Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 4፥ ሁሉንም ነገር በጋራ ማድረግ (ማቀናጀት) • 93

• መርሖቹ በየትኞቹም የቡድን ተግባራት ውስጥ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው። ጥበብን የመጠቀም ልምድ ማዳበር እያንዳንዱን ተግባር ትልቅም ይሁን ትንሽ ውጤታማ ያደርጋል። በአገልግሎት ተግባር ውስጥ ጥበብን የመጠቀም እንቅፋቶች “. . . የርሱን ዕቅድ አንስተውምና” (2 ቆሮንቶስ 2፥11) • “ከዚህ ቀደም በዚህ መንገድ ሠርተን አናውቅም።” እግዚአብሔር ለሥራው እንቅቅዳት የሚሆኑ ወጎችንና ልማዶችን አይጠቀምም። በአንድ ወቅት በሆነ መንገድ ስለተሠራ ሁልጊዜም በዚያው መንገድ መሠራት አለበት ማለት አይደለም፤ ይህ ጥበበኛ አካሄድ አይደለም (ሐዋርያት ሥራ 10)። • “ደኅና ነን።” በግልጽ የሚታይ (ወይም እውነተኛ) ስኬት ይበልጥ ፍሬያማ ከመሆን ሊገታችሁ ይችላል (ዮሐንስ 15፥2) • “የተደራጁ መሆን በመንፈስ ቅዱስ መመራትን ይገታል።” እግዚአብሔር ዕቅድ አለው፤ ዕቅዱንም በእኛ ውስጥ እየሠራ ነው። ዕቅድ በማቀድና በዕቅዱ መሠረት በመሥራታችን ልንሸማቀቅ ወይም ልናፍር አይገባም። • “ዋናው ነገር የምንሠራው ሥራ ሳይሆን የእግዚአብሔር በረከት ነው። ድልድዩን ስንደርስ እንሻገረዋለን።” አንዳንድ ነገሮች እየዋሉ እያደሩ የተሻሉ እንደሚሆኑ እሙን ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ይህ ዐይነቱ አመለካከት ሥርዐት አልበኛነትን ያመላክታል። • “ልናደርገው ይገባል” ከማለት ይልቅ “ማድረግ እንችላለን።” በስሜት ተመሥርቶ ውሳኔ መወሰን፣ ነገሮችን ማራዘም። • “ድካም”። “ድካም ሁላችንንም ፈሪ ያደርገናል” ሲደክመን

ዐዳዲስ ሐሳቦችን የምንቃወምና ያለንን ሀብት በአግባቡ የማንጠቀም እንሆናለን። ይህ ዐይነት ተቃዋሚነት መልካም አጋጣሚዎችን ወደ ማጣት ይዳርገናል።

Made with FlippingBook - Share PDF online