDF online