Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
This is the Amharic edition of Capstone Module 1 Mentor Guide.
ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ
ለውጥ እና ጥሪ
U R B A N M I N I S T RY I N S T I T U T E የ WO R L D I M PA C T I N C . ሚኒ ስ ት ሪ ነው
የመምህሩ መምሪያ
ሞጁል 1 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች
AMHARIC
የ መ ም ህ ሩ መ መ ሪ ያ
ለውጥ እና ጥሪ
ሞጁል 1
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የሚፈጥረው ቃል
የሚወቅሰው ቃል
የሚለውጠው ቃል
የሚጠራው ቃል
ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል ፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከመምህርህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና www.tumi.org/license ን ጎብኝ፡፡
ካፕስቶን ሞጁል 1: - ለውጥ እና ጥሪ የመምህሩ መመሪያ ISBN: 978-1-62932-354-1
© 2005, 2011, 2013, 2015. The Urban Ministry Institute. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው. የመጀመሪያ እትም 2005 ፣ ሁለተኛ እትም 2011 ፣ ሦስተኛው እትም 2013 ፣ አራተኛ እትም 2015 ፡፡
በ 1976 የቅጂ መብት ሕግ ወይም ከአሳታሚው በፅሁፍ ከሚፈቀደው በስተቀር የእነዚህን መማሪያ ቁሳቁሶች መቅዳት፣ እንደገና ማሰራጨት እና / ወይም መሸጥ ወይም በማንኛውንም ያልተፈቀደ መንገድ ማስተላለፍ የተከለከለ ነው ፡፡ የፍቃድ ጥያቄዎች በሚከተለው አድራሻ መቅረብ አለባቸው፥ The Urban Ministry Institute ፣ 3701 E. 13th Street, Wichita, KS 67208. The Urban Ministry Institute የWorld Impact አገልግሎት ነው በዚህ ሞጁል ውስጥ የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሙሉ በአዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ የተመሰረተ ነው፡ ፡
ይዘት
የኮርሱ ጠቅላላ እይታ
3 5 7
ስለ ጸሐፊው
የሞጁሉ መግቢያ የኮርሱ መስፈርቶች
13 ትምህርት 1
1
የሚፈጥረው ቃል
41 ትምህርት 2
2
የሚወቅሰው ቃል
67 ትምህርት 3
3
የሚለውጠው ቃል
93 ትምህርት 4 የሚጠራው ቃል
4
119
አባሪዎች
153 የካፕስቶን ሥርዓተ ትምህርትን መምራት
161
ትምህርት 1 የመምህሩ ማስታወሻዎች
167
ትምህርት 2 የመምህሩ ማስታወሻዎች
173
ትምህርት 3 የመምህሩ ማስታወሻዎች
179
ትምህርት 4 የመምህሩ ማስታወሻዎች
/ 3
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ስለ ጸሐፊው
ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ የዘ አርባን ሚኒስትሪ ኢንስቲትዩት ሥራ አስፈፃሚ እና የዎርልድ ኢምፓክት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው ፡፡ ትምህርታቸውን በዊተን ኮሌጅ እና በዊተን ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን በቢብሊካል ስተዲስ የቢ.ኤ. (1988) እና በሲስተማቲክ ቲዎሎጂ የኤም.ኤ (1989) ዲግሪዎችን በቅደም ተከተል ማግኘት ችለዋል ፡፡ በተጨማሪም ከአዮዋ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን በሃይማኖት ጥናት (ሥነ-መለኮት እና ሥነ-ምግባር) ፒኤችዲ አግኝተዋል ፡፡ የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር እና የዎርልድ ኢምፓክት ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንደመሆናቸው መጠን የከተማ ሚስዮናውያንን ፣ የቤተ ክርስቲያን ተካዮችን እና የከተማ መጋቢያን ሥልጠናን በበላይነት የሚቆጣጠሩና የሚመሩ ሲሆን ለከተሞች ክርስቲያን ሠራተኞች በስብከተ ወንጌል ፣ በቤተ ክርስቲያን እድገት እና በተቀዳሚ ተልእኮዎች የሥልጠና ዕድሎችን ያስተባብራሉ ፡፡ በተጨማሪም የተቋሙን ሰፊ የርቀት ትምህርት መርሃግብሮች ይመራሉ እንዲሁም እንደ ፕሪዝን ፌሎውሺፕ ፣ ኢቫንጀሊካል ፍሪ ቸርች ኦፍ አሜሪካ ላሉት ድርጅቶች እና ቤተ እምነቶች የአመራር ልማት ኢድሎችን ያመቻቻሉ ፡፡ የበርካታ የማስተማር እና የአካዳሚክ ሽልማቶች ባለቤቱ ዶ/ር ዴቪስ በበርካታ ዕውቅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሮፌሰር እና የፋኩልቲ አባል ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በሃይማኖት ትምህርቶች፣ ሥነ መለኮት ፣ ፍልስፍና እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች (ቢብሊካል ስተዲስ ) እንደ ዊተን ኮሌጅ ፣ ሴንት አምብሮስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሂዩስተን ድህረ ምረቃ የሥነ-መለኮት ትምህርት ቤት ፣ በአዮዋ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን ፣ በሮበርት ኢ ዌበር ኢንስቲትዩት ኦፍ ዎርሺፕ ስተዲስ ባሉ የትምህርት ተቋማት ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡ የከተማ መሪዎችን ለማስታጠቅ በርካታ መጻሕፍትን ፣ ሥርዓተ-ትምህርቶችን እና የጥናት ጽሑፎችን አዘጋጅተዋል ፣ ከነዚህም ውስጥ የ ‹ካፕስቶን› ሥርዓተ ትምህርት ፣ የ TUMI ፕሪሚየር ሲክስቲን ሞጁል ዲስታንስ ኤጁኬሽን ሴሚናሪ ኢንስትራክሽን፥ የከተሞች አብያተ ክርስቲያናት ታሪካዊቷን የኦርቶዶክስ እምነት እንደገና በማደስ ራሳቸው እንዴት ሊታደሱ እንደሚችሉ የሚያትተው ሴክርድ ሩትስ፡ ኤ ፕሪሚየር ኦን ሪትራይቪንግ ዘ ግሬት ትራዲሽን እና ብላክ ኤንድ ሂዩማን፡ ሪዲስከቨሪንግ ኪንግ አስ ኤ ሪሶርስ ፎር ብላክ ትዎሎጂ ኤንድ ኤቲክስ ተጠቃሾች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ዴቪስ እንደ ስታሊ ሌክቸር ሲሪስ ባሉ ትምህርታዊ ጉባኤዎች፣ እንደ ፕሮሚስ ኪፐርስ ራሊስ ባሉ የተሃድሶ ኮንፈረንሶች እና እንደ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኒያ ሊቭድ ቲዎሎጂ ፕሮጄክት ሲሪስ ባሉ ሥነ-መለኮታዊ ጥምረቶች ተሳትፈዋል ፡፡ ዶ/ር ዴቪስ በ 2009 ከአዮዋ ዩኒቨርስቲ የሊበራል አርትስ እና ሳይንስ ኮሌጅ የአልሙናይ የክብር ሽልማት ያገኙ ሲሆን በተጨማሪም የዘ ሶሳይቲ ኦፍ ቢብሊካል ሊትሬቸር እና ዘ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ ሪሊጅን አባል ናቸው ፡፡
/ 5
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሞጁሉ (የትምህርቱ) መግቢያ
ኃያል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን፥
የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን በእግዚአብሔር ቃል የመፍጠር፣ የመውቀስ፣ የመለወጥ እና የመጥራት ሃይል ላይ ጥልቅ እምነት አለን። አስደናቂውን የለውጥ እና ጥሪን በረከት ለመረዳት፣ የእግዚአብሔር ቃል በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ቦታ በጥልቀት መገምገም ያስፈልገናል። የሚፈጥረው ቃል የተሰኘው የመጀመርያው ትምህርታችን እንደ እግዚአብሔር ቃል የቅዱሳት መጻሕፍትን ተፈጥሮ ይዳስሳል። የእግዚአብሔር ፍጹም ታማኝነት የቅዱሳት መጻሕፍትን ፍጹም ታማኝነት እንደሚያረጋግጥ እንመለከታለን። በተጨማሪም እግዚአብሔር አጽናፈ ሰማይን በቃሉ እንዴት እንደፈጠረ እና እራሱን በኢየሱስ ክርስቶስ ከቃሉ ጋር እንዴት እንደሚለይ እንገነዘባለን። መንፈስ ቅዱስ በሚያምኑት ውስጥ አዲስ ሕይወት የሚፈጥርበት መንገድ በመሆናችን፣ በኢየሱስ ቃል ውስጥ በመኖር ደቀ መዛሙርት መሆናችንን እናረጋግጣለን። የቤተክርስቲያን አባላት እንደመሆናችንም መጠን ቃሉን እንደ አንድ ማህበረሰብ እንቀበላለን፣ ይህም የፍጥረትን ሁሉ የመጨረሻ አላማ ይሰጠናል፣ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ክብር ነው። በሚቀጥለው የሚወቅሰው ቃል በተሰኘው ትምህርት የእግዚአብሔር ቃል ኃጢአትን፣ ጽድቅን እና ፍርድን እንዴት እንደሚወቅስ እንመለከታለን። ቃሉ ኃጢአት በይዘቱ ዓለም አቀፋዊ እና በተፈጥሮው ብልሹ መሆኑን ያስተምራል። የእግዚአብሔር ቃል ጽድቅን በተመለከተም የእግዚአብሔርን ፍጹም ጽድቅና የእኛን ያለመብቃት በማሳየት ያስረዳናል፤ እግዚአብሔር በእስራኤል እና በአሕዛብ፣ በቤተ ክርስቲያን፣ በሰይጣን እና በመላእክቱ እና በክፉዎች ሙታን ሁሉ ላይ በፍትሃዊ ውሳኔው እንደሚፈርድ በማስተማር ፍርድን በተመለከተ ያስረዳል። የእግዚአብሔር ቃል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እና ስለቃሉ ታማኝነት በመልእክተኞቹ፣ በነቢያት እና በሐዋርያት በኩል ስለ እውነት ይናገረናል። የሚለወጠው ቃል የተሰኘው ትምህርት ሦስት ደግሞ የሚያተኩረው የእግዚአብሔር ቃል በአማኙ ውስጥ አዲስ ሕይወት ለመፍጠር ባለው ኃይል ላይ ነው። ይህ የሚለውጠው ቃል ከኢየሱስ ወንጌል ጋር ተመሳሳይ ነው፤ እንደገና እንድንወለድ፣ የመታደስ መታጠብ እና የመንፈስ ቅዱስ ተሃድሶ እንድንለማመድ የሚያደርገን የድኅነት ወንጌል ነው። የእግዚአብሔርን የመታደስ ኃይል የሚያሳዩ ተጨባጭ ምልክቶችን በምናምን ውስጥ ቃሉ ያፈራል። አዲስ ሕይወትን የሚፈጥር፣ የሚደግፈን፣ መንፈሳዊ ምግብን የሚመግበን፣ የሚያሳድገን እና ከዲያብሎስ ሽንገላም ራሳችንን እንድንከላከል የሚረዳን ይኸው ቃል ነው። በመጨረሻም የሚጠራው ቃል የተሰኘው ትምህርት አራት (ሜታኖያ)፣ ማለትም ወደ እግዚአብሔር ንስሐ መግባት እና እምነት (ፒስቲስ) የተሰኙ ጽንሰ-ሀሳቦችን ይዳስሳል። በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን እግዚአብሔር አማኙን ከኃጢያት ቅጣት፣ ኃይል እና ህልውና የሚያድንበት መንገድ ነው። በክርስቶስ ከኃጢአት ወደ እግዚአብሔር ስንመለስ፣ ቃሉ የእግዚአብሔርን አዲስ ተፈጥሮ (ዳግም መወለድ) እንድንቀበል እና ወደ እግዚአብሔር ሰዎች (ወደ እግዚአብሔር ላኦስ) በጸጋ በእምነት ብቻ እንድንዋሃድ ያደርገናል። ወደ መዳን የሚጠራን ቃል ደግሞ ወደ ደቀመዝሙርነት (እንደ ኢየሱስ
6 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ባሮች)፣ ወደ ነፃነት (እንደ ተቤዣቸው ልጆች) እና ወደ ተልዕኮ (በምስክርነታችን እና በመልካም ስራዎቻችን ደቀ መዛሙርት ለማድረግ) ይጠራናል። በእርግጥ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል (2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16-17)። የሚፈጥረውን፣ የሚወቅሰውን፣ የሚቀይረውን እና የሚጠራውን የእግዚአብሔር እስትንፋስ የሆነውን ቃሉን ስለምታጠና እግዚአብሔር ይባርክህ!
- ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
/ 7
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የኮርሱ መስፈርቶች
• መጽሐፍ ቅዱስ (ለዚህ ትምህርት ዓላማ ሲባል የአንተ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መሆን አለበት [ለምሳሌ NIV, NASB, RSV, KJV, NKJV, ወዘተ] እና የትርጓሜ ሐረግ መሆን የለበትም [ለምሳሌ The Living Bible, The Message] • እያንዳንዱ የካፕስቶን ሞጁል በሙሉ ትምህርቱ የሚነበቡ እና የሚያወያዩ የመማሪያ መጽሀፎችን አካትቷል ፡፡ እነዚህን ከመምህርህ እና አብረው ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን እንድታነብ፣ እንድታሰላስል እና እንድትመልስ እናበረታታሃለን ፡፡ እነዚህ ጽሑፎች በበቂ ሁነታ መገኘት ባለመቻላቸው ምክንያት (ለምሳሌ ፣ በቂ የመጻሕፍቱ ሕትመት ካለመኖሩ የተነሳ) የካፕስቶን አስፈላጊ የመማሪያ መጽሐፍ ዝርዝራችንን በድረ-ገፃችን ላይ እናስቀምጣለን። የዚህን መጽሐፍ (ሞጁል) ጽሑፎች ወቅታዊ ዝርዝር ለማግኘት እባክህን www.tumi.org/booksን ጎብኝ። • የክፍል ውስጥ ሥራዎችን ለመስራት እና ማስታወሻዎችን ለመውሰድ ወረቀት እና ብዕር ፡፡ • Fee, Gordon D. and Douglas Stuart. How to Read the Bible for All its Worth. Grand Rapids: Zondervan, 1982. • Montgomery, J. W. ed. God’s Inerrant Word. Minneapolis: Bethany, 1974. • Packer, J. I. “Fundamentalism” and the Word of God. London: IVP, 1958. • Sproul, R. C. Knowing Scripture. Downers Grove: IVP, 1977.
አስፈላጊ መጻሕፍት እና ቁሳቁሶች
የተጠቆሙ ንባቦች
8 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የግምገማዎች እና የምዘናዎች ድምር ውጤት በክፍል መገኘት እና የክፍል ውስጥ ተሳትፎ
የኮርሱ መስፈርቶች
30% 90 ነጥቦች
ፈተናዎች
10% 30 ነጥቦች
የቃል ጥናት ጥቅሶች
15% 45 ነጥቦች
የእክሴጀሲስ ፕሮጀክት
15% 45 ነጥቦች
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት
10% 30 ነጥቦች
ንባቦች እና የቤት ስራዎች
10% 30 ነጥቦች
የማጠቃለያ ፈተና
10% 30 ነጥቦች
ጠቅላላ ድምር: 100% 300 ነጥቦች
አጠቃላይ ውጤት መመዘኛ መስፈርቶች በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ መገኘት የኮርሱ ቅድመ ሁኔታ ነው ፡፡ መቅረት በውጤትህ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል። በአስገዳጅ ምክንያት መቅረት ግድ በሚሆንበት ጊዜ እባክህ አስቀድመህ ለመምህርህ አሳውቅ ፡፡ ያመለጠህ ክፍለ ጊዜ ሲያጋጥም ያመለጠህን የቤት ሥራ መስራት እና ስለዘገየህበት ሁኔታ ከመምህሩ ጋር መነጋገር የአንተ ኃላፊነት ነው። ይህ ኮርስ ባብዛኛው በውይይት መልክ የሚካሄድ እንደመሆኑ መጠን የአንተ ንቁ ተሳትፎ በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የሚፈለግና የሚጠበቅ ይሆናል። እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚጀምረው ካለፈው ትምህርት መሠረታዊ በሆኑት ሀሳቦች ላይ በተመሰረተ በአጭር ፈተና ይሆናል። ለፈተናው ለመዘጋጀት ደግሞ የተሻለው መንገድ ባለፈው ትምህርት ወቅት የተወሰዱ የተማሪውን መልመጃ (Student Workbook) እና የክፍል ማስታወሻዎችን መከለስ ነው ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አማኝ እና መሪ እንደመሆንህ መጠን በቃልህ ያጠናኸው ጥቅስ(ቃል) ለህይወትህ እና ለአገልግሎትህ መሰረት ነው ፡፡ በአንጻራዊነት ጥቅሶቹ ከቁጥር አንጻር ጥቂት ቢሆኑም በይዘታቸው ግን ጠቀሜታቸው የጎላ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የተሰጡትን ጥቅሶች (በቃል ወይም በፅሁፍ) ለመምህርህ እንድትናገር ወይም እንድታነብብ ይጠበቅብሃል ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች ለተጠሩበት የአገልግሎት ድርሻ ሁሉ ለማስታጠቅ የእግዚአብሔር ልዩ መሳሪያ ናቸው (2 ጢሞ. 3.16-17) ፡፡ ለዚህ ኮርስ የሚያስፈልጉትን መመዘኛዎች ለማጠናቀቅ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመምረጥ በንባቡ ላይ ተግባራዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ማለትም ፣ የትርጓሜ ጥናት) ማድረግ አለብህ ፡፡ ጥናቱ አምስት ገጾች ርዝመት ሊኖረው ይገባል (በድርብ የተከፋፈለ ፣ ታይፕ የተደረገ ወይም በጥሩ ሁኔታ በእጅ የተፃፈ) እና በዚህ ትምህርት ውስጥ ጎላ ብለው ከተነሱት የክርስቲያን ሚሽን መሠረተ-ትምህርቶች እና መርሆዎች
በክፍል መገኘት እና የክፍል ውስጥ ተሳትፎ
ፈተናዎች
የቃል ጥናት ጥቅስ
የእክሴጀሲስ ፕሮጀክት
/ 9
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ውስጥ አንዱ ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል፡፡ ፍላጎታችን እና ተስፋችን ቅዱሳት መጻሕፍት የአንተን እና የምታገለግላቸውን ሰዎች ሕይወት በተጨባጭ ለመለወጥ ያላቸውን አቅም እንዲረዱ ነው። ኮርሱን በምትወስድበት ጊዜ የበለጠ ለማጥናት በምትፈልገው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ የንባብ ክፍል (በግምት ከ4-9 ቁጥሮች) ለማጥናት አታመንታ፡፡ የፕሮጀክቱ ዝርዝሮች በገጽ 10-11 ላይ የተካተቱ ሲሆን በዚህ ትምህርት መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ እኛ የምንጠብቀው ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሕይወታቸው ውስጥ እና በአገልግሎት ድርሻቸው ላይ በተጨባጭ እንዲተገብሩት ነው ፡፡ ተማሪው የተማራቸውን መርሆዎች ከተግባራዊ አገልግሎት ጋር አጣምሮ የሚኒስትሪ ኘሮጀክት የማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት ፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዝርዝሮች በገጽ 12 ላይ የተሸፈኑ ሲሆን በትምህርቱ መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ የክፍል ሥራ እና የተለያዩ ዓይነት የቤት ሥራዎች በክፍል ትምህርት ወቅት በመምህርህ ሊሰጡህ ወይም በተማሪው መልመጃ (Student Workbook) ውስጥ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ ስለሚፈለገው ነገርም ሆነ የቤት ስራ ስለ ማስረከቢያው ጊዜ ጥያቄ ካለህ መምህርህን ጠይቅ። ለክፍል ውይይት ለመዘጋጀት ተማሪው የተመደበውን ንባብ ከጽሑፉ እና ከቅዱሳት መጻሕፍት ማንበቡ አስፈላጊ ነው ፡፡ እባክህ በየሳምንቱ ከአንተ የተማሪው የመልመጃ መጽሐፍ ውስጥ “የንባብ ማጠናቀቂያ ቅጽ” ን ተመልከት። ለሚደረጉ ተጨማሪ ንባቦች ተጨማሪ ዋጋ/ነጥብ የማግኘት እድል ይኖራል ፡፡ በትምህርቱ መጨረሻ ላይ መምህርህ በቤት ውስጥ የሚጠናቀቅ የመጨረሻ ፈተና (የተዘጋ መጽሐፍ) ይሰጥሃል። በትምህርቱ ውስጥ የተማርከውን እና በአገልግሎትህ ላይ ያለህን አስተሳሰብ ወይም አሠራር እንዴት እንደሚነካው እንድታንጸባርቅ የሚረዳ ጥያቄ ትጠየቃለህ፡፡ ስለ መጨረሻው ፈተና እና ሌሎች ጉዳዮች መምህርህ አስፈላጊውን መረጃዎች ይሰጥሃል።
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት
የክፍል እና የቤት ሥራ ምደባዎች
ንባቦች
ከቤት-የሚሰራ የማጠቃለያ ፈተና
ውጤት አሰጥጥ የሚከተሉት ውጤቶች በክፍለ-ጊዜው መጨረሻ ላይ በዚህ ክፍል ውስጥ ይሰጣሉ እናም በእያንዳንዱ ተማሪ መዝገብ ላይ ይቀመጣሉ።
A - የላቀ ሥራ
D - የማለፊያ ሥራ
B - በጣም ጥሩ ሥራ
F - አጥጋቢ ያልሆነ ሥራ
C - አጥጋቢ ሥራ
I - ያልተሟላ
ለእያንዳንዱ የመጨረሻ ክፍል አግባብነት ያላቸው ውጤቶች ይሰጣቸዋል ፣ ለእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚሰጠው የክፍል ነጥብ በጠቅላላው አማካይነት ውጤት ላይ የሚታሰብ ይሆናል። ያልተፈቀደ የስራ መዘግየት ወይም ሥራዎችን አለማስረከብ በውጤትህ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ፣ ስለሆነም እባክህ አስቀድመህ አቅደህ ከመምህርህ ጋር ተነጋገር።
1 0 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የኤክሴጄሲስ ፕሮጀክት በካፕስቶን ፋውንዴሽን የክርስቲያናዊሚሽን የጥናት ሞጁል ተሳታፊ እንደመሆንህ መጠን ከሚከተሉት ንባቦች በአንዱ ላይ የክርስቲያን ሚሽን እና የከተማ አገልግሎት ምንነት ላይ ኤክሴጄሲስ (ኢንደክቲቭ ጥናት) እንድትሰራ ትጠየቃለህ። መዝሙር 19.7-11 ኢሳይያስ 55.8-11 1 ቆሮንቶስ 2.9-16 2 ጢሞ 3.15-17 1 ጴጥሮስ 1.22-25 2 ጴጥሮስ 1.19-21 የዚህ የትርጓሜ ፕሮጀክት አላማ የእግዚአብሔርን ቃል ምንነት እና ተግባር የሚገልጽ ትልቅ ክፍል በዝርዝር እንድታጠና እድል ለመስጠት ነው። ከላይ ከተጠቀሱት ፅሁፎች ውስጥ አንዱን ስታጠና (ወይንም እርስዎ እና አማካሪዎ በዝርዝሩ ውስጥ የማይገኙበት እርስዎ የተስማሙበት ፅሁፍ)፣ ተስፋችን ይህ ምንባብ የቃሉን አስፈላጊነት እንዴት እንደሚያበራ ወይም እንደሚያብራራ ማሳየት ይችላሉ። በቤተክርስቲያን ውስጥ ለመንፈሳዊነታችን እና ለህይወታችን የእግዚአብሔር። እንዲሁም ትርጉሙን ከግል የደቀመዝሙርነት ጉዞህ ጋር እንዴት እንደምታዛምደው መንፈስ ቅዱስ ማስተዋልን እንዲሰጣችሁ እንመኛለን፣እንዲሁም እግዚአብሔር በአሁኑ ጊዜ በቤተክርስቲያናችሁ እና በአገልግሎታችሁ ከሰጠችሁ የመሪነት ሚና ጋር። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት እንደመሆኑ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄሲስ) ለመስራት የጥናት ክፍሉን በአውዱ ውስጥ መረዳት ያስፈልጋል። በመቀጠልም ዋናውን ትርጉም ከተረዳህ በኋላ ለሁላችንም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መርህ ማውጣትና ይህንም በተጨባጭ ከህይወት ጋር ማዛመድ ይኖርብሃል። ይህን የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥናት በምታደርግበት ወቅት እነዚህ ሶስት ደረጃዎች ሊያግዙህ ይችላሉ:- 1. በተሰጠው ምንባብ ውስጥ ለተጠቀሱት ዋና አድማጮች እግዚአብሔር መናገር የፈለገው ምንድነው? 2. ከዚህ ምንባብ ልንማረው የምንችለውና ለሁሉም ዘመንና በየትኛውም ቦታ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ልንወስደው የምንችለው መርህ ምንድነው? 3. ዛሬምመንፈስ ቅዱስ እኔን ከተማርኩትመርህ በመነሳት ምን እንዳደርግ ነው የሚፈልግብኝ? እንግዲህ እነዚህን ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ከመለስክ በቀጣይ ለወረቀት ስራህ የግልህን መረዳት ለማቅረብ ዝግጁ ነህ ማለት ነው። ለወረቀት ስራህ ይህን ቅደም ተከተል ተከትሎ መስራት ይረዳሃል፥ 1. የመረጥከው የንባብ ክፍል ዋና ጭብጥ ወይም ሃሳብ ምን እንደሆነ ለይተህ አስቀምጥ። 2. የምንባቡን ዋና ትርጉም በአጭሩ ግለጽ (ይህን በሁለት ወይም በሶስት አንቀጽ ልታስቀምጠው ትችላለህ ወይም ደግሞ በእያንዳንዱ ቁጥር አጫጭር ማጣቀሻ ወይም ማመሳከሪያ እየተጠቀምክ መሄድ ትችላለህ።)
ዓላማ
ዝርዝር መግለጫ እና አወቃቀር
/ 1 1
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
3. ይህ የምንባብ ክፍል ሊሰጠን የሚችሉ ከአንድ እስከ ሶስት የሚደርሱ የክርስቲያን ሚሽን መርሆዎችን ዘርዝር። 4. ከመርሆዎቹ ውስጥ አንዱ፣ የተወሰኑት ወይም በጠቅላላው ከሚከተሉት ነጥቦች ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ አሳይ፥ ሀ. ከአንተ የግል መንፈሳዊ ህይወት እና ከጌታ ጋር ካለህ ጉዞ ጋር ሐ. ባለህበት ማህበረሰብም ሆነ በጠቅላላው ህብረተሰብ ውስጥ ከሚንጸባረቁ ሁኔታዎችና ችግሮች ጋር የዚህን ትምህርት (ሞጁል) መጽሐፍ እና ማጣቀሻዎችን እንደ መመሪያና እንደ መርጃ ለመጠቀም ነጻነት ይኑርህ፤ ይህን በምታደርግበት ወቅት ግን የሌላን ሰው ምልከታ ከተዋስክ ወይም በዛ ምልከታ ላይ የራስህን ከመሰረትክ ለባለሃሳቡ ዕውቅና መስጠትን መዘንጋት የለብህም። ለዚህም የጽሁፍ ውስጥ ማጣቀሻዎችን፣ የግርጌ ማስታወሻዎችን፣ ወይም የመጨረሻ ማስታወሻዎችን ተጠቀም። የተጠቀምከው የማስታወሻ ዘዴ ተቀባይነት የሚኖረው 1) በጠቅላላው የጽሁፍ ስራህ ውስጥ ወጥነት ያለው ሲሆንና 2) የተጠቀምከውን የሌላን ሰው ሃሳብ በትክክል የሚያመለክት ሲሆንና ተገቢውን እውቅና ሲሰጥ ብቻ ነው ፡፡(ለተጨማሪ መረጃ ከአባሪዎች ገጽ ላይ Documenting Your Work : A guide to Help You Give Credit Where Credit is Due ተመልከት ፡፡) የትርጓሜ ጥናቱ (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክቱ) የሚከተሉትን መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆኑን አረጋግጥ:- • በአግባቡ መጻፉን(ታይፕ መደረጉን) • ከላይ ከተሰጡት ምንባቦች የአንዱ ጥናት መሆኑን • ሳይዘገይ በቀኑና በሰኣቱ ገቢ መደረጉን • ርዘመቱ 5 ገጽ መሆኑን • ከላይ የተሰጠውን መመሪያ ተከትሎ መሰራቱንና አንባቢው በቀላሉ ተከትሎ ሊረዳው የሚችል መሆኑን • ምንባቡ ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ያላቸውን ዝምድና የሚያሳይ መሆኑን እነዚህን መመሪያዎች አይተህ አትደናገጥ፤ ይህ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት ነው፤ ማድረግ የሚያስፈልግህ ምንባቡን በደንብ ማጥናት፤ ከምንባቡ ውስጥ ትርጉም መፈለግ፤ ከዚያም ቁልፍ የሆኑ መርሆዎችን ከምነባቡ ማውጣት እና መርሆዎቹንም ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ማዛመድ ናቸው፡፡ ይህ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት) የ45 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 15% ይይዛል፡፡ ስለዚህ በተቻለህ መጠን ስራህን የላቀና አስተማሪ አድርገሀ ለማቅረብ ሞክር፡፡ ለ. በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ካለህ አገልግሎት ጋር
ምዘና
1 2 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤” (ዕብራውያን 4፡12)፡፡ ሐዋሪያው ያዕቆብ ሰሚዎች ብቻ ሳይሆን አድራጊዎችም ጭምር እንድንሆን አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል፡፡ ቃሉን በተግባር ላይ እንድናውለውም ይመክረናል፡፡ ይህን ልምምድ መዘንጋት የተፈጥሮ ፊታችንን በመስታውት ውስጥ ተመልክተን ወዲያው ማንነታችንን ከመርሳት ጋር ያመሳስለዋል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያደርግ ሰው በነገር ሁሉ ይባረካል (ያዕቆብ 1፡22-25)፡፡ እኛም መሻታችን የምንቀስመውን ትምህርት በግል ህይወትህ፣ በአገልግሎትህና በቤተክርስቲያንህ ውስት ካሉ ተጨባጭ ሁኔታዎችና ፍላጎቶች ጋር በማዛመድ በተግባር ስታውለው መመልከት ነው፡፡ በመሆኑም የዚህ ትምህርት (ኮርስ) ዋና ዓላማ ከዚህ ኮርስ የተማርካቸውን ነገሮች ከሌሎች ጋር ልትከፋፈልበት የምትችልበት የሚኒስትሪ ፕሮጀክት መቅረጽ እንድትችል ነው፡፡ የዚህን ጥናት መመዘኛዎች ለማሟላት ብዙ አማራጮች አሉህ፡፡ ከሰንበት ትምህርት ቤት የወጣቶች ወይም አዋቂዎች የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ወይም ማንኛውም አገልግሎት ዘርፍ ላይ ተመስርተህ አጠር ያለ ጥናት ማካሄድ ትችላለህ፡፡ እዚህ ጋር የግድ ማድረግ የሚኖርብህ ነገር ቢኖር ከነበረህ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የተማርካቸውን ነጥቦች ከአድማጭህ ጋር መወያየት ነው፡፡ (በእርግጥ የምታካፍላቸውን ነጥቦች ከትርጓሜ ጥናትህም መውሰድ ትችላለህ፡፡) በእያንዳንዱ የፕሮጀክት ስራህ ነጻነትህን ተጠቅመህ ሳቢና ግልፅ ለማድረግ ሞክር፡፡ በዚህ ኮርስ መጀመሪያ ሀሳብህን የምታካፍልበትን ሁኔታ (አውድ) በመወሰን ለመምህርህ ማሳወቅ ይኖርብሃል፡፡ ለዚህም ፕሮጀክትህ ይህን ዝርዝርና ቅደም ተከተል በመጠቀም ሊዘጋጅ ይችላል፡፡
ዓላማ
እቅድ እና ማጠቃለያ
1. ሙሉ ስም 2. የት እና ከማን ጋር የመከፋፈል ጊዜ እንደነበረህ 3. ስለነበራቹ ጊዜ ምን እንደተሰማህና ስለነሱ ምላሽ አጠር ያለ ማብራሪያ 4. ከነበራቹ ጊዜ ስለተማርከው ነገር
ምዘና
ይህ የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የ30 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 10% ይይዛል፡፡ ስለዚህ ሃሳብህን በልበ ሙሉነት ማካፈልህንና ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ማቅረብህን እርግጠኛ መሆን ይኖርብሃል፡፡
/ 1 3
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሚፈጥረው ቃል
ት ም ህ ር ት 1
ገጽ 161
1
የትምህርቱ አላማ
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን !
የዚህን ትምህርት (ሞጁል) መጽሐፍ ካነበብክ፥ ካጠናህ፥ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል እና የጌታ ሕያውና ዘላለማዊ ቃል የጽሑፍ መዝገብ ናቸው የሚለውን ሃሳብ መሞገት ትችላለህ። • የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር አምላከ ሥላሴ ለእግዚአብሔር ቃል እውነትነት ዋስትና እንደሚሰጥ፣ ይህም ፍጹም እምነት የሚጣልበት መሆኑን ከቅዱሳት መጻሕፍት ማሳየት ትችላለህ። በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት በእግዚአብሔር ፈጣሪ እና ሕይወት ሰጪ ቃል አማካኝነት ነው። • ጌታ አምላክ ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እንዴት እንደሚገልጥ በተለይም ሁለተኛው የሥላሴ አካል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ራሱን በገለጠበት፣ ዓለምን በመቤዠት እና በጽድቅ አገዛዙ ሥር ያለውን ጽንፈ ዓለም እንዴት እንደሚመልስ ለመግለጽ ትችላለህ። • ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር የእግዚአብሔር ቃል፣ በእግዚአብሔር ሕይወት ውስጥ እንዳለ፣ መንፈስ ቅዱስ በሚያምኑት ውስጥ አዲስ ሕይወት የሚፈጥርበት መንገድ መሆኑን ማስረዳት ትችላለህ። • በዚህ በተተከለው የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ መቀጠል እና መቀበል እንዴት እውነተኛ የደቀመዝሙርነት ምልክት እና ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቤተሰብ የመሆን ምልክት እንደሆነ መግለጽ ትችላለህ። እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ቃል በቃል ኪዳኑ ማኅበረሰብ ውስጥ አብረን እንቀበላለን። • ቃሉ የፍጥረተ ዓለሙን የመጨረሻ ዓላማ የሆነውን የኃያሉን አምላክ መክበር እንዴት እንደሚገልጥ ማሳየት ትችላለህ። • የእግዚአብሔርን ቃል የመፍጠር ኃይል የሚናገረውን ምንባብ በማንበብ አሰላስለው። የሕያው የእግዚአብሔር ቃል መሻት መዝሙር 19፡7-11ን አንብብ። ዘመናችን የሚታወቅበት ነገር ከኖረ ያ የስሜታዊነት/የፍቅር ዘመን ነው ማለት ነው። ሰዎች ነገሮችን ለማግኘት፣ ተድላን ለመለማመድ፣ ቦታ ለማግኘት እና ግባቸውን ለማሳካት ራሳቸውን ይሰጣሉ፣ አንዳንዴም ለሚመኙት ነገር ትልቅ መስዋዕትነት ይከፍላሉ። ምናልባትም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ውስጥ በጣም አሳዛኙ ነገር ውሎ አድሮ ምንም
ገጽ 161
2
1
ጥሞና
ገጽ 161
3
1 4 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ፋይዳ ለሌላቸው ነገሮች ራሳቸውን አሳልፈው መስጠታቸው ነው። የሚኖሩትም በመቶ ዓመታት ውስጥ ለማይኖሩ ወይም ምንም ለማይጠቅሙ ጊዜያዊ ተድላዎች፣ ቁሳዊ ንብረቶች እና ግላዊ ስኬቶች ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ በአግባቡ ለመኖር ትልቅ ፍቅር ብቻ ሳይሆን ፍላጎቶቻችንን እና መሻቶቻችንን ቀጣይነት ወዳላቸውና አስፈላጊ ወደሆኑ ነገሮች መምራት ይኖርብናል። በእግዚአብሔር ቃል መሰረት በእርግጥ አስፈላጊ ነገሮች በጣም ጥቂት ነገሮች ናቸው፤ ስለዚህ ሊፈለጉ የሚገባቸው ጥቂት ነገሮች ብቻ ናቸው። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከተነገሩት በጣም ጠቃሚ ሀብቶች አንዱ የእግዚአብሔር ቃል ራሱ ነው። እግዚአብሔር ቅዱስ ቃሉ በሙሉ ሃይላችንና ባልተቋረጠ ጥረት የራሳችን ልናደርገው የሚገባን ውድ ሀብት እንደሆነ ገልጿል። በምድር ላይ እንደ እግዚአብሔር ቃል ጸንቶ የሚኖር ምንም ነገር የለም፤ እርሱ የሚሰጠውን ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ተስፋ እና ደስታም የሚሰጠን ምንም ነገር የለም። የእግዚአብሔር ቃል ለዓይን ብርሃንን፣ ለልብ ደስታን፣ ለመንፈስ ጥበብን፣ እና ለሰው ሕይወት ተስፋን የሚሰጥ እጅግ ታላቅ ሀብት ነው። እዚህ ላይ መዝሙረኛው የእግዚአብሔር ሕያው ቃል ስላለው አስደናቂ ተፈላጊነት በግልጽ ተናግሯል። ልጁን፣ እቅዱን እና ተስፋችንን በሚመለከት እንደ እግዚአብሔር ቃል ያለን ወይም ልንይዘው የምንችለው ምንም ነገር የለም። እርሱን በመጠበቅ እንተጋ ዘንድ ያስጠነቅቀናል፥ በቃሉም ላይ በመጣበቅ ታላቅ ብድራት አለን። ገንዘብን፣ ወይም ተድላን፣ ወይም ነፃ ጊዜን፣ ወይም ታላቅ ዕድልን በምትፈልገው ልክ የእግዚአብሔርን ቃል እየፈለግህ ነውን? በዚህ ዓለም ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ጥልቅ እውቀት ያህል ዋጋ ያለው ወይም ጠቃሚ ነገር የለም። ዛሬ የልብህ መሻት ያለው የት ነው? የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ እኛና መላው አለም የእርሱን ድንቅ ስራዎች እናስተውል ዘንድ የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥሪ በፍጥነት እንድንመልስና ለሰዎች ሁሉ የማዳኑን የምስራች እንድናውጅ ጌታ ሆይ ጸጋን ስጠን፤ እርሱም ከአንተና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚኖርና የሚነግስ አንድ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም። አሜን!
1
የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት
ገጽ 162
4
~ Martin Luther. Devotions and Prayers of Martin Luther. Trans. Andrew Kosten. Grand Rapids: Baker Book House, 1965. p 77.
/ 1 5
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ይህ ትምህርት ፈተና የለውም
ፈተና
ይህ ትምህርት የቃል ጥናት ጥቅስ የለውም
የቃል ጥናት ጥቅስ ምዘና
ይህ ትምህርት የቤት ስራ/መልመጃ የለውም
የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ
1
እውቂያ
የባለሙያ ጥያቄ ዛሬ በአጠቃላይ ህብረተሰብ ውስጥ ሙያዊም ሆነ የግል ችግር ያለባቸው አብዛኞቹ ሰዎች ችግሩን በራሳቸው ለመፍታት ወይም “አዋቂዎችን” - ሳይንቲስቶችን፣ ዶክተሮችን፣ አማካሪዎችን ወይም ሌሎችን ማማከሩ የተለመደ ነው። በአሁኑ ወቅት የእግዚአብሔር ቃል የሰዎችን ችግር ለመፍታት ምን ቦታ አለው? በአሁኑ ወቅት በኅብረተሰቡ ውስጥ ለእግዚአብሔር ቃል ትምህርት አክብሮት እንዳለህ የምታየው ወይም ማየት የሚሳንህ በምን መንገዶች ነው? ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነትን በሚመለከት በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንህ አገልግሎት በወጣቶች ቡድን ውስጥ አንድ ወሳኝ ጉዳይ እንደሚነሳ አስብ። ብዙዎቹ ህጻናት በአካባቢያቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ የተለመደ እና የሚጠበቅ መሆኑን እና በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን እና የመፀነስ አደጋን እስከተከላከሉ ድረስ ምንም ችግር እንደሌለው እየተማሩ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚነሱ ክርክሮች በወጣት ቡድናችሁ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ተማሪዎችን በመጠኑም ቢሆን እየማረኩ መጥተዋል፤ እነዚህ ተማሪዎች በዛሬው ጊዜ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ያለ አንድ ጥንታዊ መጽሐፍ ከነሱ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ እያሰቡ ነው። በሕይወታቸው የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣን ላለመቀበል ለሚታገሉት እና በኃላፊነት እና በግልጽ እስከያዝናቸው ድረስ ነገሮች ምንም አይደሉም ብለው ለሚያምኑት ልጆች ምን ትላቸዋለህ? ኢየሱስ - እሺ፥ መጽሐፍ ቅዱስ - እምቢ! ስለኢየሱስ ማንነት እና ትምህርት በጥልቀት የሚያምኑ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነትነት ላይ ችግር ያለባቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ኢየሱስ ፍቅርን፣ ትሕትናንና በጎ ፈቃድን በሰዎች መካከል አስተምሯል፥ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ብዙ ዘመናዊ ሰዎች ለማመን በሚከብዷቸው ነገሮች ስለ መላእክት፣ አጋንንት፣ እና ተአምራት በሚናገሩ ያልተለመዱ ትምህርቶች የተሞላ ነው። አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጉዳዮችን ጥያቄ ውስጥ በማስገባት የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት መቀበል የሚቻል ይመስልሃል? ለኢየሱስ “እሺ!” በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ስላሉት ብዙ ነገሮች ግን “እምቢ” ወይም “እርግጠኛ አይደለሁም”
1
ገጽ 162 5
2
3
1 6 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ማለት ይቻላል? ከኢየሱስ ጋር እውነተኛ ህብረትና እምነት እንዳለህ ለመናገር መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ሁሉ ማመን የለብህም? ለምን?
የሚፈጥረው ቃል ክፍል 1
ይዘት
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል እና የጌታ ሕያውና ዘላለማዊ ቃል የጽሑፍ መዝገብ ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር አምላከ ሥላሴ ለእግዚአብሔር ቃል እውነትነት ዋስትና ይሰጣል፤ ይህም ፍጹም እምነት የሚጣልበት ነው። በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት በእግዚአብሔር ፈጣሪ እና ሕይወት ሰጪ ቃል አማካኝነት ነው። ጌታ አምላክ ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ዓለምን በመቤዠት እና በጽድቅ አገዛዙ ሥር ያለውን ጽንፈ ዓለም እንዴት እንደሚመልስ ሁለተኛው የሥላሴ አካል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ራሱን ገልጧል። የዚህ “የሚፈጥረው ቃል” የተሰኘ የመጀመሪያ ክፍል አላማችን የትምህርቱን አንድምታዎች እንድታይና እንድትረዳ ለማስቻል ነው። ይህም:- • ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል እና የጌታ ሕያውና ዘላለማዊ ቃል የጽሑፍ መዝገብ መሆናቸውን። የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር አምላከ ሥላሴ ለእግዚአብሔር ቃል እውነትነት ዋስትና እንደሚሰጥና ይህም ፍጹም እምነት የሚጣልበት መሆኑን፥ • በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት በእግዚአብሔር ፈጣሪ እና ሕይወት ሰጪ ቃል አማካኝነት መሆኑን • ጌታ አምላክ ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ዓለምን በመቤዠት እና በጽድቅ አገዛዙ ሥር ያለውን ጽንፈ ዓለም እንዴት እንደሚመልስና ሁለተኛው የሥላሴ አካል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ራሱን እንዴት እንደሚገልጥ ትረዳ ዘንድ ነው።
የክፍል 1 ማጠቃለያ
1
I. ቅዱሳት መጻሕፍት (መጽሐፍ ቅዱስ) ከእስትንፋሱ ወጥቶ ከማንነቱና ከሥራው ጋር የተቆራኘ የሕያው እግዚአብሔር ቃል ነው።
የቪዲዮ ክፍል 1 መግለጫ
ሀ. ቅዱሳት መጻሕፍት (መጽሐፍ ቅዱስ) ሕያው እና ዘላለማዊ ቃል ነው።
1. የእግዚአብሔር ቃል ዘላለማዊ ነው፣ የእግዚአብሔርን የፍፁም እውነተኝነት እና ስልጣን ባህሪም ይዟል። 1ጴጥ. 1፡23-25።
/ 1 7
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
2. ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው።
ሀ. 2 ጢሞ. 3፡16-17
ለ. እግዚአብሔር የራሱን ፈጣሪ ሕይወት በቃሉ ውስጥ አኑሯል።
3. እግዚአብሔር ቅዱሳን መጻሕፍትን በእርሱ መንፈስ የቃል በቃል መሪነት እንዲጽፉ እንደ ፈቀደ ማመን አይጠበቅብንም። ይልቁንም መንፈስ ቅዱስ የጸሐፊዎቹን የቃላት አቅም፣ ልምዶች እና ችሎታዎች እሱ ባሰበው ልክ እንደ ተጠቀመ እናምናለን ስለዚህም በጽሑፎቻቸው ያቀረቡት ሁሉ የራሱ ፍጥረት ነው ማለት ነው። መንፈስ ቅዱስ ጸሐፊዎቹን ያነሳሳቸው እርሱ የሰነዶቹ ጸሐፊ ተብሎ ሊጠራ በሚችልበት መንገድ ነው። በዚህ መንገድ ነው ቤተክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን ለእምነት እና ለኑሮ እንደ ባለሥልጣን እና እንደ መመሪያ አድርጋ የወሰደችው።
1
ሀ. 2 ጴጥ. 1.19-21
ለ. ሰዎች ራሱ መንፈስ ቅዱስ እንደነዳቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ተናግረዋል።
ለ. ቅዱሳት መጻሕፍት (መጽሐፍ ቅዱስ) በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ በመሆኑ ከእርሱ ከወጣ እንዲሁ በከንቱ ወደ እርሱ አይመለስም። በሁሉም መንገድ፣ የእግዚአብሔር ቃል ፍፁም ታማኝ እና ፍፁም ስልጣን ያለው፤ ልንታመነውና ልናጠናው የሚገባ ሆኖ ይታያል።
1. ኢሳ. 55.8-11
ሀ. የእግዚአብሔር መንገድ ከመንገዳችን እጅግ የራቀ ነው፣ ይህም ማለት ፍፁም ከፍለጋችን ወይም ግኝታችን በላይ ነው።
ለ. የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔር እንዲሰራ በፈለገውና በሾመው ነገር ሁሉ ላይ ይሰራል።
1 8 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
2. እግዚአብሔር የመለኮታዊ ቃሉን ፍጹምነት አረጋግጧል፣ ኢሳ. 44፡26-28።
ሀ. እግዚአብሔር የባሪያውን ቃል እንደሚያጸናና የመልእክተኞቹንም ምክር እንደሚፈጽም ያውጃል። ቃሉ እውነት ነው።
ለ. እግዚአብሔር በፍጹም እርግጠኝነት እና ታማኝነት ቃሉን ያጸናል። ኢየሱስ በዮሐንስ 10፡35 ላይ “መጽሐፉ ሊሻር አይቻልም” ብሏል።
1
ሐ. ከፍጹም አስተማማኝነቱ የተነሳ የእግዚአብሔር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሁሉም ቦታ የተከበረና የተመሰገነ ነው።
1. ስለ ፍፁም ዘላለማዊነቱ የተመሰገነ ነው፣ ማቴ. 5.18.
2. እግዚአብሔር በቃሉ ከፍ ከፍ በማለቱ የተመሰገነ ነው፣ ኢሳ. 42.21.
3. ከቅዱስ ስሙ ጋር የተመሰገነ ነው መዝ. 138.1-2.
4. ለዘላቂው እውነታው የተመሰገነ ነው፣ ማቴ. 24.35.
5. የእግዚአብሔር ቃል ፍፁምነት፣ መገለጥ፣ ተአማኒነት እና ታማኝነት እውቅና ተሰጥቶታል፤ መዝሙር 19 እና 119።
ገጽ 162
6
II. በቃሉ የፍጥረት ኃይል አማካኝነት የሚሰራው ሁሉን ቻዩ አምላክ ሁሉንም ነገር በአጽናፈ አለም ውስጥ ፈጥሯል።
ሀ. የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሰማይና የምድር ፈጣሪ ነው፥ አጽናፈ ሰማይም በራሱ አልጸናም ወይም በራሱ አይደገፍም።
1. ዘፍ 1.1
/ 1 9
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
2. ምሳሌ. 16.4
3. ዕብ. 1.10
ለ. ሁለተኛ፣ እግዚአብሔር አጽናፈ ሰማይን “ኤክስ ኒሂሎ”ን ከምንም ነገር ፈጠረ።
1. ዕብ. 11.3
1
2. መዝ. 33.6
3. መዝ. 33፡8-9
4. 2 ጴጥ. 3.5
ሐ. እግዚአብሔር ዓለማትን የፈጠረው በሎጎስ፣ በእግዚአብሔር ቃል ነው፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
1. ዮሐንስ 1.1-3
2. ቆላ.1.16
3. የእግዚአብሔር ቃል በእግዚአብሔር የአጽናፈ ዓለም የፍጥረት ሥራ ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ አለው - የእግዚአብሔር ቃል የሚፈጥር ቃል ነው!
ገጽ 162
7
2 0 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
III. በሁሉን ቻይ አምላክ እና በቃሉ መካከል እጅግ የጠበቀ ግንኙነት አለ፤ ይህም ማለትም፣ “ቃሉ” ነው።
ሀ. እግዚአብሔር ራሱን በአጠቃላይ መገለጥ አማካኝነት ይገልጣል። አጠቃላይ መገለጥ እግዚአብሔር ራሱን በማንኛውም ጊዜ ለሁሉም ሰው የሚገልጥበት መገለጥ ነው።
1. እግዚአብሔር በአጠቃላይ በሥጋዊ ሥርዓት፣ በፍጥረትና በተፈጥሮ ክብር ራሱን ገልጧል፣ መዝ. 19.1.
1
2. እግዚአብሔር በአጠቃላይ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ራሱን ገልጧል - በእስራኤል ሕዝብ በኩል።
3. እግዚአብሔር ራሱን በአጠቃላይ በሰው ተፈጥሮ ይገልጣል፣ መዝሙር 8
ሀ. ምክንያት
ለ. ህሊና
ሐ. ሥነ ምግባራዊ እና መንፈሳዊ ባህሪያት
ለ. እግዚአብሔርም በልዩ መገለጥም ራሱን ይገልጣል። ልዩ መገለጥ ስንል እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰነ ጊዜና ቦታ ለራሱ ዓላማ መግለጡን ማለታችን ነው።
1. እግዚአብሔር ራሱን በልዩ መገለጥ በታሪካዊ ክስተቶች ውስጥ ገልጧል።
ሀ. የአባቶች ሕይወት
ለ. የዘፀአት ክስተት
/ 2 1
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ሐ. የቤተ መቅደሱ ግንባታ
2. እግዚአብሔር በልዩ መገለጥ በመለኮታዊ ንግግር ውስጥ ራሱን ይገልጣል።
ሀ. “የእግዚአብሔር ቃል” በድምፅ፣ በህልም ወይም በራእይ በመስጠት
ለ. ይህ ሁኔታ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በ“ፕሮፖዚሽን” ቃል አማካኝነት ፍጽምናን አግኝቷል።
1
3. እግዚአብሔር ራሱን በልዩ መገለጥ የገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ አካልና ሥራ ቃሉን በሥጋ በመግለጥ ነው።
ሀ. እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ከቃሉ ጋር በቀጥታ ተገልጧል፤ ዮሐንስ 1፡1-2።
ለ. ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ነው፣ ዮሐ 1፡14. (1) እግዚአብሔር በአካልና በጊዜ ራሱን በግልጽ ገልጧል።
(2) ለሰው ልጆች ሁሉ ልዩ የሆነ መገለጥ
ሐ. ቃልም ሥጋ በመሆን የገለጠውን ያህል ማንኛውም ሰው ወይም ነገር የእግዚአብሔርን ክብር ሊያውጅ አይችልም። (1) ዮሐንስ 1፡18
(2) 1ኛ ዮሐንስ 1፡1-3
መ. የኢየሱስ ስም በግልጽ “የእግዚአብሔር ቃል” ተብሎ ተጠርቷል፣ ራእ. 19.13
2 2 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ሐ. ሁለት ጉልህ የሆኑ የእግዚአብሔር ቃል ዓይነቶች፡ ፕሮፖዚሽናል ቃል እና ግላዊ ቃል
1. አይነት 1፡ ፕሮፖዚሽናል የእግዚአብሔር ቃል - በመንፈስ መሪነት የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል
ሀ. በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል፣ የብሉይ ኪዳን የዕብራይስጥ ቅዱሳት መጻሕፍት እና የአዲስ ኪዳን የክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍት
1
ለ. ከ1500 ዓመታት በላይ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ የመጻሕፍት ስብስብ፣ 40 ጸሐፊያን
2. አይነት 2፡ “የግል” የሆነ የእግዚአብሔር ቃል - ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ
ሀ. ኢየሱስ ለእግዚአብሔር አካል የመጨረሻ ምስክርነት የሚሰጥ የግል የመገለጥ ቃል ነው። ማቴ. 11.27.
ለ. ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር የሚመልሰን የግል የቤዛነታችን ቃል ነው፣ ዮሐንስ 14፡6.
ማጠቃለያ
» ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል እና የጌታ ሕያውና ዘላለማዊ ቃል የጽሑፍ መዝገብ ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር አምላከ ሥላሴ ለእግዚአብሔር ቃል እውነትነት ዋስትና ይሰጣል ይህም ፍጹም እምነት የሚጣልበት ነው። » በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት በእግዚአብሔር ፈጣሪ እና ሕይወት ሰጪ ቃል አማካኝነት ነው።
» ጌታ አምላክ ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ራሱን ይገልጣል።
/ 2 3
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የእግዚአብሔርን ቃል የመፍጠር ኃይልን በሚመለከት ቪዲዮው ያነሳቸውን እነዚህን እና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመመለስ ያለህን ያህል ጊዜ ውሰድ። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፍ! 1. ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል መሆናቸውን የሚናገሩት በምን መንገድ ነው? ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር እስትንፋስ የተጻፉ ናቸው ማለት ምን ማለት ነው? 2. የእግዚአብሔር ቃል “ህያው ሆኖ ለዘላለም ይኖራል” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ትርጉም ምንድን ነው? 3. እግዚአብሔር በጸሐፊዎቹ ብቻ ሳይወስን ወይም በህልም ሳያሳያቸው እና አእምሮአቸውን ሳይቆጣጠር እንዴት የእግዚአብሔርን ቃል አነሳስቶ ሊሆን ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ ደራሲዎቹ “በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው” ሲል ምን ማለቱ ነው? 4. አንድ አማኝ ቅዱሳት መጻሕፍት ፍጹም እምነት የሚጣልባቸውና እውነተኛ መሆናቸውን ማወቅ የሚችለው እንዴት ነው? 5. የእግዚአብሔር ቃል በቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የተከበረና የተመሰገነ ነው የሚለው አንድምታው ምንድን ነው? 6. በአጽናፈ ዓለም አፈጣጠር እና በእግዚአብሔር ቃል መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? “ኤክስ ኒሂሎ” የሚለው የላቲን ሐረግ ትርጉም ምንድን ነው እና ይህ ጽንሰ-ሐሳብ ከእግዚአብሔር የፍጥረት ሃሳብ ጋር እንዴት ይዛመዳል? 7. ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ እግዚአብሔር ፍጥረት አጽናፈ አለሙ እና ሎጎስ ወይም የእግዚአብሔር ቃል (ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ) ግንኙነት ምን ይላሉ? 8. “አጠቃላይ መገለጥ” ማለት ምን ማለት ነው? እግዚአብሔር በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሁሉ ራሱን የገለጠባቸው ልዩ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? 9. “ልዩ መገለጥ?” የሚለው ሐረግ ትርጉም ምንድን ነው? እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰነ ጊዜና ቦታ የገለጠባቸው ልዩ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? 10. በ“ፕሮፖዚሽናል” እና “በግል” የእግዚአብሔር ቃል መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? እንዴት ይዛመዳሉ? አንዱ ከሌላው ይቀድማል (ማለትም የበለጠ አስፈላጊ ነው)? አብራራ።
መሸጋገሪያ 1
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
ገጽ 163
8
1
2 4 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሚፈጥረው ቃል ክፍል 2
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
የእግዚአብሔር ቃል መንፈስ ቅዱስ በሚያምኑት ውስጥ አዲስ ሕይወት የሚፈጥርበት መንገድ ነው። ስለዚህ፣ ይህንን የተተከለው የእግዚአብሔር ቃል መቀጠል እና መቀበል ትክክለኛው የደቀመዝሙርነት እና ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቤተሰብ የመሆን ምልክት ነው። እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ቃል በቃል ኪዳኑ ማኅበረሰብ ውስጥ አብረን እንቀበላለን። በመጨረሻም፣ በቃሉ ታማኝነት አማካኝነት የፍጥረተ-ዓለሙ የመጨረሻ አላማ ብቻውን ሊነግረን ይችላል፣ እርሱም የኃያሉ አምላክ ክብር ነው። የዚህ የሚፈጥረው ቃል ሁለተኛ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እንድታዩ ለማስቻል ነው፡- • የእግዚአብሔር ቃል በእግዚአብሔር ሕይወትውስጥ የተካተተ ነው፣ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቃል ሕይወት ሰጪ ኃይል ውጭ ምንም ዓይነት መንፈሳዊነት ወይም እውነተኛ እምነት የለም። እግዚአብሔር በአማኞች ዘንድ አዲስ ሕይወትን የሚፈጥረው በቃሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ ነው። • እውነተኛው የደቀመዝሙርነት ምልክት የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መንፈስና እውነት መቀበልና መቀጠል ነው። መንፈሳዊ እድገት በቤተክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት እና ከመታዘዝ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። • ከማይሻረው ሥልጣኑ የተነሳ፣ ለተፈጠረው ጽንፈ ዓለም የመጨረሻውን ዓላማ ሊሰጠን የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው፣ እርሱም በሁሉም ነገር የእግዚአብሔርን ክብር እና ሞገስ ማምጣት ነው።
የክፍል 2 ማጠቃለያ
1
I. የእግዚአብሔር ቃል በራሱ በእግዚአብሔር ሕይወት የተሞላ ነው፥ ስለዚህም በሚያምኑት ሁሉ ውስጥ አዲስ ሕይወትን ይፈጥራል።
ቪዲዮ ክፍል 2 መግለጫ
ሀ. ቃሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ላይ ላለ እምነት ምላሽ በመስጠት መንፈሳዊ ሕይወትን ይፈጥራል።
1. የእግዚአብሔር ቃል በአማኙ ውስጥ አዲስ መንፈሳዊ ሕይወትን ለመፍጠር ፍጹም ተቀዳሚ ነው።
ሀ. ያዕቆብ 1፡18
/ 2 5
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ለ. ያዕቆብ 1፡21
2. የእግዚአብሔር ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን አዲስ ሕይወትን በእኛ የሚወልድ መሳሪያ ነው። 1ጴጥ. 1፡22-23።
3. ስለ ኢየሱስና ስለ መንግሥቱ የሚናገረው ወንጌል ከሰው የተገኘ ሳይሆን “ራሱ የእግዚአብሔር ቃል ነው” 1 ተሰ. 2.13.
1
ለ. መንፈሳዊ ሕይወት የተፈጠረው በእግዚአብሔር ሕያው ቃል ነው፥ የምንኖረውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው እያንዳንዱ ቃል ነው።
1. ይህን አመለካከት የያዝነው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥልጣን ላይ ነው።
ሀ. የኢየሱስ ፈተና
ለ. የዘዳግም ጥቅስ፡- የእግዚአብሔር ቃል ነጠላ ሚና፣ ዘዳ. 8.3፣ ዝከ. ማቴ. 4.4
2. የእግዚአብሔር ቃል አስደናቂ መንፈሳዊ ኃይል እና ነፍስን በመንፈስ የማብራት ኃይል አለው፣ መዝ. 19፡7-11።
3. የትኛውም የእግዚአብሔር ቃል አካል እንደማይጠቅም ወይም እንደ ከንቱ ሊቆጠር አይገባም። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ንግግርና ሃሳብ ሁሉ ይፈጸማል፥ አንዳችም አይቀርም።
4. እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን የተስፋ ቃል ለማፍረስ በፍጹም አይፈቅድም፤ ቅዱሳት መጻሕፍትም የሚታመኑ ናቸው ምክንያቱም እግዚአብሔር ራሱ ታማኝ ነው።
ሀ. 2ኛ ነገ 13፡23
2 6 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ለ. 1ኛ ዜና. 16፡14-17
ሐ. እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለአማኞች በመላክ ለቃሉ መረዳትን ይሰጣል፣ 1ኛ ቆሮ. 2.9-16.
1. የማያምን (ማለትም፣ “ፍጥረታዊው ሰው”) መንፈስ ቅዱስ የለውም፥ ስለሆነም የቃሉን መልእክት ወይም ትምህርት ሊረዳ አይችልም።
1
2. መንፈሳዊ ሰው፣ (ማለትም፣ መንፈስ ቅዱስ ያለው እና የሚመራው)፣ የእግዚአብሔር ቃል የሚለውን ብቻ ሳይሆን ሊረዱት ያልቻሉትን ሊያገኝ ካለው ፍርድ ያመልጣል።
3. ቃሉን ያነሳሳው ያው ራሱ መንፈስ ነው ትርጓሜንም የሚሰጠው 2ጴጥ. 1.21.
II. እውነተኛው የደቀመዝሙርነት ምልክት በእግዚአብሔር ቃል እየተመገቡ መቀጠል እና መኖር ነው።
ሀ. የእውነተኛ ደቀመዝሙርነት ምልክት በክርስቶስ ቃል ውስጥ መቀጠል እና መኖር ነው።
1. ዮሃንስ 8፡31-32
2. “መኖር” ማለት መገኘት፣ ቤት መሥራት፣ ማደር፣ መዝ. 1.1-3.
3. የመኖር ስሜት ከብሉይ ኪዳን የማሰላሰል አስተሳሰብ ጋር ተመሳሳይ ነው።
ሀ. መዝ. 1.1-3
ለ. ኢያሱ 1.8
/ 2 7
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ለ. መንፈሳዊ እድገት እና ብስለት ፈጣሪ እና ህይወት ሰጪ በሆነው የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ባለው እውነት በመመገብ የተመሰረተ ነው።
1. እኛ አማኞች በእርሱ ተመግበን ማደግ እንድንችል ንጹሕ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ወተት መመኘት አለብን፣ 1ጴጥ. 2.2.
2. ጳውሎስ የኤፌሶን ሽማግሌዎችን ለእግዚአብሔር እና ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቷቸቸዋል “አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።” ሐዋርያት 20፥32።
1
3. የቆላስይስ ሰዎች የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ያድርባቸው ዘንድ ተመክረዋል፣ ቆላ. 3፡16.
4. ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የእውነትን ቃል በቅንነት በመናገር ራሱን በእግዚአብሔር ዘንድ የማያሳፍር ሠራተኛ አድርጎ ለማቅረብ ቃሉን እንዲያጠና ሥልጣንን ሰጥቶታል፣ 2 ጢሞ. 2.15.
5. በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ለመኖር ብዙ መንገዶች አሉ።
ሀ. ልናነበው ይገባል። ራዕይ 1፡3 የእግዚአብሔርን ቃል ለሚያጠኑ የበረከትን የተስፋ ቃል ይሰጣል።
ለ. ልናሰላስለው ይገባል። በመዝሙር 19፡11 ዳዊት በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት እንዳይሠራ በልቡ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚሰውር ተናግሯል።
ሐ. ልናሰላስለው ይገባል። መዝሙረ ዳዊት 1፡3 እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በቀንና በሌሊት ያሰላስላል፣ ያንጎራጉራል እና ይበላል ይላል።
2 8 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
መ. ልናጠናው ይገባል። የቤርያ ሰዎች በሐዋርያት ሥራ 17.11 ከተሰሎንቄ ሰዎች ይልቅ “የላቁ ጠቢባን” ተሰኝተዋል ምክንያቱም የሐዋርያው ጳውሎስን ቃል መስማት ብቻ ሳይሆን የጳውሎስን ወንጌል ለማረጋገጥ በየቀኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑ ነበር።
ሠ. በቤተክርስቲያን ሲሰበክ እና ትምህርት ሲሰጥ መስማት ይኖርብናል። ሮሜ 10፡ 17 “እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነውና” እንደሚል ቃሉን እንስማ እንጂ ትንቢትን መናቅ የለብንም።
1
ረ. በሁሉም ሕይወታችን እና ንግግራችን ውስጥ ልናካትተው ይገባል። የሚፈጥረው ቃል በሼማ (shema) ቃል እንደተነገረው በሕይወታችን ውስጥ ዋነኛው ኃይል መሆን አለበት፣ ዘዳ. 6፡4-9።
ሐ. ይህ የእግዚአብሔር ፈጣሪ ቃል በክርስቲያን ማኅበረሰብ አውድ ውስጥ ይሰማ እና ይከበር ዘንድ ይገባል።
1. ትንቢትን አትናቁ፥ መንፈስም አታጥፉ፣ 1ኛ ተሰ. 5፡19-22።
2. ቃልን መግለጥ በጉባኤ መካከል ይመጣል፣ 1ኛ ቆሮ. 14.26.
3. እግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶችን በመንፈስ ቅዱስ ታጥቀው የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምሩ ዘንድ ስጦታ አድርጎ ለቤተክርስቲያን ሰጥቷል፣ ኤፌ. 4፡11-13።
III. ቃሉ የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ዓላማ ለፍጥረተ ዓለሙ ይገልጣል፡- ሁሉም ነገር ለጌታ ክብርን እና ሞገስን ያመጣ ዘንድ።
ሀ. ከመለኮታዊው ታሪክ ማዕከላት ውስጥ አንዱ ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት ለራሱ እና ለክቡር ስሙ ክብርን እና ምስጋናን ለማምጣት ነው የሚለው ነው።
1. ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት ለእግዚአብሔር ዓላማ ነው፣ ምሳ. 16.4.
/ 2 9
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
2. በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ፣ የሚታዩትም ሆነ የማይታዩት፣ ሁሉም መላእክት፣ ፍጥረታት፣ ሰው ወይም እንስሳት፣ ያሉት ሁሉ በእግዚአብሔርና ለክብሩ የተፈጠሩ ናቸው።
ሀ. ቆላ.1.16
ለ. ራእይ 4.11
1
ሐ. መዝ. 150.6
3. የእስራኤል ሕዝብ፣ የእግዚአብሔር የተመረጡ ሕዝቦች፣ የተመረጡት ለመጨረሻው ክብሩ ነው።
ሀ. ኢሳ. 43.7
ለ. ኢሳ. 43.21
ሐ. ኢሳ. 43.25; 60.1፣ 3፣ 21
4. እግዚአብሔር የሰውን ልጅ የሚያድነው ለራሱ ክብርን ያመጣ ዘንድ ነው፣ ሮሜ. 9.23; ኤፌ. 2.7.
5. ሁሉም አገልግሎት እና የእግዚአብሔር ሰዎች የሚያከናውኗቸው ተግባራት ሁሉ ለእግዚአብሔር የመጨረሻ ክብር መዋል አለባቸው፣ 1 ቆሮ. 10.31; ዮሐንስ 15፡8; ማቴ. 5.16.
6. የአማኝ ዋናው ዓላማ፡ በክርስቶስ ያለውን የእግዚአብሔርን ክብር በግል መመስከር እና በመገለጡም ከእርሱ ጋር አብሮ መክበር።
3 0 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ሀ. የዮሐንስ ወንጌል 17፡22
በጥቅሉ ሲታይ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በርዕሰ ጉዳዩ እና በዓላማው ከየትኛውም ዓለም ካለ መጽሐፍ ይለያል። እርሱም [የሰው ልጅን] እና የመዳን እድሉን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት ያለውን ባህሪ እና ተግባር ያንፀባርቃል፥ በመሆኑም ለራሱ ለእግዚአብሔር ወደር የሌለውን ክብር ይሰጣል። ፈጣሪውን ለፍጡሩ የሚገልጥ እና ሁሉም (የሰው ልጅ) ከነጉድለቱ ከዘላለማዊው አምላክ ጋር በዘለአለማዊ ህብረት የሚታረቁበትን እቅድ የሚገልፅ መጽሐፍ ነው። ~ Lewis Sperry Chafer. Major Bible Themes. Grand Rapids: Zondervan, 1974. p. 29.
ለ. ቆላ.3.4
ለ. ለእግዚአብሔር የፍጥረት ቃል ስንገዛ እርሱን የማክበር ዓላማን እንፈጽም ዘንድ ብርታትና መመሪያ ይሰጠናል።
1. ውስጣዊ ስሜታችንን እና ፍላጎታችንን ይገልጣል፣ ዕብ. 4.12.
1
2. የሚንቀጠቀጡ ልቦቻችንን ከእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዓላማ ጋር ያስማማል።
ሀ. ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ልባችን ደስታ እና ሐሤት፣ ኤር. 15.16
ለ. ለኃይሉ ስንገዛ የእግዚአብሔር ቃል በልባችን ውስጥ በሃይል ይንቀሳቀሳል፣ ኤር. 20.9.
3. በአእምሯችን መታደስ ወደ ፍጹም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይለውጠናል፣ ሮሜ. 12፡ 1-2።
ማጠቃለያ
» የእግዚአብሔር ቃል በራሱ በእግዚአብሔር ሕይወት የተሞላ ነው፥ ስለዚህም በሚያምኑት ሁሉ ውስጥ አዲስ ሕይወትን ይፈጥራል።
» የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት በዚህ በተተከለው ቃል ውስጥ ይኖራሉ።
» መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረን የፍጥረት ጽንፈ ዓለም የመጨረሻ ዓላማ ሁሉን ቻይ የሆነውን እግዚአብሔርን ማክበር እንደሆነ ነው። » ቅዱሳት መጻሕፍት፣ የሚፈጥረው ቃል፣ በእግዚአብሔር አገዛዝ ሥር ስንኖር እግዚአብሔርን እንድናከብር በመንፈስ ያስችሉናል።
/ 3 1
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሚከተሉት ጥያቄዎች የተነደፉት በሁለተኛው የቪዲዮ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን ሕይወት ሰጪ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችን ውስጥ ስላሉት ባሕርያት ላይ ያተኮረውን ሐሳብ እንድትከልስ ለመርዳት ነው። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፍ! 1. መጽሐፍ ቅዱስ በክርስቶስ ለሚያምን ሰው አዲስ ሕይወት በመስጠት ረገድ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚጫወቱትን ሚና እንዴት ይገልጸዋል? አዲስ ውልደትን ለመፍጠር እምነት ከቃሉ ጋር ምን ሚና ይጫወታል? 2. የኢየሱስ ፈተና የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችን ያለውን ኃይል የሚያስተምረን በምን መንገድ ነው? ኢየሱስ በምድረ በዳ በዲያብሎስ ሽንገላ በተፈተነ ጊዜ ምን አይነት እውነት ጠቅሷል? 3. መንፈሳዊ ሰው የቅዱሳን ጽሑፎችን ትርጉም እንዲገነዘብ መንፈስ ቅዱስ ምን ሚና ይጫወታል? ፍጥረታዊው ሰውስ - ሊረዳው ይችላልን? ለምን? 4. የኢየሱስ ክርስቶስ የደቀመዝሙርነት እውነተኛ ምልክት ምንድን ነው? በመንፈሳዊ እድገት እና የእግዚአብሔርን ቃል በመመገብ መካከል ያለውን ግንኙነት ግለጽ? 5. አንድ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እንዴት መኖር እንደሚችል ቅዱሳት መጻሕፍት የሚጠቁሟቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው? በቃሉ ውስጥ መኖር በክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ ከመኖር ጋር እንዴት ይገናኛል? 6. ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል እንድትረዳ እና እንድትተገብር እግዚአብሔር የሰጣት ምን አይነት ሰዎችን ነው? ክርስቲያኖች አገልግሎት እንዲሰጡ በመርዳት ረገድ ያላቸውስ ሚና ምንድን ነው? 7. በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት፣ እግዚአብሔር ለፈጠረው ጽንፈ ዓለም ያለው ዘላለማዊ ዓላማ ምንድን ነው? 8. እግዚአብሔር ለአማኞች የሰጠው የመጨረሻው የላቀ ዓላማ ምንድን ነው? አማኞች ይህን ዓላማ በሕይወታቸው ውስጥ ማስፈጸም የሚችሉትስ እንዴት ነው? 9. ቅዱሳት መጻሕፍት በዓለም ላይ ካሉ መጻሕፍት ሁሉ የተለዩና የላቁ የሆኑት በምን መንገድ ነው? 10. ፈጣሪ ለሆነው የእግዚአብሔር ቃል ስንገዛ በልባችንም ሆነ በሕይወታችን ውስጥ ምን እንዲፈጠር እንጠብቃለን? አብራራ።
መሸጋገሪያ 2
የተማሪው ጥያቄዎችና ምላሽ
ገጽ 163
9
1
3 2 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ግንኙነት
ይህ ትምህርት የእግዚአብሔርን ቃል የመፍጠር ሃይል አንዳንድ ወሳኝ ገፅታዎችን ያጎላል፣ በፅንፈ ዓለሙ አፈጣጠር ውስጥ እና በአማኙ ልብ ውስጥ ስለሚፈጠረው አዲስ መንፈሳዊ ህይወት ያስረዳል። በሁሉም መልኩ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በአለም እና በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ያለውን ስራ ለመረዳት የእግዚአብሔር ቃል እሳቤ ጠቃሚ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሕያው እና ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ቃል ነው። በእርሱ አነሳሽነት ተጽፏል፤ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ማንነት እና ስራው ጋር በቀጥታ የሚታወቀው በራሱ የእግዚአብሔር ህይወት ተሞልቷል። ቅዱሳት መጻሕፍት ከእግዚአብሔር ማንነትና ሥራ ጋር በጣም የተቆራኙ በመሆናቸው በሚገልጹት እና እውነት በሆኑ ነገሮች ሁሉ ላይ ሙሉ በሙሉ እምነት የሚጣልባቸው እና ስልጣን ያላቸው ናቸው። አጽናፈ ሰማይ እና በውስጡ የያዘው ሁሉም ህይወት የተፈጠረው “ኤክስ ኒሂሎ” (ማለትም ከምንም) በእግዚአብሔር ቃል ሕይወት ሰጪ ኃይል ማለትም በፍጥረት ጊዜ በተናገራቸው ቃላት ነው፤ በተጨማሪም፣ ሁሉን ቻዩ አምላክ ሕያው በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሁሉንም ነገር ፈጥሯል (ዮሐንስ 1.1-3፤ ቆላ. 1.16)። ቅዱሳት መጻሕፍት በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉት “ፕሮፖዚሽናል” የእግዚአብሔር ቃል ሲሆን ሁለቱንም ብሉይ ኪዳን (ማለትም፣ የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች) እና አዲስ ኪዳንን (ማለትም፣ የክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍት) ያካትታል። እግዚአብሔር ራሱን በገለጠበት፣ ዓለምን በመቤዠት እና በጽድቅ አገዛዙ ሥር ያለውን ጽንፈ ዓለም በሚመልስበት በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ራሱን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሙሉ በሙሉ ገልጿል። የእግዚአብሔር ቃል፣ በመንፈስ ቅዱስ የተፃፈ እና የእግዚአብሔር ሕይወት ያለበት፣ በኢየሱስ በሚያምኑት ውስጥ አዲስ ሕይወትን የሚፈጥር ዋና መሣሪያ ነው። የወንጌል መልእክት ከላይ ከእግዚአብሔር እንድንወለድ የሚያደርገን መንፈሳዊ ዘር ነው። ትክክለኛው የክርስቶስ ደቀመዝሙርነት ምልክት አማኞችን ነጻ በሚያወጣው በኢየሱስ ቃል ውስጥ መኖር እና መቀጠል ነው። እርሱ በመንፈሱ የጻፈውን የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጉም እንድንረዳ እና እንድናስተውል እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ አማኝ መንፈስ ቅዱስን ሰጥቷል (1ቆሮ. 2.9-16 ዝ. 2 ጴጥ. 1.21-22)። መንፈስ ቅዱስ የፍጥረት አጽናፈ ዓለም የመጨረሻ ዓላማ ሁሉን ቻይ የሆነውን እግዚአብሔርን ማክበር እንደሆነ ያስተምረናል (ኢሳ. 43.7፤ ምሳ. 16.4፤ 1 ቆሮ. 10.31)። ቅዱሳት መጻሕፍት፣ የሚፈጥረው ቃል፣ በእግዚአብሔር አገዛዝ ሥር ስንኖር እግዚአብሔርን እንድናከብር በመንፈስ ያስችለናል።
የቁልፍ ፅንሰ-ሀሳቦች ማጠቃለያ
ገጽ 163 10
1
/ 3 3
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
በዚህ ትምህርት ውስጥ የተካተቱትን ጭብጦች እና ማዕቀፎች በተመለከተ ጥያቄዎችዎን አብረውህ ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር ለመወያየት ጊዜው አሁን ነው ፡፡ አሁን ካጠናኸው ትምህርት አንጻር ምን ልዩ ጥያቄዎች አሉህ? ምናልባት ከዚህ በታች ያሉት ጥያቄዎች የራስህን ዝርዝርና ወሳኝ ጥያቄዎችን ለመመስረት ይረዱህ ይሆናል ፡፡ * ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው ስንል “የመጀመሪያዎቹ ፊደሎች” (ማለትም፣ ነቢያትና ሐዋርያት የጻፏቸው ሰነዶች)፣ ትርጉሞች፣ የትርጉም ቅጂዎች ወይም ሁሉም ነገር ማለታችን ነው? * እግዚአብሔር ዓለምን በቃሉ በኩል እንደፈጠረ ያለን እምነት ስለ ዝግመተ ለውጥ በሚደረጉ ንግግሮች ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል? የዝግመተ ለውጥ ንድፈ ሐሳብ ሊያሳስበን የሚገባ ነገር ነው ወይስ አይደለም? * የእግዚአብሔር ቃል ሕያው፣ የሚሰራ እና ፈጣሪ ከሆነ፣ በሚሰማው ሰው ሁሉ ልብ ውስጥ አንድ ዓይነት ሥራ የማይሠራው ለምንድነው? በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች የቃሉን መልእክት የማይቀበሉት ለምንድን ነው? * የእግዚአብሔር ቃል በኢየሱስ እና በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ባለው የእግዚአብሔር ቃል መካከል ያለው ግንኙነት በትክክል ምንድን ነው? የትኛው ነው ከሌላው መቅደም ያለበት? በተመሳሳይ መንገድ እንዲወሰዱ እና እንዲከበሩ የታሰቡ ናቸው? * የእግዚአብሔርን ቃል ስናጠና እርሱ እንደሚያስተምረን ማወቅ እንድንችል ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንዴት እናገናኘዋለን? * የእግዚአብሔርን ቃል በማህበረሰቡ አውድ ውስጥ ለማጥናት ከፈለግሁ የእግዚአብሔርን ቃል በግል የማጠናበት አስፈላጊነት ምንድነው? በቤተ ክርስቲያኔ ውስጥ በሚሰጡ አንዳንድ ትምህርቶች ወይም በመጋቢዬ ካልተስማማሁ ምን ማድረግ አለብኝ? ከፍተኛ ያለመግባባት ጉዳይ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ላይ ተከታታይ ትምህርቶችን በማስተናገድ ላይ እንዳለች አንዲት ወጣት ክርስቲያን መሪ በመጋቢው ስብከት ውስጥ የማትረዳቸው ትምህርቶች አጋጥሟታል ስለዚህም በአንደኛው እይታ፣ አልተስማማችም። አንዳንድ ነጥቦችን ከመጋቢው ጋር ስትወያይ አሳልፋለች ነገር ግን አንዳቸውም አላሳመኗትም፥ ከቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ ጋርም አልሄደላትም። መጋቢው ይህ እርሱ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት ያለው አመለካከት ብቻ እንደሆነ፣ ነገር ግን እርሱ ጥሩ አስተማሪ እንደሆነና ብዙዎች ሃሳቡን አሳማኝ ሆኖ እንዳገኙት በግልጽ ተናግሯል። መጋቢው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሪ፣ ጥሩ ክርስቲያን አስተማሪ እና በክርስቶስ የሆነ ትሑት ወንድም ነው። እንግዲህ ይህች እህት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ምን ማድረግ አለባት?
የተማሪው ትግበራ እና አንድምታዎች
ገጽ 164 11
1
ጥናቶች
1
ገጽ 164 12
3 4 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የእምነት ክህደት? በትምህርት ቤት ውስጥ በሳይንስ ክፍል ውስጥ ካሉ ተማሪዎች አንዱ በዝግመተ ለውጥ ንድፈ ሃሳብ ላይ ጥናታዊ ወረቀት መጻፍ አለበት። ይህ ተማሪ በቤተክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔር አለምን እንዴት በእግዚአብሔር ቃል በተለይም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንደፈጠረ ሲማር ቆይቷል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍጥረት የሚሰጠው ትምህርት ትክክል እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያምናል፣ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ በክፍል ውስጥ ስለ ሳይንስ የሚያጋጥሙትን ጉዳዮች በሙሉ የሚናገር አይመስልም። የሳይንስ ትምህርቱን ወደ ሃይማኖታዊ የውይይት ቡድን መለወጥ አይፈልግም ነገር ግን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሳይንስ ክፍል ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍጥረት ያለውን አመለካከት የሚናገርበትን መንገድ ለማግኘት እየታገለ ነው። ይህ ወጣት ወንድም ለምክር ወደ አንተ ቢመጣ ምን እንዲያደርግ ወይም እንዳያደርግ ትመክረዋለህ? የእግዚአብሔር ቃል በእንግሊዙ ንጉሥ ጄምስ መሰረት በቤተክርስቲያን የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ውስጥ የትኞቹ ትርጉሞች ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው በሚለው ላይ ከባድ አለመግባባት እና ግጭት ተፈጥሯል። በቡድን ውስጥ ልንጠቀምበት የሚገባው ብቸኛው መጽሐፍ ቅዱስ ኪንግ ጀምስ ባይብል እንደሆነና የተፈተነ እና እውነተኛ፣ ትርጉም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከጥንት ጀምሮ የተከበረ እና ውድ እንደሆነ ከሽማግሌዎች መካከል አንዱ ተናግሯል። የወጣቶቹ ቡድን አንዳንድ “ዘመናዊ” ትርጉሞችን ለመጠቀም አጥብቀው ይፈልጋሉ፣ ምክንያቱም ለማጥናት እና ለማስታወስ በጣም ቀላል ስለሆኑ ነው። ለቀደሙት የሽማግሌዎች ወገን ከአዲሱ ትርጉም ጥቅሶች ሲነበቡ፣ የጥቅሱ አጠቃላይ ትርጉም የተቀየረ ያህል ነው። ሁለቱም ወገኖች መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ የተጻፈው በእንግሊዝኛ እንዳልሆነ ያውቃሉ፣ ነገር ግን ከሁለቱም ወገኖች ዕብራይስጥ ወይም ግሪክኛ የሚረዳ የለም። እንደ መጋቢ ይህንን ችግር በቤት ህብረት ቡድን ውስጥ እንዴት መፍታት ይቻላል? መንፈስ ቅዱስ ያስፈልግሃል በቴሌቭዥን የተላለፈውን ማንም ሰው ያለ መንፈስ ቅዱስ ረዳትነት መጽሐፍ ቅዱስን ሊረዳ አይችልም የሚል ትምህርት ከሰማ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ከሚገኙት ዲያቆናት አንዱ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አለመረዳቱ በጣም ያሳስበዋል። መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበትና እንዳተመው ቢረዳም (ለምሳሌ፡ ሮሜ. 8.1-18፤ ኤፌ. 1.13፤ ገላ. 5.16-23)፣ “መንፈስ ቅዱስ ካላስረዳ” ሲባል ምን ማለት እንደሆነ አያውቅም። መንፈስ ቅዱስ አስተማረኝ ለማለት ብዙ ስሜታዊ ልምምዶችን ማድረጉን በጣም ይጠራጠራል፣ ሆኖም ይህ ውድ ወንድም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሳል፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው እና ክርስቶስን እየመሰለ የሚኖር አገልጋይ እንደሆነ ሁሉም ይገነዘባል። አሁንም በመንፈስ መማር/መረዳት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ይፈልጋል። ይህ ወንድም ቀጣይነት ባለው የመጽሐፍ ቅዱስ አረዳድ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ የማስተማር አገልግሎት ያለውን ሚና እንዲረዳ እንዴት ታስተምረዋለህ?
2
1
3
4
/ 3 5
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
1 ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል እና የጌታ ሕያውና ዘላለማዊ ቃል የጽሑፍ መዝገብ ናቸው። ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው (በትክክል የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነው) በሚቀበሉት እና በሚናገሩት ሁሉ ዘንድ ፍጹም ታማኝ ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር አምላከ ሥላሴ ለእግዚአብሔር ቃል እውነትነት ዋስትና ይሰጣል፤ ይህም ፍጹም እምነት የሚጣልበት ነው። በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት በእግዚአብሔር ፈጣሪ እና ሕይወት ሰጪ ቃል አማካኝነት ነው። ጌታ አምላክ ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ዓለምን በመቤዠት እና በጽድቅ አገዛዙ ሥር ያለውን ጽንፈ ዓለም እንዴት እንደሚመልስ ሁለተኛው የሥላሴ አካል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ራሱን ገልጧል። እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበት፣ ዓለምን የሚቤዠው እና አጽናፈ ዓለሙን በጽድቅ አገዛዙ የሚመልሰው እሱ ነው። ይህ የመንፈስ ቃል በሚያምኑት ውስጥ አዲስ ሕይወት ይፈጥራል። እውነተኛ ደቀመዝሙርነት በቤተክርስቲያን ውስጥ በዚህ ቃል ውስጥ መኖር ነው፣ እሱም በአማኙ ዘንድ መንፈሳዊ ብስለትን፣ ጥልቀትን፣ እና በእግዚአብሔር አላማ እና ፈቃድ ውስጥ እድገትን ያመጣል። ስለሚለውጠው ቃል ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል: Fee, Gordon D. and Douglas Stuart. How to Read the Bible for All its Worth. Grand Rapids: Zondervan, 1982. Montgomery, John Warwick. God’s Inerrant Word. Minneapolis: Bethany Fellowship, 1973.
የትምህርቱን ዋና ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ
ማጣቀሻዎች
Sproul, R.C. Knowing Scripture. Downers Grove: InterVarsity, 1977.
Tenney, Merrill. The Bible: The Living Word of Revelation. Grand Rapids: Zondervan, 1968.
የእግዚአብሔርን ቃል የመፍጠር ሃይል ጥናትህን ካጋጠመህ ወይም ከሚያጋጥምህ በጣም እውነተኛና ተግባራዊ የአገልግሎት ግንኙነትህ ጋር ለማያያዝ የምትሞክርበት ጊዜ አሁን ነው። በዚህ በሚቀጥለው ሳምንት የምታስበውና የምትጸልይበትም ሁዳይ ይኸው ነው። በዚህ ሳምንት በሕይወትህ እና በአገልግሎትህ የእግዚአብሔር ቃል የመፍጠር ኃይል እንዴት መገለጥ አለበት? በዚህ ትምህርት በቤተክርስቲያን ውስጥ በምታደርገው አገልግሎት ላይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ አንዳንድ ግንዛቤዎችን አግኝተሃል? መንፈስ ቅዱስ በደንብ እንድትረዳው ወይም በጥልቀት ለማጥናት መውሰድ ያለብህ ምን የተለየ ፅንሰ ሃሳብ ነው ያሳየህ? በጌታ ፊት ለአፍታ አሰላስል እና ቃሉ በቤተክርስቲያንህ፣ በቤተሰብህ እና በህይወትህ ውስጥ የሚፈጥር ቃል መሆኑን የበለጠ ግልፅ ማድረግ የምትችልበትን መንገድ እንዲገልጥልህ ጠይቀው።
የአገልግሎት ግንኙነቶች
ገጽ 164
13
3 6 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የእግዚአብሔርን ቃል ሕያው የሆነውን እና የሚሞላውን ሕይወት ሰጪ ኃይል እና መለኮታዊ ኃይልን በተመለከተ ልብህን እንዲያበራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለምነው። በሳምንቱ ውስጥ በህይወትህ ውስጥ ቃሉን በማንበብ፣ በማጥናት፣ በማስታወስ እና በማሰላሰል እንድታሳልፍ የበለጠ እና የተሻለ ጊዜ እንዲሰጥህ እግዚአብሔርን ለምን። እነዚህን እውነቶች ስታዳምጥና ስታሰላስል ከቤተክርስቲያንህ የሚወጡት ስብከቶች እና ትምህርቶች ህያው እንዲሆኑልህ እግዚአብሔርን ተማጸን። ከሁሉም በላይ በአንተ ትምህርት የእግዚአብሔርን ማንነት እና አላማ የበለጠ ግልፅ ለማድረግ በመንፈስ የተረዳ የእግዚአብሔር ቃል አስተማሪ አድርጎ እንዲጠቀምብህ እግዚአብሔርን ለምን። የእግዚአብሔርን ቃል በሚገባ በተረዳህ መጠን ወደ ራስህ ነፍስና አእምሮ ዘልቆ በአንተ ላይ ተጽዕኖ በሚያደርግ መጠን አገልግሎትህና ምስክርነትህ በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥም ሆነ እግዚአብሔር እርሱን እንድትወክል በሰጠህ ልዩ ልዩ ኃላፊነቶች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ የበለጠ ይሆናል።
ምክር እና ጸሎት
ገጽ 165 14
1
ምደባዎች
2 ጴጥሮስ 1: 19-21
የቃል ጥናት ጥቅስ
ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።
የንባብ የቤት ስራ
በሚቀጥለው ሳምንት በዚህ ትምህርት ይዘት (የቪዲዮ ይዘት) ላይ ጥያቄዎች ይጠየቃሉ። በተለይ በትምህርቱ ዋና ሃሳቦች ላይ በማተኮር ማስታወሻዎን ለመሸፈን ጊዜ ማሳለፍዎን ያረጋግጡ። የተመደበውን ንባብ አንብብ እና እያንዳንዱን ንባብ ከእያንዳንዱ አንቀጽ ወይም ሁለት በማይበልጥ ማጠቃለል። በዚህ ማጠቃለያ እባኮትን በእያንዳንዱ ንባብ ውስጥ ዋና ነጥብ ነው ብለው የሚያስቡትን የተሻለ ግንዛቤ ይስጡ። ዝርዝር ስለመስጠት ከልክ በላይ አትጨነቅ; በመጽሐፉ ክፍል ውስጥ የተብራራውን ዋና ነጥብ ብቻ ጻፍ። እባኮትን በሚቀጥለው ሳምንት እነዚህን ማጠቃለያዎች ወደ ክፍል አምጡ። (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ የሚገኘውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ” ተመልከት፡፡)
ሌሎች የቤት ስራዎች
ገጽ 165 15
/ 3 7
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
በሚቀጥለው ሳምንት ትምህርት ዓለምን ስለ ኃጢአት፣ ጽድቅ እና ፍርድ ለመኮነን እንደ መንፈስ ቅዱስ መሣሪያ የእግዚአብሔርን ቃል ኃይል ማጥናታችንን እንቀጥላለን። ኃጢአትን በተመለከተ ለእግዚአብሔር ሕግ አለመታዘዛችንን ቃሉ ይወቅሰናል። ጽድቅን በተመለከተ፣ ጌታ መለኪያ የሌለው ጻድቅ መሆኑን እና የእኛ ጽድቅ ደግሞ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ወይም ብቁ እንዳልሆነ ያሳያል። ፍርድን በተመለከተ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ወደ ጽድቅ ፍላጎቱ ከማምጣትና እነርሱም መታዘዛቸውን ለማሳየት ያለውን ፍላጎት ያሳያል። እንዲሁም ቃሉ እንዴት የኢየሱስ ክርስቶስን እውነት እንደመጽሃፍ ቅዱሳዊ ዋና ጭብጥ እና ትኩረት እንደሆነ፣ የእግዚአብሔር መንግስት የእግዚአብሔር ታሪክ መነሻ እንደሆነች፣ ነቢያት እና ሐዋርያት በዓለም ላይ የእግዚአብሔር መገለጥ እውነተኛ እና አስተማማኝ ምስክሮች እንደሆኑ እንመለከታለን።
ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት
1
ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል ፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከመምህርህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና Www.tumi.org/license ን ጎብኝ፡፡
ስም _________________________________________
ሞጁል 1: ለውጥ እና ጥሪ ንባብ ማጠናቀቂያ ገፅ
ቀን _________________________________________
ለእያንዳንዱ ለተመደበው ንባብ የጸሃፊውን ዋና ነጥብ አጭር ማጠቃለያ (አንድ ወይም ሁለት አንቀጽ) ጻፍ ፡፡ (ለተጨማሪ ንባብ ፣ የዚህን ገጽ ጀርባ ተጠቀም ፡፡)
ንባብ 1
ርዕሱ እና ጸሐፊው: ______________________________________________ ገጾች _____________
ንባብ 2
ርዕሱ እና ጸሐፊው: ______________________________________________ ገጾች ______________
/ 4 1
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሚወቅሰው ቃል
ት ም ህ ር ት 2
ገጽ 167 1
የትምህርቱ ዓላማዎች
ኃያል በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን!
በዚህ ትምህርት ውስጥ ያሉትን ጽሑፎች ካነበብክ፣ ካጠናህ እና ከተወያየህበት እና ከተገበርከው በኋላ፣ እውነቱን ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር መግለጽ እና መከላከል ትችላለህ፡- • የእግዚአብሔር ቃል ኃጢአትን፣ ጽድቅን እና ፍርድን የሚወቅስ ቃል ነው። • የእግዚአብሔርን አካልና ሥራ ከምንረዳባቸው መንገዶች ሁሉ፣ ኃጢአትን እንድንረዳ የሚያስችለን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነው - በሥፋቱ እና በባህሪው የሚበላሽ ነው። • የእግዚአብሔር ህግ በኃጢአታችን ይወቅሰናል፣ ይህም በድርጊታችን እና በዓሳባችን እና በእግዚአብሔር ቅዱስ ፍላጎቶች መካከል ያለውን ርቀት ያሳያል። • የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጽድቅ ይወቅሳል፣ የእግዚአብሔርን ህግ ለመጠበቅ ብቃት እንደሌለን ያሳያል፤ የእግዚአብሔርን ፅድቅ በእምነት በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ይገልጣል። • የእግዚአብሔር ቃል ፍርድን በሚመለከት ይወቅሳል፣ በሁሉም ቦታ ያሉ ፍጥረታትን ሁሉ ተጠያቂ ለማድረግ ያለውን ሃሳብ እና በእስራኤል እና በአህዛብ፣ በቤተክርስቲያን፣ በሰይጣን እና በመላእክቱ እና በክፉ ሙታን ሁሉ ላይ ሊመጣ ያለውን ፍርድ ያሳያል። • የእግዚአብሔር ቃል የእውነትን ተፈጥሮ፣ ማለትም፣ ስለ እግዚአብሔር፣ በዓለም ላይ ስላለው ስራ እና የሰው ልጅ እጣ ፈንታ እና አላማን በሚመለከት ትክክለኛ የሆነውን እምነትን ያመጣል። • የእግዚአብሔር ቃል ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት ዋና ርዕሰ ጉዳይ ማለትም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት እና ሥራ መገለጥ እምነትን ያመጣል። • የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን መገለጥ አጠቃላይ ዳራ ማለትም የመንግስቱን እቅድ መገለጥ በተመለከተ እምነትን ያመጣል። • የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን አካል እና እቅድ የመወከል እና የመናገር ተግባር በተሰጣቸው በእግዚአብሔር በተመረጡት መልእክተኞች፣ ነቢያት እና ሐዋርያት ታማኝነት እምነትን ያመጣል።
2
4 2 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ጥሞና
የመከራ በረከት መዝሙር 32:1-11ን አንብብ። ከህሊና ወቀሳ ጋር ታግለህ ታውቃለህ? የሐሰት ጥፋተኝነት አይደለም፣ አስተውል፣ ነገር ግን አንድ ስህተት እንደሠራህ በልብህ እያወቅክ፣ እና ባደረግከው ነገር መጥፎ ስሜት ተሰምቶህ እሱን ለማስተካከል፣ ለመፍታትና ለጎዳኸው ሰው ትክክል ለማድረግ ፈልገህ ታውቃለህ? ይህ ስሜት ሊኖሩህ ከሚችሉት በጣም ጤናማ ውስጣዊ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ነው ። ምንም እንኳን አሳዛኝ እና ከባድ ፣ አልፎ ተርፎም አሳፋሪ ቢመስልም ፣ በስህተትህ መወቀስ ስሜት ሊኖሩህ ከሚችሉ በጣም አስፈላጊ ስሜቶች ውስጥ አንዱ ነው። ስለ እሱ ምንም ጥርጥር የለውም፣ ይህ በደለኝነትህን በእግዚአብሔር ፊት በደለኝነትህን ያወቅህበት የተወቀስክበት ሁኔታ ከስሜት ጋር የተያያዘ ነው። በእውነቱ፣ ስህተት የሚሠራ እና ምንም የማያውቅ፣ የኃላፊነት ስሜት ወይም ነቀፋ የማይሰማው ሰው ከባድ መንፈሳዊ ችግር ውስጥ ገብቷል። በእግዚአብሔር የመፈረድ ችሎታ ማነስ ያለ ንስሐ፣ ሀዘን፣ ወይም ለመለወጥ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ስህተትን ለመስራት ተጋላጭ ያደርጋችኋል። ዳዊት በዚህ መዝሙር ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ይቅር የማለት ችሎታ እና ንስሃውን በማዘግየት እና ወደ ጌታ ሲመለስ ስለራሱ ህመም እና እፍረት ይናገራል። መንፈስ ቅዱስ በኃጢአታችን ሲወቅሰን የምናስተውለው መከራ ከሌሎቹ የውስጥ ትግል ወይም ስቃይ የተለየ የተባረከ መከራ ነው። ይህ መከራ የራሳችንን መተላለፍ፣ የእግዚአብሔርን የጽድቅ መስፈርት፣ የእግዚአብሔርን እውነት በራሳችን ኃይል መጠበቅ አለመቻላችንን፣ እና ለሠራነው ጥፋት ለእግዚአብሔር ያለንን ባለውለታችን እንድንገነዘብ ያስችለናል። ይህ መከራ ስለ ራሳችን እና ስለ እግዚአብሔር ወደ እውነት ይመራናል; በደላችንን በእግዚአብሔር ፊት እስክንቀበል ድረስ ምስኪኖች እንሆናለን; ይህ መከራ ለኃጢአታችን ይቅር ወደሚለው አንድ ብቻ ይመራናል። ከአምላክ ጋር መቀራረብ ከፈለግን ከሚያስፈልጉን ነገሮች ሁሉ የሚበልጠው አምላክ የሚፈልገውን በቀላሉ ሊያውቅ የሚችል ሕሊናና የሠራነውን ስህተት አምነን ለመቀበል ዝግጁ ከሆንን ምሕረት ሊሰጠን ፈቃደኛ መሆኑ ነው። ምሕረቱንም እንደገና ትቀበሉ ዘንድ ወደ እርሱ ኑ። ስለ መከራው በረከት እግዚአብሔር ይመስገን! የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ የሚገኝ) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ: የዘላለም አምላክ አባታችን ሆይ፣ ለእግዚአብሔር ቃል ሕይወት ሰጪ ኃይል እና መንፈስ ቅዱስህ ያንን ቃል በልባችን ውስጥ እንዴት እንደሚተከል እናመሰግናለን። ሁለታችንም ብቁ አለመሆናችንን እና ታላቅ ምህረትህን ስለሚገልጥልን ለእሱ የዋህ የማውገዝ ኃይሉ እናመሰግናለን። በፊትህ የተሰበረ እና የተከፈቱትን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ ነህ። የቃልህን የጥፋተኝነት ኃይል እና የልጅህን ደም የማንጻት ኃይል እንድንፈልግ ዛሬ ጸጋን ስጠን። በአንተ እና በአንተ ብቻ ምህረት እና ይቅርታ እና ጸጋ አለ. ክብር ለአንተ ይሁን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን! ጌታ እግዚአብሔር፣ የሰማይ አባት፣ ከእርሱ መልካም የሆነውን ሁሉ በቅንነት የምንቀበልበት፣ በእርሱም በየቀኑ ከክፉ ነገር ሁሉ የምንጠብቀው በቸርነቱ፣ እነዚህን ሁሉ ስጦታዎች በመንፈስ ቅዱስህ በሙላት እንድትጠቀምበት እንለምንሃለን። የዋህ ቸርነትህን እና ምህረትህን እንድናመሰግን እና እንድናወድስ ልብ እና እውነተኛ እምነት; በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልጅህ። አሜን።
ገጽ 167
2
2
የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት
ገጽ 167
3
~ Martin Luther. Devotions and Prayers of Martin Luther. Trans. Andrew Kosten. Grand Rapids: Baker Book House, 1965. p 77.
/ 4 3
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ማስታወሻዎችህን አስቀምጥ ፣ ሀሳብህን ሰብስበህ የትምህርት 1ን ፈተና ውሰድ ፣ የሚለውጠው ቃል
አጭር ፈተና ገጽ 168 4
ከሌላ ሰው ጋር በመሆን ላለፈው ክፍለ ጊዜ የተመደበውን የቃል ጥናት ክፍል ፃፍ ወይም በቃልህ አንብብ: 2 ጴጥ 1: 19 - 21
የቃል ጥናት ክፍል ቅኝት ገጽ 168 5
ባለፈው ሳምንት ለተሰጠው የንባብ የቤት ስራ መምህርህ የሚጠብቅብህን ዋና ዋና ነጥቦችና ማጠቃለያ አቅርብ (ንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ)።
የቤት ስራ ማስረከቢያ
እውቂያ
2
እውነተኛው ሃይማኖት ይጸናልን? በአካባቢው በሚገኝ ጁኒየር ኮሌጅ ውስጥ በፍልስፍና ትምህርት ክፍል ውስጥ የሚገኘው ከቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች አንዱ “ባህላዊ አንጻራዊነት” የሚለው ሐሳብ አጋጥሞታል። ይህ ሃሳብ የሚያመለክተው ሁሉም ባህሎች እኩል መሆናቸውን ነው፤ በመሆኑም ሁሉም የተለያዩ የእምነት ስርዓቶቻቸው, ሃይማኖታዊ አስተሳሰቦቻቸው እና የሥነ-ምግባር ደንቦች እኩል ናቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሃይማኖታዊ ሥርዓቶችና አስተሳሰቦች ሁሉ በላይ በሆነ መንገድ ልዩ እና ቀዳሚ ነው ብሎ የሚያምነው ይህ የቤተ ክርስቲያን መሪ ይህ ሃሳብ አስጨንቆታል። ስለ “ባህላዊ አንጻራዊነት” ይህን የተለየ አመለካከት እንዴት ሊረዳው ይገባል? የትኞቹ መዝሙሮች ናቸው “የጽዮን መዝሙሮች”? ወጣት ክርስቲያኖች ምን ዓይነት ሙዚቃ ማዳመጥ እንዳለባቸው በሚመለከት በወጣቱ ቡድን አባላት መካከል ከባድ ክርክር እየተፈጠረ ነው። ይህ ሁሉ የጀመረው ከታዳጊዎቹ አንዱ ከሚወዳቸው ራፕ አርቲስቶች አንዱን በሲዲ ማጫወቻ ውስጥ ለማጫወት ሲያስገባና አንዳንድ ልጆች አርቲስቱ የሚጠቅሳቸውን አይነት ነገሮች በመቃወማቸው ነው። ሙዚቃውን ያመጣው ወጣት እግዚአብሔርን በጣም የሚወድ ክርስቲያንና እያደገ ያለ ታዳጊ ሲሆን ለጠፉ ጓደኞቹ ጥሩ ምስክር እንዲሆን በዓለም ላይ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ ቢያምንም በተፈጠረው ውዝግብ ተጎድቷል። ሌሎች ደግሞ ይህ ዓይነቱ ሙዚቃ እግዚአብሔራዊ አይደለም ብለው ይከራከራሉ፤ ስለ ሁከት፣ ስቃይ እና ትግል የሚናገር በመሆኑ ብርታትን የሚሰጥ ሳይሆን ተስፋ የሚያስቆጥ ነው ብለው ያምናሉ። ሁለቱም ወገኖች ስለ ጉዳዩ አስፈላጊነት እና ስለ እውነታው ትግበራ እኩል ያመኑ ይመስላል። በሙዚቃ ጉዳይ ላይ በነዚህ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል የተፈጠረውን ይህን አለመግባባት ለመፍታት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ምንድነው?
1
ገጽ 168 6
2
4 4 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ፍትሃዊ አይደለም! በቅርቡ ስለ መጨረሻው ዘመን እና ዳግም ምጽአት የሚያጠና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን ከመጨረሻው ዘመን ጋር የተያያዙትን የተለያዩ ፍርዶች ማጥናት ጀመረ። በቡድኑ ውስጥ ካሉት እህቶች አንዷ ጥናቱ ብዙ ውስጣዊ ውጥረት እና ውዥንብር ፈጥሮባታል፣ በተለይም በአንድ ነጥብ ላይ - ስለ ክርስቶስ ሰምተው በማያውቁት ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል በሚለው ሃሳብ ላይ። በአእምሮዋ፣ ስለ ኢየሱስና ስለ ፍቅሩ ለመስማት ዕድል ባላገኙ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ላይ ይፈርዳል የሚለው ሐሳብ ተቀባይነት የለውም። “እግዚአብሔር ይህን ማድረግ የለበትም - ማንም ስለ ጌታ ስላልነገራቸው ብቻ በእግዚአብሔር ተፈርዶባቸው ወደ ገሃነም ይገባሉ። ይህ ደግሞ እነርሱ ምንም ባላጠፉት እግዚአብሔርን ስላለማወቃቸው መውቀስ ተገቢ አይሆንም።” በጥናቱ ውስጥ ላሉት ሌሎች ደግሞ ጉዳዩ የእግዚአብሔር ፍትሃዊነት ሳይሆን የእግዚአብሔር ቅድስና ነው። እግዚአብሔር ባስቀመጠው መስፈርት (ማለትም በክርስቶስ ማመን) ሁሉንም ካልፈረደ የጌታን ስም የሚጠራ ይድናል ብሎ ተናግሯልና የራሱን ጽኑ አቋም እንደሚያፈርስ ይከራከራሉ (ሮሜ 10፡9-10)። በግልጽ መወያየታቸውን ቢቀጥሉም ጉዳዩን ለመፍታት ግን አልቻሉም። ምን ማድረግ አለባቸው?
3
2
የሚወቅሰው ቃል ክፍል 1
ይዘት
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
በዚህ ክፍል፣ የእግዚአብሔር ቃል የመንፈስ ቅዱስ መሣሪያ ሆኖ ዓለምን ስለ ኃጢአት፣ ጽድቅ እና ፍርድ እንዴት እንደሚወቅስ እንመረምራለን። ኃጢአትን በተመለከተ የእግዚአብሔር ቃል ለእግዚአብሔር ህግ አለመታዘዛችንን እና ህይወታችንን ከቅዱስ ባህሪው እና ፍላጎቶች ጋር ባለማስተካከላችን ይወቅሰናል። ጽድቅን በተመለከተ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወሰን በሌለው የእግዚአብሔር ጽድቅ እና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት በሌለው የኛ ጽድቅ መካከል ያለውን ርቀት ያሳየናል። በመጨረሻም የእግዚአብሔር ቃል ፍርድን በተመለከተ የሚሰጠውን ትምህርት እንመለከታለን፣ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ከጽድቅ ፍላጎቶቹ እና ለእርሱ ካላቸው መታዘዝ አንጻር ተጠያቂ ለማድረግ ያለውን ሃሳብ እንማራለን። የዚህ የቃሉ የመጀመሪያ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እንድታዩ ለማስቻል ነው፡- • የእግዚአብሔር ቃል ኃጢአትን፣ ጽድቅን እና ፍርድን የሚወቅስ ቃል ነው። • የእግዚአብሔርን አካልና ሥራ ከምንረዳባቸው መንገዶች ሁሉ ኃጢአትን እንድንረዳ የሚያስችለን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነው። • የእግዚአብሔር ህግ በኃጢአታችን ይወቅሰናል፣ ይህም በድርጊታችንና በሃሳባችን እና በእግዚአብሔር የቅድስና ፍላጎት መካከል ያለውን ርቀት ያሳያል።
የክፍል 1 ማጠቃለያ
/ 4 5
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
• የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጽድቅ ይወቅሳል፣ የእግዚአብሔርን ህግ ለመጠበቅ ብቃት እንደሌለን ያሳያል፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ፅድቅ በእምነት በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ይገልጥልናል። • የእግዚአብሔር ቃል ፍርድን በሚመለከት ይወቅሳል፣ በሁሉም ቦታ ያሉ ፍጥረታትን ሁሉ ተጠያቂ ለማድረግ ያለውን ሃሳብ እና በእስራኤል እና በህዝቦች፣ በቤተክርስቲያን፣ በሰይጣን እና በመላእክቱ እና በክፉ ሙታን ሁሉ ላይ ሊመጣ ያለውን ፍርድ ያሳያል።
11.1
የቪዲዮ ክፍል 1 መግለጫ
I. መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት የዓለምን ኃጢአት ይኮንናል።
2
ገጽ 169
7
ሀ. ኃጢአት ዓለም አቀፋዊ እና በባሕሪውም በካይ እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስተምሩናል።
1. ኃጢአት ሁሉን አቀፍ ነው።
ዮሐንስ 16: 7 - 11 “እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤ ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤ ስለ ጽድቅም፥ ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህም በኋላ ስለማታዩኝ ነው፤ ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።”
ሀ. ሮሜ 3፡23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል፥ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል ይላል።
ለ. ኃጢአት በእግዚአብሔር ላይ ነው፤ ኃጢአት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ማመጽ ነው። (1) መዝ. 51.4
(2) ሉቃስ 15፡18
2. ኃጢአት ከእግዚአብሔር ባህሪ እና ዓላማ ጋር የሚቃረን እና የማይስማማ ማንኛውም ነገር ነው።
ሀ. ሁሉንም ሰው የሚነካ እና ሁሉንም የሰው ልጅ እኩል የሚያበላሽ ነው።
ለ. ኃጢአት ሁሉን አቀፍ ሲሆን ሁሉንም ፍፁም የሚበክል ባሕርይ አለው ሮሜ. 3.9-12.
4 6 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
3. ሁላችንም በእግዚአብሔር ፊት ጥፋተኞች ነን፣ ሮሜ. 5፡18-19።
ሀ. በራሳችን የኃጢአት ተግባር ምክንያት
ለ. ከአዳማዊው ኃጢአት ጋር ካለን የጠበቀ ግንኙነት የተነሳ (ሮሜ. 5.18-19)
ለ. የእግዚአብሔር ህግ በሃጢያታችን ይኮንነናል።
1. የእግዚአብሔር ሕግ ቅዱስ፣ በጎና ተቀባይነት ያለው ነው፤ እንደ ፍጥረቶቹ በእኛና በፍጥረቱ ላይ ያለውን ፍላጎት ይወክላል፤ የእኛንም ኃጢአት ይገልጣል።
2
ሀ. ሮሜ. 7፡7-8
ለ. ሮሜ. 7:12
2. ከሥጋችን ድካም የተነሣ ሕግን በመጠበቅ ማንም አይድንም።
ሀ. ማናችንም ብንሆን የእግዚአብሔርን ሕግ በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ባለው መንገድ አላከበርንም፣ ገላ. 3፡10-12።
ለ. ሕጉ የተዘጋ ሥርዓት ነው። የእግዚአብሔርን ህግ በትንሹም ቢሆን አለመጠበቅ በሁሉ ጥፋተኛ እንደመሆን ነው፣ ያዕ 2፡10-11
ሐ. የእግዚአብሔር ቃል የሰሚውን ልብ በመስበር ለእግዚአብሔር ወንጌል እውነት ይከፍታል።
1. የእግዚአብሔር ቃል ከኃጢአት የመጠበቅ መንፈሳዊ ኃይል አለው፣ መዝ. 119.11.
Made with FlippingBook Annual report maker