Church PLANT Manual, Amharic Edition

78 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ቤተ ክርስቲያንን መትከል በሁሉም ረገድ ከፍተኛ ጥረትን የሚጠይቅ ሥራ ነው። ቤተ ክርስቲያን የሚተክሉ ቡድኖች ደቀመዝሙር ማፍራትን እንደ ዋና መርሕ ይዘው በእጃቸው ባለው ሥራ ላይ ማተኮር ይጠበቅባቸዋል። መብዛት በቡድኑ አእምሮ ውስጥ ቀዳሚ ትኩረት ካልተሰጠው ብዙ ፈተናዎችን ያስከትላል። ትኩረታቸውን አንዲት ቤተ ክርስቲያንን ብቻ በመትከል ላይ ያደረጉ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች ቍጥራቸው ሲበዛና አመራሩን ለቀጣዩ ትውልድ የሚያሸጋግሩበት ጊዜ ሲደርስ ከፍተኛ ፈተና ይገጥማቸዋል። ቤተ ክርስቲያንን የሚተክሉ ቡድኖች ለመብዛት ሆነ ብለው እስካልሠሩ ድረስ ለማሳደግ ለብዙ ጊዜ የደከሙበትን አባል እንደሚያጡ በማሰብ ይቸገራሉ። ዐዲስ የተተከለውን ቤተ ክርስቲያን ውጤታማነትና ዐቅም ያዳክማል ብለው ስለሚያስቡ ጥሩ ጥሩ መሪዎቻቸው ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትን ለመትከል እንዳይሄዱ ይቃወማሉ። ይህም ደግሞ ብዙ ጊዜ አብያተ ክርስቲያናት ልጅ ቤተ ክርስቲያን ለመትከል ምርጥ ከሚሉት ያነሰ ቡድን ይልካሉ። በርግጥም፣ የቤተ ክርስቲያን ትኩረት አንድ-ቤተ ክርስቲያንን በማሰብ ብቻ ከተገደበ ለመጸለይ፣ ለማቀድና አንድ ቤተ ክርስቲያንን መምራትና ከእነሱ ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴን ከግምት የማስገባት ተገግዳሮትን ለመታገል የሚያስፈልገው ጊዜና ቦታ ፈጽሞ አይገኝም። ይህንን ሁሉ ካልን፣ አንድ የቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድን መባዛት/ማብዛትን የልባቸው ማዕከል እንዲሆን በትጋት መስራት አለባቸው። ከዚህ በታች የተለያዩ ሞዴሎችን እናቀርባለን። ለሁሉም ዐውድ ተስማሚ የሆነ “ለሁሉም ልክ የሚሆን” ሞዴል እንደሌለ እናውቃለን። ዐውዳዊ ማድረግ ቍልፍ ነው። ይሁን እንጂ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ሞዴሉ ምንም ይሁን ምን በቁጥር መብዛት መጀመራቸው በጣም አስፈላጊ ነው። መብዛትን እንደ መጨረሻ ግባቸው የሚረዱ የቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኖች የመጀመሪያ ቤተ ክርስቲያናቸውን በተለየ መልኩ የመትከልን ሂደት ያከናውናሉ። እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድን መጀመሪያ ከተከሉት ቤተ ክርስቲያን አንድ ቀን በሆነ መንገድ የሚለቁበት ቀን ይመጣል “ልጃቸው” በታላቅ ግልጽት ለሥራ፣የፈጠራ ችሎታ፣ ራስን ከሁኔታው ጋር የማስማመማት ችሎታ፣ቅልጥፍናና ጥበብ ያለው ስራ የሚያከናውነኑበት ጊዜ ሲደርስ ነጻ ይወጣሉ።

Made with FlippingBook - Share PDF online