Church PLANT Manual, Amharic Edition
xvi • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
ክርስቲያን በኩል መደረግ ያለበት ሲሆን ይህም ዐዲስ አማኖች በእምነታቸው እንዲያድጉ የሚያስችል መሠረት የሚሆን ማኅበረ ሰብእ ይጥላል። የቤተ ክርስቲያን ተከላ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ወኪል መሆኗን ዕውቅና ይሰጣል። ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ (ዘፍጥረት 12፥1-3) ከሚለው ለአብርሃም ከገባለት የተስፋ ቃል አንሥቶ ዮሐንስ ባየው ራእይ ውስጥ የተገለጹት ሕዝቦች፣ ነገዶች፣ ወገኖችና ቋንቋዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እስከሚሰግዱበት (ራእይ 7፥9-10) ትእይንት ድረስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርክት የእግዚአብሔር መንግሥት አገዛዝ በምድር ላይ የመስፈንን ጭብጥ ይተርካል። ቤተ ክርስቲያን መትከል ሐዋርያዊ ተግባር ሲሆን ይህም የዚህ መንግሥት መስፋፋት ተጨባጭ መገለጫ ነው። ክርስቶስ የሚታወቅበትና የሚከብርበትን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መትከል የእግዚአብሔር ንጉሥነትና አገዛዝ የሚገለጥበትን (አካባቢ) እና አገዛዙ በዐዲስ ሕዝቦች መካከል (ወኪል) የሚታይበትና የሚታወጅበትን መንገድ ያሳያል። ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ለዓለም ያለው ጽኑ ፍቅር የዐዲስ ኪዳን ዋነኛ መልእክት ነው። ዮሐንስ 3፥16 በልጁ መሥዋዕትነት ለሰው ልጆች ሁሉ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍቅር በመግለጽ ይህን ዋና ጉዳይ በብርቱ ጠቅለል አድርጐ ገልጾታል። አብያተ ክርስቲያናትን መትከል ይህን ፍቅር በየአካባቢው፣ በየሰፈሩና በየመንደሩ ተጨባጭ በሆነ መልኩ መግለጥ ነው። ለወንጌል ሩቅ የሚባል፣ የተለየ ወይም ፈታኝ የሚባል ቦታ የለም፤ በየትኛውም ስፍራ ያሉ ሁሉ እግዚአብሔር ትሩፋኑን ለማዳን ያለው ሉዓላዊ ዕቅድና ዘላለማዊ ዓላማ ሊሰሙ ይገባል። እያንዳንዷ ዐዲስ ቤተ ክርስቲያን የመትከል ጥረት የእግዚአብሔርን የድነት ግብዣ አቃፊነት የሚያሳይ ማስረጃ ነው። ያ ዐዲሱ የአማኞች ስብስብ የእያንዳንዱን ሰው እና እያንዳንዷ ነፍስ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ ውስጥ ያላትን ዋጋ የሚጐላና የሚያረጋግጥ ነው። ቤተ ክርስቲያን ተከላ ገና ለሚያምኑ ሰዎች እግዚአብሔር ያለውን ፍቅር በተጨባጭ የሚያሳይ ወኪል ነው።
Made with FlippingBook - Share PDF online