Conversion and Calling, Amharic Student Workbook
5 4 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
II. የእግዚአብሔር ቃል ከአብርሃም ጋር በገባው እና በኢየሱስ ክርስቶስ በተፈጸመው የእግዚአብሔር መንግሥት እቅድ ቃል ኪዳን አማካኝነት እውነትን ያሳየናል።
ሀ. ኢየሱስ ሁለቱንም የቅዱሳት መጻሕፍት ኪዳናት በአንድነት የሚያገናኝ ርዕሰ ጉዳይ ነው።
1. ሐዋርያው ዮሐንስ እንደተናገረው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የክፉውን ሥራ ሊያፈርስ ወደ ዓለም መጣ፣ 1ኛ ዮሐንስ 3፡8።
2. በውድቀት ውስጥ በአዳም እና በሔዋን ዓመፅ ምክንያት፣ የሰው ልጅ የኃጢአት ባሪያ ተደርጎ፣ በእርግማን ሥር ሆኖ፣ እና ለሞት ፍርሃትና አምባገነንነት ተዳርጓል (ሥጋዊ ሞት እንዲሁም ከእግዚአብሔር መለያየት እንዲገጥማቸው አድርጓል)።
2
3. ነገር ግን እግዚአብሔር ከታላቅ ፍቅሩ እና ምሕረቱ የተነሳ የኃጢአታችንን ዋጋ እንዲከፍልና ዲያብሎስ በሰው ልጆች እና በፍጥረት ላይ ያለውን የይገባኛል ጥያቄ ያጠፋ ዘንድ አንድያ ልጁን ወደ አለም ላከው፣ ቲቶ 2፡11-14
ለ. የእግዚአብሔር የሰውን ልጅ የመቤዠት እቅድ ከአብርሃም ጋር በተደረገው ቃል ኪዳን ተገልጧል።
1. እግዚአብሔር ለአብርሃም ቃል ኪዳን ገባ፣ ዘፍ. 12፡1-3.
ሀ. እርሱን ታላቅ ሕዝብ ለማድረግ
ለ. እርሱን ለመባረክ እና ስሙን ታላቅ ለማድረግ
ሐ. የባረኩትን ለመባረክ የረገሙትንም ለመርገም
መ. ከአብርሃም የተነሳ የምድር አህዛብ ሁሉ እንዲባረኩ
Made with FlippingBook - Online magazine maker