Conversion and Calling, Amharic Student Workbook

1 0 2 /

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ማጠቃለያ

» ቃሉ ወደ ደቀመዝሙርነት ይጠራናል፣ በእግዚአብሔር ታላቅ መንግሥት ታሪክ ውስጥ በደቀመዝሙርነት ሕይወት እንድንሳተፍ ተጠርተናል። » ኢየሱስን ከጋብቻ እና ከቤተሰብ በላይ እንድንወደው ተጠርተናል፥ በዚህም የእርሱ ክብር ሃሳብ በህይወታችን ውስጥ ዋናውን ቦታ ይይዝ ዘንድ ነው። » የተጠራነው በዚህ ዓለም ውስጥ እንደ እንግዶችና መጻተኞች እንድንኖር ነው፣ እርሱ እንደመራን ለእርሱ እንገኝ ዘንድ ነፃ ሆነን እንድንኖርን ነው። » ለራሳችን እየሞትን ለክብሩ እንድንኖር ለክብሩ የመሥዋዕት አገልጋዮች እንሆን ዘንድ ተጠርተናል። እነዚህን እና ሌሎች ቪዲዮው ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ በቂ ጊዜ በመውሰድ ከታች ያሉትን ጥያቄዎች መልስ። በኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት ስር ቃሉ እንዴት የደቀመዝሙርነት ህይወት እንድንኖር እንደሚጠራን ወሳኝ ሀሳቦችን እንደተረዳህ እርግጠኛ ሁን። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. ንስሐ እንድንገባ እና በኢየሱስ ክርስቶስ እንድናምን በሚጠራን በእግዚአብሔር ቃል እና በኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንድንኖር በሚጠራው በዚያው ቃል መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? መልስህን አስረዳ። 2. ጋብቻንና ቤተሰብን ጨምሮ ከሌሎች ነገሮች ሁሉ በላይ ‘ኢየሱስን መውደድ’ ምንን ይጨምራል? ከሌሎች ታማኝነት ጋር ሲነጻጸር አንድ ሰው ለኢየሱስ ያለውን ታማኝነት እንዴት መረዳት አለብን? ግለጽ። 3. እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ታማኝ በመሆን እና ስደትን በመቀበል መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ሆነን ነገር ግን ከእንደዚህ ዓይነት ስደት ማምለጥ የምንችልበት መንገድ ይኖር ይሆን? 4. “በዚህ ዓለም እንደ እንግዶችና መጻተኞች በክርስቶስ ያገኘነውን አዲሱን ማንነታችንን እንቀበል” ማለት ምን ማለት ነው? ለእግዚአብሔር ቅርብ ነን ስለሚሉ ነገር ግን ዓለምንና ክፉ ስርዓቷን ስለሚወዱት ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ይላሉ? 5. ክርስቲያኖች የሚመጣው የእግዚአብሔር መንግሥት ተወካዮች እንደመሆናቸው መጠን የዓለምን ሀብት፣ ዝናና ሥልጣን ለማግኘት ምን ያህል ጥረት ማድረግ አለባቸው? መልስህን በጥንቃቄ አብራራ። 6. እግዚአብሔር ለክብሩ እንደ አገልጋዮች በመስዋዕትነት እንድንኖር ጠርቶናል ሲባል ምን ማለት ነው?

መሸጋገሪያ 1

የተማሪው ጥያቄዎች እና መልሶች

4

Made with FlippingBook - Online magazine maker