Conversion and Calling, Amharic Student Workbook

8 8 /

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል? በቅርቡ ሦስት ወጣቶች በአካባቢው ያሉ ወጣቶች በሚሰበሰቡበት መናፈሻ ውስጥ ክርስቶስን ለመቀበል ጸለዩ። ይህ ቡድን የበታች ስለሚባሉት ዘሮች በተለይም ለጥቁሮች እና ሂስፓኒኮች ያላቸው አመለካከት ቀና አይደለም። ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ አንድ ሰው እነዚህ ልጆች ወደ ቤተ ክርስቲያን እና ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሕብረቶች እየመጡ በመሆናቸው በልጆቹ ሕይወት ላይ እውነተኛ ለውጦችን ያስተውላል። ነገር ግን በየጊዜው አልፎ አልፎ አንዳንድ የጭፍን ጥላቻ እና የዘረኝነት አመለካከቶች እንዳሉባቸው ይገነዘባል። ከዚህ ባህሪያቸው የተነሳ በአካሉ ውስጥ ያሉ አንዳንዶች ስለመዳናቸው ይጠራጠራሉ፥ ሌሎች ደግሞ እግዚአብሔር በሕይወታቸው እየሰራ እንደሆነና በክርስቶስ እያደጉ በሄዱ ቁጥር ይበልጥ እያገለገሉ እንደሚቀጥሉ ይከራከራሉ። በነዚህ ወጣቶች ህይወት ውስጥ ምን አይነት ለውጥ መጠበቅ እንችላለን? ይህስ ለውጥ ጊዜ የሚወስድ ከሆነ የዘር ጥላቻን በተመለከተ ካለፈው ህይወት ባርነት ለመላቀቅ ምን ያህል ጊዜ ይፈጅባቸዋል? “እንዲህ ማድረግ ምቾት አይሰጠኝም.” የአንድ ህብረት አዳዲስ አባላት ላይ በተደረገው ጥናት ውስጥ አንዲት እህት በየሳምንቱ ባደባባይ ለመጸለይ እንደምትቸገር ታውቋል። ዓይናፋር ነች፣ ብቻዋን መጸለይ ትወዳለች ነገር ግን በሌሎች ሰዎች ፊት ጮክ ብሎ የመጸለይ ላይ ችግር አለባት። ጮክ ብሎ መጸለይም ያን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አታምንም። “ኢየሱስ ወደ ጓዳ ገብተን ብቻችንን እንድንጸልይ አልነገረንም? ታዲያ ከሌሎች ጋር ጮክ ብሎ መጸለይ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?” በማለት ትሟገታለች። ይህች እህት ጸሎት በእውነት ከዳኑ ሰዎች ሁሉ ልንጠብቀው የሚገባን አንዱ የመለወጥ ምልክት መሆኑን እንድትረዳ ምን የተለየ ምክር ትሰጣታለህ? ለእርሷስ ይህንን እንዴት በይፋ ማድረግ እንዳለባት መማር ያን ያህል አስፈላጊ ነውን? እርሷ ባደባባይ መጸለይን ባትቀበል ይህ ምናልባት አልዳነች እንደሆን ይጠቁማል? ለምን? የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሚለውጥ ቃል ነው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ይህን ብርቱ ቃል ወደ ሜታኖያ እንዲመራን ይጠቀምበታል፥ ይህም ማለት ከኃጢአት ንስሐ መግባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። ይህ ቃል ወደ ንስሐ (ሜታኖያ) ድኅነት የሚያደርስና በአማኙ ላይ እምነትን (ፒስቲስ) ለማምጣት በተመሳሳይ ኃይል የሚሰራ፣ አማኙንም ከኃጢአት ቅጣት፣ ኃይል እና ህይወት የሚያድን እምነት ነው። የእግዚአብሔር ቃል አንድ ጊዜ በንስሐ እና በእምነት መስራት ከጀመረ የእግዚአብሔርን ይቅርታ እና የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በአማኙ ሕይወት ውስጥ የሚያረጋግጡ ምልክቶችን ይፈጥራል። አማኙም በውስጣዊ ማንነቱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔርን እንደ ሰማያዊ አባት ማወቅን፣ አዲስ የጸሎት ልምምድን፣ የእግዚአብሔርን ቃል መረዳትን እና የኢየሱስን ድምጽ ምሪት መከተልን ጨምሮ የአዲሱን ህይወት ምልክቶችን ያሳያል። በውጫዊውና በሚዛመደው መንገድ ደግሞ የሚለወጠው ቃል ራስን ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር መለየትን፣ አዲስ የክርስቶስን ባህሪ እና የአኗኗር ዘይቤን ማሳየትን፣ ለሌሎች አማኞች ፍቅር እና የጠፉትን ለክርስቶስ የመማረክን መሻት ጨምሮ ውጫዊ ምልክቶችን ያሳያል።

3

4

3

የትምህርቱን ንድፋዊ ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ

Made with FlippingBook - Online magazine maker