Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
/ 1 3
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሚፈጥረው ቃል
ት ም ህ ር ት 1
ገጽ 161
1
የትምህርቱ አላማ
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን !
የዚህን ትምህርት (ሞጁል) መጽሐፍ ካነበብክ፥ ካጠናህ፥ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል እና የጌታ ሕያውና ዘላለማዊ ቃል የጽሑፍ መዝገብ ናቸው የሚለውን ሃሳብ መሞገት ትችላለህ። • የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር አምላከ ሥላሴ ለእግዚአብሔር ቃል እውነትነት ዋስትና እንደሚሰጥ፣ ይህም ፍጹም እምነት የሚጣልበት መሆኑን ከቅዱሳት መጻሕፍት ማሳየት ትችላለህ። በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት በእግዚአብሔር ፈጣሪ እና ሕይወት ሰጪ ቃል አማካኝነት ነው። • ጌታ አምላክ ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እንዴት እንደሚገልጥ በተለይም ሁለተኛው የሥላሴ አካል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ራሱን በገለጠበት፣ ዓለምን በመቤዠት እና በጽድቅ አገዛዙ ሥር ያለውን ጽንፈ ዓለም እንዴት እንደሚመልስ ለመግለጽ ትችላለህ። • ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር የእግዚአብሔር ቃል፣ በእግዚአብሔር ሕይወት ውስጥ እንዳለ፣ መንፈስ ቅዱስ በሚያምኑት ውስጥ አዲስ ሕይወት የሚፈጥርበት መንገድ መሆኑን ማስረዳት ትችላለህ። • በዚህ በተተከለው የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ መቀጠል እና መቀበል እንዴት እውነተኛ የደቀመዝሙርነት ምልክት እና ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቤተሰብ የመሆን ምልክት እንደሆነ መግለጽ ትችላለህ። እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ቃል በቃል ኪዳኑ ማኅበረሰብ ውስጥ አብረን እንቀበላለን። • ቃሉ የፍጥረተ ዓለሙን የመጨረሻ ዓላማ የሆነውን የኃያሉን አምላክ መክበር እንዴት እንደሚገልጥ ማሳየት ትችላለህ። • የእግዚአብሔርን ቃል የመፍጠር ኃይል የሚናገረውን ምንባብ በማንበብ አሰላስለው። የሕያው የእግዚአብሔር ቃል መሻት መዝሙር 19፡7-11ን አንብብ። ዘመናችን የሚታወቅበት ነገር ከኖረ ያ የስሜታዊነት/የፍቅር ዘመን ነው ማለት ነው። ሰዎች ነገሮችን ለማግኘት፣ ተድላን ለመለማመድ፣ ቦታ ለማግኘት እና ግባቸውን ለማሳካት ራሳቸውን ይሰጣሉ፣ አንዳንዴም ለሚመኙት ነገር ትልቅ መስዋዕትነት ይከፍላሉ። ምናልባትም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ውስጥ በጣም አሳዛኙ ነገር ውሎ አድሮ ምንም
ገጽ 161
2
1
ጥሞና
ገጽ 161
3
Made with FlippingBook Annual report maker