Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
/ 7 1
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሚለውጠው ቃል ክፍል 1
ይዘት
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
ይህ ክፍል በእግዚአብሔር ቃል እና በመለወጥ እና በመቀየር ኃይል መካከል ያለውን ግንኙነት ይጠይቃል። በዚህ ጥናት የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንዴት የሚለወጥ ቃል እንደሆነ እንማራለን። ይህ የሚለውጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ወደ ሜታኖያ ማለትም ወደ እውነተኛው የኃጢአት ንስሐ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ይመራናል። በተጨማሪም፣ በአማኙ ላይ ንስሐን የሚያመጣው ይኸው ወንጌል እንዴት ወደ እምነት እንደሚያመልሰን እንመለከታለን። ወደ ንስሐ የሚመራን ቃል ደግሞ ወደ እምነት (ፒስቲስ) ይመራናል፣ በእርሱም እግዚአብሔር አማኝን ከኃጢያት ቅጣት፣ ኃይል እና መገኘት ያድነዋል። ለዚህ የሚለወጠው የቃሉ የመጀመሪያ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እንድትረዳ ለማስቻል ነው፡- • የሚለወጠው ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከሚገኘው የመዳን የምስራች ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ትረዳ ዘንድ ነው። ይህም የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሚለውጥ ቃል ነው። • የሚለውጠው ቃል ወደ ሜታኖያ እንደሚመራን ትረዳለህ፥ ይህም ማለት ከኃጢአት ንስሐ መግባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። • የሚለወጠው ቃል፣ ንስሀን የሚያመጣው ቃል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ካለ እምነት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሲሆን ነፍስን ከኃጢያት ቅጣት፣ ልምምድ እና ሃይል እንደሚያድን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መታመንን ይፈጥራል።
የክፍል 1 ማጠቃለያ
3
I. የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሚለውጥ ቃል ነው።
የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት
ሀ. ለአይሁድም ለግሪክም የእግዚአብሔር ኃይል የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የኢየሱስን የመስቀል ላይ መስዋዕትነት የሚመለከት ቃል ነው።
ገጽ 174 5
1. ከመስቀሉ በፊት የመዳን ቃል የመጣው በመጠባበቅ መልክ የመሲሑ ሥራ ተስፋ በመሆን በእንስሳት የደም መስዋዕትነት ምሳሌ ነው።
ሀ. በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው የ“ስርየት” እሳቤ የሚያወራው ኃጢአት “ስለሚስተሰረይለት” የመታለፍ ጽንሰ-ሀሳብ ነው። የመሥዋዕቱ ሥርዓት እውነተኛው የእግዚአብሔር በግ ሁሉንም የኃጢአትና የጽድቅን ጉዳዮች የሚፈታበትን ቀን በጉጉት ይጠባበቃል።
Made with FlippingBook Annual report maker