Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

1 1 8 /

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ምደባዎች

የቤት ስራ ማስረከቢያ የለም

የቃል ጥናት ጥቅስ

የቤት ስራ ማስረከቢያ የለም

የንባብ የቤት ስራ

አሁን የሚኒስትሪ ፕሮጀክትህ እና የኤክሴጀሲስ ፕሮጀክትህ በአስተማሪህ ተገምግሞና ተወስኖ ተቀባይነት ሊኖረው ይገባል ፡፡ የተሰጡትን ሥራዎች በጊዜው ማስረከብ ትችል ዘንድ አስቀድመህ ማቀድህን አረጋግጥ።

ሌሎች የቤት ስራዎች

ገጽ 186 14

የመጨረሻው በቤት የሚሰራ ፈተና ይሆናል ፤ ከመጀመሪያዎቹ ሶስት ፈተናዎች የተወሰዱ ጥያቄዎችን ፣ ከዚህ ትምህርት የተገኙ አዳዲስ ጥያቄዎችን እና አጫጭር ምላሾችን የሚጠይቁ የጹሑፍ ጥያቄዎችንም ያጠቃልላል ፡፡ እንዲሁም በፈተናው ላይ ለትምህርቱ የተሰጡትን የቃል ጥናት ጥቅሶች በማንበብ ወይም በመፃፍ ላይ መዘጋጀት አለብህ፡፡ ፈተናህን ስታጠናቅቅ እባክህ ለመምህርህ በማሳወቅ ቅጂህን ማግኘቱን አረጋግጥ። ማስታወሻ - የመጨረሻውን ፈተና ካልወሰድክ እና ለአስተማሪህ የተሰጡትን የቤት ስራዎች ሁሉ (የሚኒስትሪ ኘሮጀክት ፣ የኤክሴጀሲስ ፕሮጀክት እና የመጨረሻ ፈተና) ባግባቡ ካላጠናቀቅህ በዚህ ሞጁል የሚኖርህን አጠቃላይ ውጤት ማስላት አይቻልም። በምድር ሁሉ ላይ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሆነውን የእግዚአብሔርን ማዳን በተመለከተ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚለውጥ እና የሚጠራ ብርቱና ኃያል ነገር የለም። የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን ወንድ ወይም ሴት ልጆች ለአገልግሎት ለማስታጠቅ የእግዚአብሔር መሳሪያ ነው፥ ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲጠቀምብህ ከፈለግህ የቅዱሳት መጻሕፍት ተማሪ የመሆን ኃላፊነትህን በቁም ነገር ልትመለከተው ይገባል። አንተ ራስህ እና እንዲሁም የሚሰሙህ ሰዎች ሁሉ የእርሱን የመፍጠር፣ የማሳመን፣ የመለወጥ እና የመጥራት ኃይሉ እንዲሰማችሁ እግዚአብሔር ልብህንና ነፍስህን ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ቃል እንዲቆጣጠር ራስህን እንድትሰጥ ጸጋውን ይስጥህ። በዚህ ሞጁል ውስጥ የእርሱ ቃል የመጨረሻ ቃል ይሁንልን። ምሳሌ 2፡1-9 “ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ብትቀበል፥ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፥ ጆሮህ ጥበብን እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፥ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ። ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት፥ ለማስተዋልም ድምፅህን ብታነሣ፥ እርስዋንም እንደ ብር ብትፈላልጋት፥ እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፤ የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ። እግዚአብሔር ጥበብ ይሰጣልና፤ ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤ እርሱ ለቅኖች ደኅንነትን ያከማቻል፤ ያለ ነውር ለሚሄዱትም ጋሻ ነው፤ የፍርድን ጎዳና ይጠብቃል፤ የቅዱሳኑንም መንገድ ያጸናል። የዚያን ጊዜ ጽድቅንና ፍርድን ቅንነትንና መልካም መንገድን ሁሉ ታስተውላለህ።”

የማጠቃለያ ፈተና ማስታወቂያ

4

ስለዚህ ትምህርት (ሞጁል) የመጨረሻ ቃል

Made with FlippingBook Annual report maker