Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

/ 8 9

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

የእግዚአብሔር ቃል ስላለው የመለወጥ ሃይል ተጨማሪ ሃሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል: Henrichsen, Walt. Layman’s Guide to Applying the Bible. Grand Rapids: Zondervan Books, 1985.

ማጣቀሻዎች

Kuhatschek, Jack. Applying the Bible. Grand Rapids: Zondervan Books, 1990.

Lewis. C. S. Mere Christianity. New York: Macmillan Company, 1960.

Stott, J. R. W. Understanding the Bible. Glendale: Regal Books, 1972.

እነዚህን እውነቶች በቤተክርስቲያንህ በኩል ከራስህ አገልግሎት ጋር ለማዛመድ መፈለግ የትምህርቱን ዋና ነገር ያመለክታል። የእግዚአብሔርን ቃል የመለወጥ ኃይልን ስታስብ አሁን በአገልግሎትህ ላይ እነዚህ እውነቶች ተግባራዊ ይደረጉ ዘንድ በሚያስፈልግበት ጊዜ ምን ልዩ ተግዳሮቶች፣ ጉዳዮች ወይም ሁኔታዎች ያጋጥሙሃል? በከተማ አገልግሎት ዙሪያ ካሉት ጉዳዮች ሁሉ ምናልባትም እንደዚ አንገብጋቢ ጉዳይ ሊኖር አይችልም፡- የእግዚአብሔርን ቃል ለመጠቀም ያለን ችሎታና ድፍረት፣ እንዲሁም ቃሉን የምንካፈልላቸውን ሰዎች ህይወት የመለወጥ እና የመቀየር ችሎታው ነው። በምትሳተፍባቸው የተለያዩ የአገልግሎት እድሎች ላይ በማተኮር በዚህ ትምህርት ስለ እግዚአብሔር ቃል ከተማርከው ትምህርት አንጻር ሁኔታዎችን ወይም ጉዳዮችን እንደገና ማሰብ ትችል ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዲያስተምርህ ጠይቅ። ለዚህ ሞጁል የምትሰራውን የሚኒስትሪ ፕሮጀክት ስታስብ ምናልባት ከእነዚህ እውነቶች ጋር በተግባራዊ መንገድ በማገናኘት ልትጠቀምበት ትችላለህ። ማስተዋል ይሰጥህ ዘንድ የእግዚአብሔርን ፊት ፈልግ፤ ያገኘኸውንም ግንዛቤ በክፍልህ ውስጥ ላሉ ሌሎች ተማሪዎች ለማካፈል በቀጣዩ ሳምንት ይዘህ ቅረብ። አንተ ወይም የምታገለግላቸው ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የመለወጥ ሃይልን የምትለማመዱባቸው በጣም የተለዩ ምሳሌዎችን እና ሁኔታዎችን እንደምታውቅ ጥርጥር የለውም። ምናልባትም ከእነዚህ ፍላጎቶች እና ሁኔታዎች መካከል አንዳንዶቹ ይበልጥ ግልጽ የሆኑልህ የእግዚአብሔርን ቃል የመለወጥ ችሎታ ባጠናህበት ሂደት ውስጥ ሊሆን ይችላል። እንግዲህ የቃሉን የመለወጥ ሃይል እና ሌሎችንም የህይወት ጥያቄዎች አብሮህ ወደ ጌታ የሚያቀርብ የጸሎት አጋር ለመፈለግ አታመንታ። በዚህ ጉዳይ ላይ አስተማሪህ ዘወትር ከጎንህ ለመሆን ዝግጁ መሆኑን አስታውስ። እንዲሁም፣ በዚህ ጥናት ላይ ለሚፈጠሩብህ ማናቸውም ጠጣር ጥያቄዎች ይመልሱልህ ዘንድ የቤተክርስትያን መሪዎችህ (በተለይም መጋቢህ) የተዘጋጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብሃል። ለእግዚአብሔር ራስህን ክፍት በማድረግ እርሱ እንደወደደ እንዲመራህ ፍቀድለት። እግዚአብሔር ቃሉን በምልክቶች እና በድንቆች በአንተ እና በምታገለግላቸው ሰዎች ህይወት ውስጥ እንዲያጸና ለምነው። በኢሳይያስ 55.8-11 ላይ ከአፌ የሚወጣ ቃሌ የምሻውን ያደርጋል፥ የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም የሚለውን የእግዚአብሔርን ልዩ የተስፋ ቃል ያዝ።

የአገልግሎት ግንኙነቶች

3

ምክር እና ጸሎት

ገጽ 177

14

Made with FlippingBook Annual report maker