Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 4፥ ሁሉንም ነገር በጋራ ማድረግ (ማቀናጀት) • 91

ትምህርት 10 በአገልግሎት ውስጥ ጥበብን መጠቀም 1

በቤተ ክርስቲያን ተከላ ተግባር ውስጥ በሚገባ ስትሳተፉ ጥንቃቄ ካላደረጋችሁ ትርምስና የስሜት መናወጥ በሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች ትጠመዳላችሁ። ጊዜያችሁን በአግባቡ መጠቀም፤ ማድረግ ከምትችሏቸው ነገሮች ይልቅ ማድረግ ላለባችሁ ነገሮች ቅድሚያ መስጠት ይህንም በአገልግሎታችሁ ውስጥ በጥበብ በተግባር ማዋላችሁ በተገቢው መልኩ እንድታገለግሉና ጉዟችሁን እንድትቀጥሉ ይረዳችኋል። ስለዚህም፣ ቤተ ክርስቲያን ለመትከል ከሚያስፈልጓችሁ ጠቃሚ መሣሪያዎች አንዱ ሥራችሁን በመደበኛ ሂደት መገምገም ነው። የእግዚአብሔርን ዐላማ መፈጸም የምንችለው እንዴት ነው? በአገልግሎት ውስጥ ጥበብን በመጠቀም። ጥበብ በእውነቶች መካከል የተሻለውን እውነት መምረጥ ነው። ኤፌሶን 5፥15-17 - እንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ። ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ። ስለዚህ ሞኞች አትሁኑ፤ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ። ምሳሌ 24፥3-6 - ቤት በጥበብ ይሠራል፤ በማስተዋልም ይጸናል፤ በዕውቀትም ውድና ውብ በሆነ ንብረት፣ ክፍሎቹ ይሞላሉ። ጠቢብ ሰው ታላቅ ኀይል አለው፤ ዕውቀት ያለውም ሰው ብርታትን ይጨምራል፤ ጦርነት ለመግጠም መልካም ምክር፣ ድል ለማድረግም ብዙ አማካሪዎች ያስፈልጋሉ።

1 Adapted from seminars by Rev. Don Allsman in Ripe for Harvest , pp. 65-76, 457-460.

Made with FlippingBook - Share PDF online