Church PLANT Manual, Amharic Edition
ክፍል 3: ማሳደግና ሽግግር • 77
ትምህርት 9 የመብዣ መንገዶችን መቀየስ ሬቨረንድ ቴድ ስሚዝ
የመብዣ መንገዶችን መቀየስ የመጀመሪያ ቤተ ክርስቲያናችሁን ለመትከል እየታገላችሁ ስለማባዛት ማሰብ አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል እናውቃለን። ይሁን እንጂ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያመላክተው ጤናማ ነገሮች ያድጋሉ። 1 ኢየሱስ በሰገነት ላይ የተሰበሰቡትን ጥቂት የደቀ መዛሙርት ቡድን (የሐዋርያት ሥራ 1፥13) በወንጌል በኩል ዓለምን እንዲለውጡ ዐስቦ ነበር። በርግጥም እንደ ጳውሎስና ጓደኞቹ ያሉ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች “ዓለምን” አንደ ገለባበጡ (የሐዋርያት ሥራ 17፡6) ይነገር ነበር። ዓለም አቀፍ የወንጌል ዐደራ በጌታችን በሁሉም የታላቁ ተልእኮ መልእክቶች ውስጥ በግልጽ ተቀምጧል። (ለምሳሌ፦ ማቴዎስ 28፥18-10)። የመጀመሪያ ቤተ ክርስቲያን በምትተክሉበት ጊዜ፣ ቡድናችሁ “እንዴት እንበዛለን” ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ መልስ ለመስጠት በጥሞና ማሰብ እና በሰፊ ሁኔታ መታገል ይኖርባችኋል። በዚህ ክፍል ውሰጥ የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን ከመትከላችሁ በፊትም ቡድናችሁ ደቀ መዝሙርት ማፍራት የሚችሉበትን ልዩ መንገድ እንዲያስተውሉ ለማበረታታት ጥቂት ምሳሌዎችን እንመለከታለን። በዚህ ክፍል የቀረቡት ምሳሌዎች አንድ የቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድን ደቀ መዛሙርት ማፍራትን በቤተ ክርስቲያን እድገት ውስጥ ወሳኝ እንደሆነና ሆነ ብሎ ትኩረት ሊሰጥበት እንደሚገባ ይጠቁማሉ። መብዛት በአጋጣሚ የሚከናወን ነገር እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል። ከጠላት ተግዳሮት ባሻገር፣ ወደ መብዛት ስትገሰግሱ ቡድናችሁን ብዙ መሰናክሎች ይገጥሙታል። ለመብዛት አንዱ ቍልፍ መሰናክል ቡድናችሁ ለመብዛትና ደቀ መዛሙርት ለማፍራት አስፈላጊውን ትኩረት እና ጊዜ አለመስጠት ነው።
1 Biblical texts like Mark 4:26-32 and 1 Corinthians 3:6 underscore the metaphor.
Made with FlippingBook - Share PDF online