Conversion and Calling, Amharic Student Workbook
/ 1 4 3
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
አ ባ ሪ 1 5 የመንገደኛው ፍለጋ ዶን ኤል ዴቪስ
ታላቁን ንጉስ ለማየት ፍለጋ ላይ እንደ ፒልግሪሞች መሆን አንድ አይነት ማዕከል፣ አንድ አይነት ተስፋ፣ አንድ አይነት ህልም ለመካፈል
እያንዳንዱን ሸክም ተሸክመን ጎን ለጎን መሄድ አለብን በእምነት በመጽናት ፣ በስሜት እና በከፍተኛ ጥንቃቄ
ከክርስቶስ ጋር ባለው ወዳጅነት ክብራችን እና አክሊላችን እውነተኛ ደስታችን በእርሱ ብቻ እንዲገኝ ነው።
የእያንዳንዱን ነፍስ ዋጋ በአዲስ አይኖች ለማየት በምድር ላይ ካሉት ከሁሉም ትንሹን ለመንከባከብ
ምስጋናው እንዲትረፈረፍ በጥልቅ ናፍቆት ለመቃጠል በጣፋጭ አንድነታችንም ውበቱ ይገለጥ ዘንድ
አዎ፣ ግባችን፣ ክብራችን፣ ግባችን ይህ ነው። ክርስቶስ እንደገና በዚህ ምድር ላይ እንዲታይ መንግሥቱና ክብሩ በኃይል እንዲታወቅ ነው። መልካሙ በእኛ ይገለጥ ዘንድለወዳጆቻችን ስንል ህይወታችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ነው።
ፍሬው ይወለድ ዘንድ ጸጋውም እንዲበዛ በጋራ በመካፈል ብርሃናችን እንዲበራ።
ዓለም በአንድ ልብ በአንድ ጊዜ ወደ እርሱ ይሳብ ዘንድ የተሰበረውም ልብ ሁሉ፣ ትሑት ወይም የዋህ ቢሆን
የጌታችንን ምህረት ቀምሰው፣ ይፈወሱ እና ነጻ ይወጡ ዘንድ ነው። እንግዲህ አሁን የዚህን ዓለም ጣፋጭ ደስታ እንደ ትቢያ እንቆጥራለን
የመንግሥቱን እውነተኛ ሀብቶች ለማግኘት ወደ ግብ እንተጋለን። በክብር ተልእኮአችን እንድትቀላቀሉን እንጋብዛችኋለን። ከነዘውዱ ከእኛ ጋር በደስታ ሊቀመጥ፥ እንደ እንግዳ ያለንን ሁሉ እንሰጣለን እና አንድ ነገር ማድረግ አለብን - በታላቁ ንጉሥ በክርስቶስ ፊት ባዘጋጀውው ግብዣ ላይ አብሮ ለመቅረብ።
Made with FlippingBook - Online magazine maker