Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
/ 1 0 3
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
7. ለክርስቶስ ለመኖር “ለራስ መሞት” ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚያሳይ ምሳሌ ምን ሊሆን ይችላል? የኢየሱስ ባሪያ ሆነን መኖራችን “ሀብታም እና ዝነኛ” መሆን እንደማንችል ያረጋግጣልን? መልስህን አስረዳ። 8. “ብንኖርም ብንሞትም የጌታ ነን” የሚለውን አባባል አብራራ። ለራሱ ሞቶ ራሱን ለእግዚአብሔር ክብር አሳልፎ የሰጠ ሰው ምን ዓይነት አመለካከት አለው?
የሚጠራው ቃል ክፍል 2
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
እኛን የለወጠ እና ወደ ደቀመዝሙርነት የጠራን ያው ቃል በእግዚአብሔር ህዝብ (ላኦስ) ውስጥ እንደ ክብሩ ቤተሰብ አባላት በመሆን በማህበረሰብ ውስጥ እንድንኖር እና እንድንሰራ ይጠራናል። የእግዚአብሔር ሕዝብ አባላት እንደመሆናችን መጠን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ነፃነታችንን ታላቁን ትእዛዝ ለመፈጸም እንደ ዕድል ለመጠቀም፣ ማለትም ሌሎችን ለመውደድና ለማገልገል እንዲሁም ሌሎችን ለማዳን ተጠርተናል። እንደ እግዚአብሔር ቤተሰብ አባላት፣ ለደቀመዝሙርነት፣ ለማህበረሰብ እና ለነጻነት የተጠራን እንደመሆናችን መጠን፣ እኛም በመንግሥቱ ተልዕኮ እንድንሳተፍ ተጠርተናል። እግዚአብሔር አባታችን ታላቁን ተልእኮ እንድንፈጽም፣ ከመንፈሳዊ ጠላታችን ዲያብሎስ ጋር እንድንዋጋ እና የመንግሥቱን ሕይወት በፍቅራችን እና በበጎ ሥራችን እንድናሳይ ጠርቶናል። ለዚህ የሚጠራው ቃል ሁለተኛ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እንድታይ ለማስቻል ነው፡- • እንደ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንድንኖር የሚጠራን ያው ቃል በእግዚአብሔር ህዝብ (ላኦስ) ውስጥ እንደ ክብሩ ቤተሰብ አባላት በመሆን በማህበረሰብ ውስጥ እንድንኖር እና እንድንሰራ ይጠራናል። • የእግዚአብሔር ሕዝብ አባላት እንደመሆናችን መጠን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ነፃነታችንን ታላቁን ትእዛዝ ለመፈጸም እንደ ዕድል ለመጠቀም፣ ማለትም ሌሎችን ለመውደድና ለማገልገል እንዲሁም ሌሎችን ለማዳን ተጠርተናል። • ነጻ እንደወጡ የእግዚአብሔር ሕዝብ አባላት፣ ለተልዕኮ ተጠርተናል። የ21ኛው ክፍለ ዘመን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን ታላቁን ተልእኮ እንድንፈጽም፣ አሕዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት እንድናደርግ፣ ከመንፈሳዊ ጠላታችን ዲያብሎስ ጋር እንድንዋጋ እና የመንግሥቱን ሕይወት በፍቅራችንና በበጎ ሥራዎቻችን እንድናሳይ ተጠርተናል።
የክፍል 2 ማጠቃለያ
4
Made with FlippingBook Annual report maker