Church PLANT Manual, Amharic Edition
80 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
ዕውቅና ባላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤቶች፣ በአካል ወይም በርቀት መማር የምትሹ ዕውቅና ወዳለው የኢቫንጄል ትምህርት ቤታችን ተማሪዎችን መላክ ትችላላችሁ። ይሁን እንጂ፣ ብዙ ቡድኖችን የመላክና የማብዛት ሥራው ላይ የማሳተፍ ውጠን ካላችሁ ጸልዩበት፣ ዐስቡበትና ከኢቫንጄል ትምህርት ቤት ጋራ አጋር በመሆን በራሳችሁ ዐውድ ውስጥ ትምህርትና ሥልጠናውን እንዴት ማከናወን እንደምትችሉ በዚህ ውይይት መጨረሻ ላይ የቀረበውን “የቤተ ክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴ መፍጠር” የሚለውን ተመልከቱ። III.ከሌሎች ቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኖች ጋራ ትስስር መፍጠር የቤተ ክርስቲያን ተካዮች ከሌሎች ቤተ ክርስቲያን ተካዮች ጋራ በአጋርነት የመሥራት ፍላጎት ያላቸው በርካታ አብያተ ክርስቲያናትና ቡድኖች አሉ። በተለይ በከተማ አካባቢ ቤተ ክርስቲያን ለመትከል ፍላጎት ያላቸው ይበዛሉ። በአካባቢያችሁ ከሚገኙ በርካታ የቤተ ክርስቲያን ተካዮች ጋራ የትብብር ግንኙነቶችን መፈለግና ዐብሮ ለመሥራት ከእናንተ ዐውድና ራእይ ጋራ የሚጣጣመውን የቤተ ክርስቲያን ተካዮች ትስስር የትኞቹ እንደሆኑ በጸሎት ማወቅ ያስፈልጋችኋል። ይህ የመንግሥቱ ሥራ እንደ መሆኑ መጠን ከማንኛውም አንድ ልብና አስተሳሰብ ካላቸው አብያተ ክርስቲያን ጋራ ዐብሮ ለመሥራት የሚኖሩ አማራጮች ላይ ምርምር እንድታደርግ እናበረታታለን። IV.የቤተ ክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴ መፍጠር ምንም እንኳን ከቤተ ክርስቲያን ተካዮች ጋራ ተባብሮ የመሥራት ፍላጎት ያላቸው ብዙ የቤተ ክርስቲያን የትስስር አውታሮች ቢኖሩም፣ አንዳንድ ቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኖች ኢቫንጀል ትምህርት ቤት ይካፈላሉ ይህንን የሚያደርጉትም አንድ ብቻ ቤተ ክርስቲያን ለመትከል የሚያስችል ሞዴል ለመሥራት ሳይሆን ዐዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን የመትከል እንቅስቃሴን ለመፍጠር ነው። ይህ የእናንተም ፍላጎት ከሆነ፣ ወርልድ ኢምፓክት ኢቫንጀል ትምህርት ቤት የቤተ ክርስቲያን/ የተማሪዎች ኃላፊ ሥልጠናን ይሰጣል። ይህ ሥልጠና ዐዳዲስ የቤተ ክርስቲያን ተካዮችን እንቅስቃሴ ለማስታጠቅ፣ ለመላክና ለመከታተል ታስቦ በኢቫንጀል ትምህርት ቤት የተዘጋጀ ነው። ስለ ወርልድ
Made with FlippingBook - Share PDF online