Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

7 8 /

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ማጠቃለያ

» የሚለወጠው ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የመዳን የምስራች ጋር ተመሳሳይ ነው። የክርስቶስ ወንጌል የሚለውጥ ቃል ነው። » ይህ ብርቱ ቃል ወደ ሜታኖያ ይመራናል፣ ማለትም፣ ከኃጢአት እና ከንቱ ሃይማኖታዊ ሥራዎች ንስሐ ለመግባት በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር እምነት ይመራናል። » ይህ ቃል በውስጣችን እምነትን (ፒስቲስ) ያፈራል፣ በዚህም አማካኝነት እግዚአብሔር አማኙን ከኃጢአት ቅጣት፣ ኃይል እና ህልውና ያድነዋል፥ ይታደገውማል።

እነዚህን እና ሌሎች ቪዲዮው ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ የቻልከውን ያህል ጊዜ ውሰድ። የሚለውጠው ቃል የኢየሱስ ወንጌል ነው፣ ወደ ንስሐ እና እምነት፣ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መዳን የሚመራን። እነዚህን ፅንሰ-ሀሳቦች ማወቅ እና መረዳት ለአገልግሎት እና ለደቀመዝሙርነት በተለይም የሶላ ግራቲያ (በጸጋ ብቻ) እና ሶላ ፊዴ (በእምነት ብቻ) የተሐድሶ ሃሳቦች ወሳኝ ናቸው። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፥ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አስደግፍ፡፡ 1. የማያምን ሰው በክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት ለመጀመር ውጫዊ የአኗኗር ለውጥ ብቻ ሳይሆን በውስጡ አዲስ ሕይወት መለማመድ ለምን አስፈለገው? 2. የእግዚአብሔር ቃል በወንጌል እና በአዲሱ አማኝ መለወጥ መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? በእግዚአብሔር ለመዳን ስለ ክርስቶስ የሚናገረውን ምሥራች ማመን ለምን አስፈለገ? 3. ሜታኖያ የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉም ምንድን ነው? የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ንስሐ ሐሳብ አንዳንድ ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የትኞቹ ናቸው? በውስጡ ያለውን የንስሐ ተግባር ያላካተተ የማዳን እምነት ሊኖር ይችላል? መልስህን አስረዳ። 4. ሶላ ግራቲያ የሚለው ቃል ምን ማለት ነው? ይህ ቃል የሚለውጠውን የቃሉን ምንነት እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው? 5. ለሶላ ፊዴ የሚሰጠው ትርጉም ምንድን ነው? የተሃድሶ አስተምህሮ (“በእምነት በጸጋ ብቻ”) እግዚአብሔር የአዲሱን አማኝ ነፍስ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚቀይርበትን መንገድ እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው? 6. ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐዋርያው ​ምስክር ጋር የተያያዙትን ልዩ ነገሮች ዘርዝር። እኛ አማኞች ለኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት፣ ሞት፣ መቀበር እና ትንሳኤ የሚሰጡትን ምስክርነት እንዴት እንቀበል? 7. ለክርስቲያን በኢየሱስ በኩል ከእግዚአብሔር የመቤዠት እና የመለወጥ ኃይል ጋር የተያያዙት ሦስቱ ጊዜያት ምን ምን ናቸው? እግዚአብሔር በአንድ ምዕራፍ ሊያድንና አማኙ በሌላኛው ምዕራፍ ሊጠፋ ይችላልን? አብራራ።

መሸጋገሪያ 1

የተማሪው ጥያቄዎችና ምላሾች

ገጽ 175

8

3

Made with FlippingBook Annual report maker