Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
6 8 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ከላይ መወለድ፣ የእግዚአብሔር ዲኤንኤ ተካፋዮች መሆንን ይጠይቃል። ኢየሱስ ይህን ስርነቀል የሆነ የመንግሥቱን ትምህርት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያውጅ ኒቆዲሞስ ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስና ስለ እግዚአብሔር ቃል መናገሩን አላወቀም ነበር። ኒቆዲሞስ በድንጋጤ እና ግራ በመጋባት አንድ ጎልማሳ ሰው እንዴት ወደ እናቱ ማሕፀን ተመልሶ ዳግም ሊወለድ እንደሚችል ጠየቀው። ኢየሱስ ስለ መንፈሳዊነት ሲሰጥ ስለነበረው መሠረታዊ አስተምህሮ ምንም ፍንጭ አልነበረውም። የዘላለምን ሕይወት ለማግኘትና ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ለመመሥረት አንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በመንፈስ ዳግም መወለድ አለበት። እግዚአብሔር ቃሉን እንደ መንፈሳዊ ዘር በመጠቀም በአማኙ ውስጥ አዲስ ተፈጥሮን ይፈጥራል፣ ይህም ተፈጥሮ በመንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ነው። የእግዚአብሔር ቃል በአዲስ አማኝ ሕይወት ውስጥ መለወጥን ያመጣል፥ የአንድን ሰው ሕይወት ከማስተካከል ወይም ከማሻሻል ያለፈ ነገር ያደርጋል - ሙሉ በሙሉ ይለውጠዋል። ክርስቶስ በእምነት ወደ ተለወጠው ሰው ልብ ውስጥ ሲገባ፣ አዲስ ህይወትን ያመጣውን አምላክ ባህሪያት ለማሳየት የሚያስችል አቅም ያለው አዲስ ሰው ሆኖ ዳግም ይወለዳል። ለዚህም ነው ክርስቲያናዊ ቁርጠኝነት ከውጫዊው ባህል ጋር በመመሳሰል ወይም በመጣጣም ሊጠቃለል የማይችለው። የእግዚአብሔር ሐሳብ በአማኙ ውስጥ የክርስቲያን አገልግሎት እና እምነት መሠረት እና ምንጭ የሆነ አዲስ ሕይወት መፍጠር እና ማሳየት ነው። የወላጆቻችንን መልክ፣ አቅም እና ባህሪ እንጋራለን። እንዲሁ ከአብ ብንወለድ ደግሞ እርሱን እንመስላለን፣ መልኩንም እናንጸባርቃለን፣ ህይወቱንም እንካፈላለን። ዮሐንስ 3 : 3 – 6 “ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው። ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።” ኢየሱስ ክርስቶስን በሚመለከት በወንጌል ቃል ላይ ያለ እምነት ብቻ በአማኙ ውስጥ አዲስ ሕይወት መፍጠር ይችላል። አንተስ? በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከእግዚአብሔር ቤተሰብ መወለድህን የሚያሳዩትንና “የአባትህ ዓይን” እንዳለህ የሚያረጋግጡትን ባህሪያት ታሳያለህ? “ዳግመኛ መወለድ አለብህ!” የኢየሱስን ቃል እንደገና ተመልከት፡-
3
Made with FlippingBook Annual report maker