Church PLANT Manual, Amharic Edition

ቀዳሚ ቃል • xiii

“የአለቆችንና የባለሥልጣናትንም ማዕረግ በመግፈፍ በመስቀሉ ድል ነሥቶ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ” (ቈላስይስ 2፥15)። ምንም እንኳ የጨለማው መንግሥት ቢሸነፍም ሰይጣንና ጭፍሮቹ በቢሊዮን የሚቈጠሩ ነፍሶችን በመንፈሳዊ እስር ጠፍንገው አስረዋቸዋል። አንዳች ነፍስ እንድትጠፋ አይሻም ነገር ግን ሁሉም በወንጌል ኅይል ነጻ ይወጡ ዘንድ ኢየሱስ ለቤተ ክርስቲያኑ ትነሣ፣ ትወጣ፣ ወደ ፊት ትኼድና ትበዛ ዘንድ ተልእኮ ሰጥቷታል። ይህ እጅግ በጣም ወሳኙ የቤተ ክርስቲያን ተግባር ነው - ተልእኮ፥ ይኸውም ሥልጣን ያላቸው ላኪዎች (የታወቁ፣ የታጠቁ፣ የተሾሙ) ሰዎችን ቤተ ክርስቲያን ወዳልተተከለበት አካባባቢ ወንጌልን ለማወጅ፣ ነፍሳትን ለማዳን፣ የተለወጡትን ደቀ መዛሙርት ለማድረግ እንዲሰበስቡ መላክ ሲኾን እንዲሁም በዚያ ማኅበረ ሰብእ ውስጥ የእግዚአብሔርን መንግሥት ፍሬ የሚያፈሩ አብያተ ክርስቲያናትን የሚያበዙ የእግዚአብሔር መንግሥት ማኅበረ ሰቦችን ማብዛት ነው። የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ ቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኖችን ለማሠልጠን የተዘጋጀ ሲኾን መሠረታዊ መርሑም ጤናማ አብያተ ክርስቲያናትን በዚህም ኾነ በዓለም ዙሪያ በድኽነት ውስጥ በሚገኙ ማኅበረ ሰቦች ውስጥ መትከል የሚል ነው። ጌታ በቅርብ ይመጣል፥ ዋጋውም በርሱ ዘንድ አለ። እስከዚያው ድረስ ግን አብያተ ክርስያቲያናት በየስፍራው ይተከሉ ዘንድ የመኸሩ ሠራተኞችን የመለየት፣ የማስታጠቅና የማገዝ ሥራችንን ቸል አንበል። “… ወደ ኋላ [ከሚያፈገፍጉት] አይደለንም…” (ዕብራውያን 10፥39) ቦብ ኤንጅል (ሬቨረንድ) የቤተ ክርስቲያን ተከላ ዳይሬክተር መጋቢት 19፥ 2016 ዓ.ም.

Made with FlippingBook - Share PDF online