Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
2 4 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሚፈጥረው ቃል ክፍል 2
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
የእግዚአብሔር ቃል መንፈስ ቅዱስ በሚያምኑት ውስጥ አዲስ ሕይወት የሚፈጥርበት መንገድ ነው። ስለዚህ፣ ይህንን የተተከለው የእግዚአብሔር ቃል መቀጠል እና መቀበል ትክክለኛው የደቀመዝሙርነት እና ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቤተሰብ የመሆን ምልክት ነው። እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ቃል በቃል ኪዳኑ ማኅበረሰብ ውስጥ አብረን እንቀበላለን። በመጨረሻም፣ በቃሉ ታማኝነት አማካኝነት የፍጥረተ-ዓለሙ የመጨረሻ አላማ ብቻውን ሊነግረን ይችላል፣ እርሱም የኃያሉ አምላክ ክብር ነው። የዚህ የሚፈጥረው ቃል ሁለተኛ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እንድታዩ ለማስቻል ነው፡- • የእግዚአብሔር ቃል በእግዚአብሔር ሕይወትውስጥ የተካተተ ነው፣ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቃል ሕይወት ሰጪ ኃይል ውጭ ምንም ዓይነት መንፈሳዊነት ወይም እውነተኛ እምነት የለም። እግዚአብሔር በአማኞች ዘንድ አዲስ ሕይወትን የሚፈጥረው በቃሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ ነው። • እውነተኛው የደቀመዝሙርነት ምልክት የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መንፈስና እውነት መቀበልና መቀጠል ነው። መንፈሳዊ እድገት በቤተክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት እና ከመታዘዝ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። • ከማይሻረው ሥልጣኑ የተነሳ፣ ለተፈጠረው ጽንፈ ዓለም የመጨረሻውን ዓላማ ሊሰጠን የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው፣ እርሱም በሁሉም ነገር የእግዚአብሔርን ክብር እና ሞገስ ማምጣት ነው።
የክፍል 2 ማጠቃለያ
1
I. የእግዚአብሔር ቃል በራሱ በእግዚአብሔር ሕይወት የተሞላ ነው፥ ስለዚህም በሚያምኑት ሁሉ ውስጥ አዲስ ሕይወትን ይፈጥራል።
ቪዲዮ ክፍል 2 መግለጫ
ሀ. ቃሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ላይ ላለ እምነት ምላሽ በመስጠት መንፈሳዊ ሕይወትን ይፈጥራል።
1. የእግዚአብሔር ቃል በአማኙ ውስጥ አዲስ መንፈሳዊ ሕይወትን ለመፍጠር ፍጹም ተቀዳሚ ነው።
ሀ. ያዕቆብ 1፡18
Made with FlippingBook Annual report maker