Church PLANT Manual, Amharic Edition
መቅድም • xvii
ቤተ ክርስቲያን ተከላ የማኅበራዊና ባህላዊ ለውጦች መለኮታዊ አቃጣጣይ ነው።
በመጨረሻም፣ የክርስቶስ ወንጌል ምሥራች በአንድ ማኅበረ ሰብእ ውስጥ ሕያው ሲሆን በአካባቢው ያሉ ጕባኤዎች በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና በባህላዊ መንገድ የለውጥ ብርቱ ወኪል ይሆናሉ። አብያተ ክርስቲያናት የተስፋ ምስክር ማዕከላት ይሆናሉ፤ በፍትሕ፣ በትምህርት፣ በጤና እና በማኅበረ ሰብ እድገት ውስጥ ተግባራዊ መገለጫዎችን ያቀርባሉ። በማኅበረ ሰቡ ውስጥ በክርስቶስ በኩል እውነተኛውን አምላክ ካለማወቅ የሚመጣውን መንፈሳዊ ባዶነት ብቻ ሳይሆን የማኅበረ ሰቡን አካላዊና ማኅበረ ሰባዊ አስፈልጐቶችንም በተመለከተ ይሠራሉ። ከዚህ ቀደም ወንጌልን ሰምተው በማያውቁ አካባቢዎች ቤተ ክርስቲያናትን በመትከል ክርስቲያኖች ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣና የእግዚአብሔር መንግሥት በሙሉ ገጽታዋ እንድትታይ የማድረግ እንቅስቃሴን ሊጀምሩ ይችላሉ። በማጠቃለያ፣ ኢየሱስ ገና ባልታወቀባቸው ቦታዎች ውስጥ አብያተ ክርስቲያናትን ለመትከል በሐዋርያዊ ጥሪ ውስጥ ስትሳተፉ የእግዚአብሔርን ተልእኮ ትፈጽማላችሁ። ቤተ ክርስቲያን ተከላ በዋናነት የቤተክርስቲያን ጥሪ የእግዚአብሔርን ልብ በተግባር ማሳየት መሆኑን ያስተጋባል። ታላቁ ተልእኮንም ያካትታል፣ የእግዚአብሔር መንግሥት መገለጥን ያሰፋል፣ እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ ያለውን ፍቅር ያሳያል እንዲሁም የመንግሥቱ ሕይወት የሁሉን አቀፍ ለውጥ አቀጣጥይ መሆኑን ያመለክታል። ይህ ተልእኮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኀላፊነትን የሚወጣና እጅግ በጣም ጥልቅ ከሆኑት የክርስትና እምነት ተግባራዊ መገለጫዎች ጋራ የሚጣጣም በመሆኑ ዛሬ ላይ የቤተ ክርስቲያን አጣዳፊና አስገዳጅ ተግባር ያደርገዋል። የእግዚአብሔርን መንግሥት፣ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን በምታገለግሏቸው ማኅበረ ሰቦች ውስጥ በምትገልጡበት ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ዐብሯችሁ እንዲሄድ ከልባችን እንጸልያለን። በመንገዳችሁ ሁሉ ርሱ ከእናንተ ጋራ ይሁን። ዶ/ር ዶን ዳቪስ የፕሬዘዳንቱ ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚ አማካሪ መጋቢት 19፣ 2016 ዓ.ም.
Made with FlippingBook - Share PDF online