Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 3: ማሳደግና ሽግግር • 79

የመብዛት ሞዴሎች (መንገዶች)

I. አመራርን ብቁ ለሆኑ መሪዎች ማሸጋገርና ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ መትከል ይህ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ሚስዮናዊ ሞዴል የሚባል ሲሆን ባለፉት ዓመታት በዓለም ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ ሞዴል ነው። አንድ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን አንድን ቤተ ክርስቲያን ሲተክል ለረዥም ጊዜ እረኛ ሆኖ እንደማያገለግል ያውቃል። የዚህ ሞዴል ዓላማ ከማኅበረ ሰቡ የወጡ የአጥቢያ መሪዎችን (የአንድ አካባቢ) ለመጋቢ አመራር ማብቃት፣ ማስታጠቅ፣ ለተልእኮ አገልግሎት ሥራ በተለመደው ሂደት ውስጥ አደራ መስጠት ነው። ከዚያም በቀጣይ የሚስዮናዊ ቡድኑ ዒላማ ወደተደረገው የማኅበረ ሰብ ክፍል በመሄድ የተከላ ሂደቱን ይደግማል። ይህ ዘዴ በወርልድ ኢምፓክትስ ቤተ ክርስቲያንን ተከላ ሰነዶች ላይ በግልጽ ተንጸባርቋል፣ እስከ አሁን ድረስ፣ በአብዛኛው ባህል ተሻጋሪ ሚሲዮናዊያን ሆነው ወደ አሜሪካ ከተሞች ውስጥ ለሚያገለግሉ የወርልድ ኢምታክት ሠራተኞች የተዘጋጀ ነው። በዚህ ሞዴል፣ የቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኑ ቤተ ክርስቲያን ሲተክል ቤተ ክርስቲያኗ የምትልክ ቤተ ክርስቲያን እንድትሆን ራእይ ሰንቆ ይሠራል። ከጅማሬዋ አንሥቶ፣ ቤተ ክርስቲያንኗ የምትተከለው ቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኖችን ለማቋቋምና ለመላክ ነው። የተተከለው ቤተ ክርስቲያን፣ ልጅ ቤተ ክርስቲያንን ይተክላል (ይወልዳል)። የተተከለው ቤተ ክርስቲያን ያለበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን፣ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚልኩ ሊሆኑ ይገባቸዋል (ሐዋርያተ ሥራ 13፥1-3) ከሁሉ የተሻሉ መሪዎቻቸው ሄደው ዐዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲተክሉ የእግዚአብሔር መንግሥት በእነርሱ ዐውድ እንዲስፋፋ ማድረግ ነው። ልትልኳቸው ያሰባችኋቸውን የቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኖች ቤተ ክርስቲያንን ለመትከል መደበኛ ዝግጅት ያደርጉ ዘንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ውስጥ እንዲያልፉ በከፍተኛ ሁኔታ እንመክራለን። የወደፊት ቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኖቻችሁን ፍቃድና II. የምትልክ ቤተ ክርስቲያን መሆን፦ የቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኖችን ማሳደግና መላክ

Made with FlippingBook - Share PDF online