Church PLANT Manual, Amharic Edition
መቅድም የኢየሱስ ስም ገና ባልታወቀባቸው ወይም በማይመለክባቸው አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያናትን መትከል ጥልቅ ጥሪና የክርስቲያናዊ ተልእኮ ዋና አካል ነው። ይህ ተልእኮ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ተልእኮ ዋና ዐሳብ ጋራ የተሳሰረ ሲሆን ይህም በዓለም ያሉ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ጥሪ እንዲያውቁት፣ እንዲሁም በልጁ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መንግሥቱ እንድትገዛ ያደርጋል። ግራ በተጋባውና በተሰበረው ዓለም ውስጥ ጥቂት ተጸብራቅ እንኳ ለዚህ ክቡርና አሁንም ጠቃሚ ለሆነው ፍለጋ አሳማኝ ምክንያቶችን ይሰጣል። ቤተ ክርስቲያን ተከላ ታላቁን ተልእኮ ለመፈጸም ሐዋርያዊ ዘዴን ይጠቀማል። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው የመጨረሻው ትእዛዝ ታላቁ ተልእኮ መባል ይታወቃል (ማቴዎስ 28፥18-20)፤ በዚህ ትእዛዙም “ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” ብሏቸዋል። ይህ ኀላፊነት በቅድሚያ በሚያውቁት ወይም አስቀድሞ በተሰበከበት ዐውድ ውስጥ ይጀምርና ወደ ሁሉም መልክዓ ምድራዊና ባህላዊ ድንበሮች ሁሉ ይዘልቃል። የእግዚአብሔርን የድነትና የትድግና ጥሪ ከዚህ ቀደም ያልሰሙ ወይም ሰምተው ምላሽ ያልሰጡ ሰዎች ሁሉ ሊረዱና ሊቀበሉት በሚችሉት መንገድ ምሥራቹን መስማት አለባቸው። ክርስቶስ በማይታወቅባቸው አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያናትን መትከል ይህን ጥሪ ያስተጋባል፤ ይህም እያንዳንዱ ሕዝብ ያለበት ቡድን ወንጌልን የመስማት ዕድል እንዲኖረው ያስችለዋል። ደቀ መዝሙርነትና ጥምቀት የሚከናወኑት በአጥቢያ ቤተ
xv
Made with FlippingBook - Share PDF online