Conversion and Calling, Amharic Student Workbook

/ 3 5

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

1 ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል እና የጌታ ሕያውና ዘላለማዊ ቃል የጽሑፍ መዝገብ ናቸው። ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው (በትክክል የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነው) በሚቀበሉት እና በሚናገሩት ሁሉ ዘንድ ፍጹም ታማኝ ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር አምላከ ሥላሴ ለእግዚአብሔር ቃል እውነትነት ዋስትና ይሰጣል፤ ይህም ፍጹም እምነት የሚጣልበት ነው። በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት በእግዚአብሔር ፈጣሪ እና ሕይወት ሰጪ ቃል አማካኝነት ነው። ጌታ አምላክ ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ዓለምን በመቤዠት እና በጽድቅ አገዛዙ ሥር ያለውን ጽንፈ ዓለም እንዴት እንደሚመልስ ሁለተኛው የሥላሴ አካል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ራሱን ገልጧል። እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበት፣ ዓለምን የሚቤዠው እና አጽናፈ ዓለሙን በጽድቅ አገዛዙ የሚመልሰው እሱ ነው። ይህ የመንፈስ ቃል በሚያምኑት ውስጥ አዲስ ሕይወት ይፈጥራል። እውነተኛ ደቀመዝሙርነት በቤተክርስቲያን ውስጥ በዚህ ቃል ውስጥ መኖር ነው፣ እሱም በአማኙ ዘንድ መንፈሳዊ ብስለትን፣ ጥልቀትን፣ እና በእግዚአብሔር አላማ እና ፈቃድ ውስጥ እድገትን ያመጣል። ስለሚለውጠው ቃል ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል: Fee, Gordon D. and Douglas Stuart. How to Read the Bible for All its Worth. Grand Rapids: Zondervan, 1982. Montgomery, John Warwick. God’s Inerrant Word. Minneapolis: Bethany Fellowship, 1973.

የትምህርቱን ዋና ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ

ማጣቀሻዎች

Sproul, R.C. Knowing Scripture. Downers Grove: InterVarsity, 1977.

Tenney, Merrill. The Bible: The Living Word of Revelation. Grand Rapids: Zondervan, 1968.

የእግዚአብሔርን ቃል የመፍጠር ሃይል ጥናትህን ካጋጠመህ ወይም ከሚያጋጥምህ በጣም እውነተኛና ተግባራዊ የአገልግሎት ግንኙነትህ ጋር ለማያያዝ የምትሞክርበት ጊዜ አሁን ነው። በዚህ በሚቀጥለው ሳምንት የምታስበውና የምትጸልይበትም ሁዳይ ይኸው ነው። በዚህ ሳምንት በሕይወትህ እና በአገልግሎትህ የእግዚአብሔር ቃል የመፍጠር ኃይል እንዴት መገለጥ አለበት? በዚህ ትምህርት በቤተክርስቲያን ውስጥ በምታደርገው አገልግሎት ላይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ አንዳንድ ግንዛቤዎችን አግኝተሃል? መንፈስ ቅዱስ በደንብ እንድትረዳው ወይም በጥልቀት ለማጥናት መውሰድ ያለብህ ምን የተለየ ፅንሰ ሃሳብ ነው ያሳየህ? በጌታ ፊት ለአፍታ አሰላስል እና ቃሉ በቤተክርስቲያንህ፣ በቤተሰብህ እና በህይወትህ ውስጥ የሚፈጥር ቃል መሆኑን የበለጠ ግልፅ ማድረግ የምትችልበትን መንገድ እንዲገልጥልህ ጠይቀው።

የአገልግሎት ግንኙነቶች

Made with FlippingBook - Online magazine maker