Conversion and Calling, Amharic Student Workbook
5 6 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
III. የእግዚአብሔር ቃል በነቢያት እና በሐዋርያት ምስክርነት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የእውነት መልእክተኞች አማካኝነት ስለ እውነት ይውቅሳል። የእግዚአብሔር የቃሉ መገለጥ በነቢያት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በተሾሙት መልእክተኞቹ፣ በሐዋርያቱ በኩል ተነግሯል።
ሀ. እግዚአብሔር በጥንት ጊዜ በነቢያት ተናግሯል።
1. እግዚአብሔር ለተመረጡት ሕዝቡ በነቢያት ተናግሯል፣ ዕብ. 1.1.
2. እግዚአብሔር በነቢያቱ በኩል የተናገረው የሰውን ልጅ ለማዳን ያለውን እቅድ ዋና ዝርዝር ይዟል፣ 1 ጴጥ. 1.10-12.
2
ለ. እግዚአብሔር ለዓለም ለመጨረሻ ጊዜና ፍጹም በሆነ መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ተናግሯል።
1. ኢየሱስ ለሰው ልጆች የእግዚአብሔር የመጨረሻው መገለጥ ነው፣ ዕብ. 1.2.
2. ኢየሱስ ብቻውን የአብን ክብር የሚገልጥ ነው፣ ዮሐ 1፡18.
3. እንደ ክርስቶስ በቂ የሆነ ሌላ የመገለጥ ምንጭ የለም፣ ቆላ. 2፡8-10።
ሐ. ኢየሱስ ሥልጣን ያለውን የተስፋውን መልእክት ለሐዋርያት በአደራ ሰጥቷል።
1. ከክርስቶስ ጋር ለመሆንና ስሙን ለመስበክ የተመረጠ፣ ማርቆስ 3፡13-15
2. ዮሐንስ 17 የእግዚአብሔርን መገለጥ እንደሚገልጡ ሰዎች የሐዋርያትን ልዩ ሚና በተመለከተ ትልቅ ግንዛቤን ይሰጣል። ኢየሱስ ለእርሱ እንደ ተመረጡ መልእክተኞች ለሐዋርያት ልዩ ሥልጣንና ምስክርነት ሰጥቷቸዋል፤ እንዲሁም፡-
ሀ. የአብን ስም ገልጦላቸዋል።
Made with FlippingBook - Online magazine maker