Conversion and Calling, Amharic Student Workbook

/ 9 7

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ውስጥ ያሉ እንግዶችን እና መጻተኞችን ማንነት መቀበልን ያካትታል። የደቀመዝሙርነት ጥሪ በመስዋዕትነት የክብሩ አገልጋዮች እንድንሆን እግዚአብሔር የሰጠንን ትእዛዝም ያካትታል። በዚህ ሕይወት ውስጥ የሆንነውና ያለን ሁሉ እግዚአብሔርን ለማወቅ እና በዚህ ዓለም እንደርሱ ባሪያዎቹ እንድንታወቅ የተሰጠ ነው። ለዚህ የሚጠራው ቃል የመጀመሪያ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እንድታይ ለማስቻል ነው፡- • ወደ ድነት እና ወደ መለወጥ የሚመራን ቃል ያው ቃል ለፈቃዱ ታዛዥ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሆነን እንድንኖር ደግሞ ይጠራናል። • ወደደቀመዝሙርነት የሚጠራንይህቃልእርሱን ከሁሉበላይጌታአድርገን እንድናገለግለውና ጋብቻ እና ቤተሰብን ጨምሮ ከሌሎቹ ፍቅሮች ይልቅ ከልብ እንድንወደው ራሳችንን ለኢየሱስ እንድናቀርብ ይፈልጋል። • ጥሪውበዚህ ዓለምውስጥእንደ እንግዶችናመጻተኞች በክርስቶስ ያለውን አዲሱንማንነታችንን እንድንቀበል ይጠይቀናል፤ ይህም በዚህ በዓለም ውስጥ የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች ሆነው እንደሚሰሩ የኢየሱስ ተወካይ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንድንሆን ነው። • የደቀመዝሙርነት አኗኗር የሚገለጠው ለክብሩ የመስዋዕትነት አገልጋዮች ሆነን እንድንኖር ለቀረበልን ጥሪ በጎ ምላሽ ስንሰጥ ነው። የክርስቶስ ባሪያዎች እንደመሆናችን መጠን እርሱ በሚመራው መሠረት የሆንነውን ሁሉ እናደርጋለን፤ እርሱን ማክበር እና ፈቃዱን በዓለም ላይ መፈጸም አለብን።

4

የቪዲዮ ሴግመንት 1 መግለጫ

I. እንደ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ለደቀ መዝሙርነት ተጠርተናል። የዚህ ጥሪ የመጀመሪያ ገጽታ የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅር የማግኘት የላቀው የእግዚአብሔር ሥልጣን ነው።

ሀ. ይህ ለኢየሱስ ክርስቶስ የሚኖረን ፍቅር ለትዳር እና ለቤተሰብ ካለን ፍቅር መላቅ አለበት።

1. ለክርስቶስ የሚኖረን ፍቅር ለወንድሞች፣ ለእህቶች እና ለወላጆች ካለን ፍቅር በላይ መሆን አለበት፣ ማቴ. 10፡34-37።

2. ለክርስቶስ ያለን ፍቅር ለትዳር ጓደኛ እና ለልጆች ካለን ፍቅር በላይ መሆን አለበት።

ሀ. ማቴ. 10.37

ለ. ሉቃ 14፡26

Made with FlippingBook - Online magazine maker