Conversion and Calling, Amharic Student Workbook
/ 8 7
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ስለእግዚአብሔር ቃል የመለወጥ ኃይል ምንነት ጥያቄዎችህን ከተማሪዎችህ ጋር የምትወያይበት ጊዜ አሁን ነው። በንስሐ እና በእምነት ስለመለወጥ የራስህን ሃሳቦች በጥንቃቄ በማሰብ በውይይትህ ውስጥ አብራራቸው። አሁን ካጠናኸው ጽሑፍ አንጻር ምን ልዩ ጥያቄዎች አሉህ? ምናልባት ከዚህ በታች የቀረቡት አንዳንድ ጥያቄዎች የራስህን፣ ልዩና ወሳኝ ጥያቄዎችን ለመፍጠር ሊረዱህ ይችላሉ። * አንድ ሰው እግዚአብሔርን በቅርበት አውቄአለሁ ብሎ መናገር ይችላልን? እግዚአብሔርን አውቃለሁ የሚል ሰው በሕይወቱ ውስጥ እውነተኛ ለውጥ እንዳመጣ የሚያሳይ ምልክት ማሳየቱ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? * የእግዚአብሔር ቃል ያመነውን ሰው አመለካከትና ተግባር ምን ያህል ይለውጣል? ይህ ሂደት በልብ ውስጥ እንዴት እንደሚከናወን ማወቅ ለእኛ አስፈላጊ ነውን? ለምን? * አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል በሰዎች (በአማኞችም ጭምር) ሕይወትና አመለካከት ላይ ምንም ተጽእኖ እንደሌለው የሚመስለው ለምንድነው? ቃሉ እየተሰበከ በማንም ሰው ሕይወት ውስጥ ምንም አይነት ለውጥ እየታየ ባይመስል ችግሩ ምንድን ነው? * ቃሉን የሚሰሙት አማኞች ሆኑም አልሆኑ የእግዚአብሔርን ቃል ለሌሎች ባደረስን ቁጥር አንዳች ዓይነት ለውጥ ወይም ምላሽ እንዲደረግ መጠበቅ አለብን? መልስህን አስረዳ። ንስሐ መግባትን እንደ “ሥራ” ልንወስደው ይገባልን? በቤተ ክርስቲያን ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን የሉቃስን ወንጌል አንድ ላይ ሲያጠና በአባላቱ መካከል ስለ ንስሐ ምንነት ከባድ ውይይት ተደረገ። አንዳንዶች የዳንነው በእምነት በኩል በጸጋ ብቻ ስለሆነ ንስሐ ከእምነት የተለየ ነው ማለት ስህተት ነው ብለው ይከራከሩ ጀመር። አንድ ሰው ሲመለስ እና በኢየሱስ በሚያምንበት ጊዜ ንስሐ በዚያ መመለስ ውስጥ እንዳለ ይከራከራሉ። ሌሎች ደግሞ ንስሐ ከእምነት በፊት የነበረ የተለየ ተግባር ነው ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ጊዜ ባለፈ ቁጥር ጥያቄውን በትክክል ባለመረዳታቸውና አልፎ ተርፎም የክርክሩን አስፈላጊነት ባለመገንዘባቸው ግራ መጋባታቸው እየጨመረ መጥቷል። እንግዲህ አንተ እነዚህን ጉዳዮች እንዲረዱ እንድትረዳቸው ብትመደብ ምን ታስተምራቸው እና ምን ታደርግ ነበር? ምልክት ከሌለ መዳን የለም እግዚአብሔር ወደ ቤተክርስቲያናችሁ በመጣው በአዲሱ የወጣቶች አገልጋይ በኩል በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ ይመስላል። በቤተክርስቲያኒቱ የአገልግሎት ዝግጅቶች ላይ ብዙ ልጆች እየመጡ ነው፤ ብዙ ወጣቶች በቤተክርስቲያኒቱ በተዘጋጁ የተለያዩ የአምልኮ ኮንሰርቶች እና የስብከተ ወንጌል ስብሰባዎች ላይ ጌታን እየተቀበሉ ነው። ቁጥራቸው እየበዛ በሄደ ቁጥር ብዙዎቹ ልጆች ከጌታ ውጪ ለሆነ ለሌላ ዓላማ እዚያ እንዳሉ ይሰማቸው ጀመር። ብዙ ልጆች አለባበሳቸው ተመሳሳይ ሆነ፣ ብዙዎች ማጨስ ጀመሩ፣ አንዳንዶቹም እንዲያውም ሱስ ጀማመሩ፣ ሌሎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተለወጡ። ስለተፈጠረው ነገር ምን እንደምታስብ ብትጠየቅ የለውጡን ጉዳዮች ከወጣት አገልግሎት መሪው ጋር እንዴት መፍታት ይቻላል?
የተማሪው ትግበራ እና አንድምታዎች
3
ጥናቶች
1
2
Made with FlippingBook - Online magazine maker