Church PLANT Manual, Amharic Edition

92 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

በአገልግሎት ተግባራት ውስጥ ጥበብን መጠቀም የሚያስገኛቸው ጥቅሞች • ግልጽ የሆነ ርእይ ቡድኑ በተገቢው መሠረት እየሠራ መሆን አለመሆኑን ሁሉም በግልጽ እንዲያይ ያስችለዋል። • ግልጽ የሆነ መመሪያ ግራ መጋባትን በማስወገድ ተስፋና በራስ መተማመንን ያጎናጽፋል። • እያንዳንዱ ሰው ኀላፊነቱን ያውቃል። • ሰዎች እዚያው ቆይተው ለራእዩ መፈጸም መትጋት ይፈልጉ እንደሆነ ወይም ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ይፈለጉ እንደሆነ መወሰን ይችላሉ። ራእዩን የማይደግፉ ሰዎች በቡድናችሁ ውስጥ አያስፈልጉም። በቡድናችሁ ውስጥ እንዲህ ዐይነት ሰዎች ካሉ ችግር ፈጣሪ ወይም በንቃት የማይሳተፉ መሆናቸው አይቀሬ ነው። • የባከኑ ተግባራት አነስተኛ ናቸው (በዕድሎች ላይ ሳይሆን በራእዩ ላይ አትኩሩ)። • ለራእዩ ምንም አስተዋጽኦ ለማያበረክቱ ዕድሎች “አይሆንም” ማለት የምትችሉበትን ከባቢ ትፈጥራላችሁ። • ለራእዩ የሚያበረክቱ መልካም አጋጣሚዎችን ማወቅና መጠበቅ ያስችላል። ነህምያ ለንጉሡ ራእዩን የሚያብራራት አጋጣሚ ሲፈጠር ዝግጁ ነበረ። • ግልጽነትና መመሪያ መኖሩ የቡድን አባላትን ከጉዳትና ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋል ። ወታደሮች የሚሞቱት ግልጽነትና መመሪያ ሳይኖር ሲቀር ነው። • ጥበብ በራእይ (እምነት) እና እውነታ (ብልኅነት) መካከል ሚዛን መጠበቅን ግድ ይላል።

• ግልጽ መመሪያ መኖር ሰዎችን ለተሻለ ፈጠራ ያነሣሣል። • “የሁኔታዎች ተጠቂ” መሆንን በመቀነስ ንቁ ተሳታፊ መሆን የሚያስችሉ መሣሪያዎችን ያቀርባል።

Made with FlippingBook - Share PDF online