Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
Animated publication
ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ
T H E U R B A N M I N I S T RY I N S T I T U T E a m i n i s t r y o f WO R L D I M PA C T, I N C .
የክርስቲያን ሚሽን መሰረቶች
ሪ
ማ
ው
ተ
የ
መ
ፍ
ል
ሐ
መ
ጽ
ጃ
መ
ሞጁል 4 ኧርባን ሚሽን
የ ተ ማ ሪ ው መ ል መ ጃ መ ጽ ሐ ፍ
የክርስቲያን ሚሽን መሰረቶች
ሞጁል 4
ኧርባን ሚሽን
የክርስቲያን ሚሽን ራዕይና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት - ክፍል 1
የክርስቲያን ሚሽን ራዕይና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት - ክፍል 2
ክርስቲያን ሚሽን እና ከተማ
ክርስቲያን ሚሽን እና ድሆች
ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል ፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከመምህርህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡ ፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና Www.tumi.org/license ን ጎብኝ፡፡
ካፕስቶን ሞጁል 4: - የክርስቲያን ሚሽን መሠረቶች የተማሪው መልመጃ መጽሐፍ ISBN: 978-1-62932-229-2
© 2005, 2011, 2013, 2015. The Urban Ministry Institute. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው. የመጀመሪያ እትም 2005 ፣ ሁለተኛ እትም 2011 ፣ ሦስተኛው እትም 2013 ፣ አራተኛ እትም 2015 ፡፡
በ 1976 የቅጂ መብት ሕግ ወይም ከአሳታሚው በፅሁፍ ከሚፈቀደው በስተቀር የእነዚህን መማሪያ ቁሳቁሶች መቅዳት፣ እንደገና ማሰራጨት እና / ወይም መሸጥ ወይም በማንኛውንም ያልተፈቀደ መንገድ ማስተላለፍ የተከለከለ ነው ፡፡ የፍቃድ ጥያቄዎች በሚከተለው አድራሻ መቅረብ አለባቸው፥ The Urban Ministry Institute ፣ 3701 E. 13th Street, Wichita, KS 67208.
The Urban Ministry Institute የWorld Impact አገልግሎት ነው የሚተረጉምበት ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስ እዚህ ላይ ተለይቶ ይታወቃል።
ይዘት
የኮርሱ አጠቃላይ እይታ
3 5 7
ስለ ጸሐፊው
የሞጁሉ (የትምህርቱ) መግቢያ
የኮርሱ መስፈርቶች
13 ትምህርት 1
1
የክርስቲያን ሚሽን ራዕይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት - ክፍል 1
55 ትምህርት 2
2
የክርስቲያን ሚሽን ራዕይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት - ክፍል 2
105 ትምህርት 3
3
ክርስቲያን ሚሽን እና ከተማ
153 ትምህርት 4
4
ክርስቲያን ሚሽን እና ድሆች
199
አባሪዎች
/ 3
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ስለ ጸሐፊው
ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ የዘ አርባን ሚኒስትሪ ኢንስቲትዩት ሥራ አስፈፃሚ እና የዎርልድ ኢምፓክት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው ፡፡ ትምህርታቸውን በዊተን ኮሌጅ እና በዊተን ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን በቢብሊካል ስተዲስ የቢ.ኤ. (1988) እና በሲስተማቲክ ቲዎሎጂ የኤም.ኤ (1989) ዲግሪዎችን በቅደም ተከተል ማግኘት ችለዋል ፡፡ በተጨማሪም ከአዮዋ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን በሃይማኖት ጥናት (ሥነ-መለኮት እና ሥነ-ምግባር) ፒኤችዲ አግኝተዋል ፡፡ የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር እና የዎርልድ ኢምፓክት ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንደመሆናቸው መጠን የከተማ ሚስዮናውያንን ፣ የቤተ ክርስቲያን ተካዮችን እና የከተማ መጋቢያን ሥልጠናን በበላይነት የሚቆጣጠሩና የሚመሩ ሲሆን ለከተሞች ክርስቲያን ሠራተኞች በስብከተ ወንጌል ፣ በቤተ ክርስቲያን እድገት እና በተቀዳሚ ተልእኮዎች የሥልጠና ዕድሎችን ያስተባብራሉ ፡፡ በተጨማሪም የተቋሙን ሰፊ የርቀት ትምህርት መርሃግብሮች ይመራሉ እንዲሁም እንደ ፕሪዝን ፌሎውሺፕ ፣ ኢቫንጀሊካል ፍሪ ቸርች ኦፍ አሜሪካ ላሉት ድርጅቶች እና ቤተ እምነቶች የአመራር ልማት እድሎችን ያመቻቻሉ ፡፡ የበርካታ የማስተማር እና የአካዳሚክ ሽልማቶች ባለቤቱ ዶ/ር ዴቪስ በበርካታ ዕውቅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሮፌሰር እና የፋኩልቲ አባል ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በሃይማኖት ትምህርቶች፣ ሥነ መለኮት ፣ ፍልስፍና እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች (ቢብሊካል ስተዲስ ) እንደ ዊተን ኮሌጅ ፣ ሴንት አምብሮስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሂዩስተን ድህረ ምረቃ የሥነ-መለኮት ትምህርት ቤት ፣ በአዮዋ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን ፣ በሮበርት ኢ ዌበር ኢንስቲትዩት ኦፍ ዎርሺፕ ስተዲስ ባሉ የትምህርት ተቋማት ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡ የከተማ መሪዎችን ለማስታጠቅ በርካታ መጻሕፍትን ፣ ሥርዓተ-ትምህርቶችን እና የጥናት ጽሑፎችን አዘጋጅተዋል ፣ ከነዚህም ውስጥ የ ‹ካፕስቶን› ሥርዓተ ትምህርት ፣ የ TUMI ፕሪሚየር ሲክስቲን ሞጁል ዲስታንስ ኤጁኬሽን ሴሚናሪ ኢንስትራክሽን፥ የከተሞች አብያተ ክርስቲያናት ታሪካዊቷን የኦርቶዶክስ እምነት እንደገና በማደስ ራሳቸው እንዴት ሊታደሱ እንደሚችሉ የሚያትተው ሴክርድ ሩትስ፡ ኤ ፕሪሚየር ኦን ሪትራይቪንግ ዘ ግሬት ትራዲሽን እና ብላክ ኤንድ ሂዩማን፡ ሪዲስከቨሪንግ ኪንግ አስ ኤ ሪሶርስ ፎር ብላክ ትዎሎጂ ኤንድ ኤቲክስ ተጠቃሾች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ዴቪስ እንደ ስታሊ ሌክቸር ሲሪስ ባሉ ትምህርታዊ ጉባኤዎች፣ እንደ ፕሮሚስ ኪፐርስ ራሊስ ባሉ የተሃድሶ ኮንፈረንሶች እና እንደ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኒያ ሊቭድ ቲዎሎጂ ፕሮጄክት ሲሪስ ባሉ ሥነ-መለኮታዊ ጥምረቶች ተሳትፈዋል ፡፡ ዶ/ር ዴቪስ በ 2009 ከአዮዋ ዩኒቨርስቲ የሊበራል አርትስ እና ሳይንስ ኮሌጅ የአልሙናይ የክብር ሽልማት ያገኙ ሲሆን በተጨማሪም የዘ ሶሳይቲ ኦፍ ቢብሊካል ሊትሬቸር እና ዘ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ ሪሊጅን አባል ናቸው ፡፡
/ 5
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የሞጁሉ (የትምህርቱ) መግቢያ
ኃያል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለእናንተ ይሁን፥
የሚሽን/ተልእኮ ጽንሰ ሃሳብ በከተማ አብያተ ክርስቲያኖቻችን ዘንድ ሊኖረው የሚገባውን ያህል ትኩረት ሲያገኝ አንመለከትም፡፡ ከውቅያኖስ ማዶ ተሻግሮ በሁሉም የዓለም ማዕዘናት ውስጥ እንዳለ ሥራ በስፋት ከተመለከትነው ፣ ለሚሽን የሚገባውን ዓይነት ትንታኔ ለመስጠት አለመቻላችንን እንረዳለን ፡፡ በአንድ በኩል የክርስትና እምነት በጥቅሉ እንደ ተልእኮው ምላሽ ተደርጎ ሊታይ ይችላል፣ ይህም ምላሽ ወደ አሕዛብ ሄዶ የናዝሬቱ የኢየሱስን የእግዚአብሔር መንግሥት ጌትነት እና ንግስና ለማወጅ የተደረገው ጥሪ ምላሽ ተደርጎ ሊታይ ይችላል ፡፡ አዲስ ኪዳን በክርስትና እምነት ውስጥ ፈር ቀዳጅና ዋና ሚስዮናውያን በነበሩ ሐዋርያት ለተመሰረቱት አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠ የሚስዮናዊ ሰነዶች ስብስብ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ራሱ በክርስቶስ በኩል ወደ ዓለም በመምጣትና ዓለምን ከራሱ ጋር በማስታረቅ የመጀመሪያው ሚስዮናዊ ነው (2 ቆሮ. 5፥18-21)፤ በእርግጥም ክርስትና ተልእኮ ነው ፡፡ በመሆኑም ይህ ሞጁል ከዚህ ቁልፍ ርዕሰ-ጉዳይ ጋር ይዛመዳል ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንጻር የሚሽንን ሥነ-መለኮት እና ጉዳቶቹንም ለመረዳት ይረዳሃል ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የእግዚአብሔርን አጠቃላይ አላማና ተግባር ሳንረዳ እግዚአብሔር በዓለም ውስጥ በሚሽን አማካኝነት ምን እየሰራ እንዳለ ልንረዳ አንችልም። ስለዚህ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ትምህርቶቻችን ሚሽንን በአራት የተለያዩ መነጽሮች እንመለከታለን - ሚሽንን እንደ ትእይንት እና ተስፋ ፣ ሚሽንን እንደ ፍቅር እና ጦርነት በቅደም ተከተል እንመለከታለን ፡፡ የክርስቲያን ሚሽን ራዕይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት - ክፍል አንድ በተሰኘው የመጀመሪያው ትምህርታችን ውስጥሚሽንን እንደ ዘወትር ድራማወይም ክስተት የሚያየውን ምልከታ እንዳስሳለን ፡፡ እዚህ ላይ ዓላማችን የሚሽንን ተግባር ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር ለመረዳት የሚያስችለውን ማዕቀፍ ለማቅረብ ነው ፡፡ ስለ ሚሽን አጠቃላይ ፍቺ በመስጠት እንጀምራለን ከዚያም ስለ ሚሽን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤ ጠቅለል ያለ ሃሳብ ይዘረዘራል ፡፡ ሚሽን በታሪክ ውስጥ እና በየዘመናቱ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ለሰው ልጆች ቤዛነትን ለማምጣት የተጠቀመበት መሳሪያ መሆኑን ከቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቀስ ሚሽንን በታሪክ እና በድራማ መነፅር እንመለከታለን። የክርስቲያን ሚሽን ራዕይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት - ክፍል ሁለት በተሰኘው የሁለተኛው ትምህርታችን ውስጥ ደግሞሚሽንን እንደ ዘመናት ፍቅር እና እንደ አመፀኞ ጦርነት እንመረምራለን ፡፡ እነዚህ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙት ምስሎች እንደ አማኞች ለሥነ-መለኮታዊ መረዳታችን ሚሽን ምን ያህል ወሳኝ እንደ ሆነ እንድንመለከት ያስችሉናል ፡፡ እግዚአብሔር ከፍቅሩ የተነሳ ለእርሱ ርስት የሚሆንን ህዝብ ከዓለም ለመጥራት ያለውን የእግዚአብሔርን ቁርጠኝነት እናያለን ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ሚስት ከተሳለው የእስራኤል ታሪክ በመጀመር በጣዖት አምልኮ እና ባለመታዘዝ የሚቀጥለውን የዚህን ታላቅ ታሪክ ዋና ጭብጥ እንገመግማለን ፡፡ ይህንን ጭብጥ በኢየሱስ ማንነት ውስጥ እንመለከታለን ፣ ከዚያም አዲሱ ቃል ኪዳን የእግዚአብሔርን ሰዎች አህዛብን እንዴት እንዳካተተ እንመለከታለን ፡፡ የዘመናት ጦርነትን በተመለከተ ደግሞ በናዝሬቱ በኢየሱስ ሰውነት በኩል የእግዚአብሔርን መንግሥት አገዛዝ መታወጅ እንመለከታለን ፡፡ ከእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ግልፅ ማረጋገጫ በመጀመር ፣ እግዚአብሔር በሀጢአት፣ በዲያቢሎስ እና በሰው ልጆች ዓመፅ ከፀጋው የወደቀውን ፍጥረቱን እንደገና ለማቋቋም እንደወሰነ እናያለን ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር
6 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
አጽናፈ ዓለሙን በራሱ አገዛዝ ሥር ለማስመለስ የጦረኛ ቦታን ወስዷል። በናዝሬቱ በኢየሱስ ሰውነት አማካኝነት እግዚአብሔር በአጽናፈ ሰማይ ላይ የመግዛት መብቱን እያረጋገጠ ነው ፣ ሚሽኑም/ ተልእኮው ያ መንግሥት ነው ፡ ክርስቲያን ሚሽን እና ከተማ በተሰኘው ሶስተኛው ትምህርት ውስጥ ትኩረታችንን ወደ ሚሽኑ ዓላማ እና እግዚአብሔር ለከተማ እና ለድሆች ወዳለው ዓላማ እናዞራለን ፡፡ ጥንታዊቷን ከተማ ፣ አደረጃጀቷን እና ባህሪያቷን በተለይም በጌታ ላይ የማመፅ ምልክት ምሳሌያዊ ባህሪዋን በመመልከት እንጀምራለን ፡፡ የከተማን መንፈሳዊ ጠቀሜታ እንመለከታለን ፣ እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከበርካታ ከተሞች ጋር ያለውን መስተጋብር በመመልከት ትርጉማቸውን እንመረምራለን ፡፡ እግዚአብሔር የከተማን ፅንሰ-ሀሳብ ለራሱ ዓላማ እንዴት እንደ ተቀበለ ፣ ከአመፅ እና ከጣዖት አምልኮ ጋር ያለውን ትስስር በመሻር ፣ ለሚሽን እና ለወደፊቱ የመንግሥቱ ክብር እንዴት እንደዋጀ እንመለከታለን ፡፡ ስለዚህ በዚህ ትምህርት ውስጥ በከተማሚሽን ውስጥ ለመሳተፋችን ምክንያቶችን እናቀርባለን ፡፡ እንደ ተጽዕኖ ፣ ኃይል እና መንፈሳዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለተጨቆኑ ፣ ለተጠቁ እና ለድሆች መሸሸጊያ እንደመሆናችን መጠን እኛ የ 21ኛው ክፍለ ዘመን ደቀመዛሙርት ለከተማው በትንቢታዊ መልክ ለመናገርና ለመኖር መጣር አለብን ፡፡ የመንፈሳዊ መዳረሻችን እና የውርሳችን ሥዕል እና ምልክት እንደመሆኑ መጠን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ባሉ ከተሞች ውስጥ ወንጌልን ለመስበክ ፣ ደቀ መዝሙሮችን ለማፍራት እና አብያተ ክርስቲያናትን ለመትከል የተቻለንን ሁሉ ማድረግ አለብን ፡፡ በመጨረሻም ፣ በክፍል አራት ውስጥ ሌላ የክርስቲያን ሚሽን ወሳኝ አካል እንመለከታለን ፡፡ ክርስቲያን ሚሽን እና ድሆች በተሰኘው ትምህርት ውስጥ ስለ ድሆች እና ሚሽን ፅንሰ-ሀሳብ በበለፀገው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሻሎም ወይም ምሉዕነት ፅንሰ-ሀሳብ መነፅር እንመረምራለን ፡፡ እንደ ያህዌ የቃል ኪዳን ማህበረሰብ ፣ የእስራኤል ህዝብ ድህነትን በፍትህ እና በጽድቅ በሚተካ ለጌታ ቃልኪዳን በእንደዚህ ያለ ታማኝነት እንዲኖሩ ተጠርተዋል። በዘፀአት ወቅት እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብፅ ነፃ በማውጣቱ እውነታ ላይ በመመስረት ለቃል ኪዳን ሕዝቡ የድህነትና የጭቆና ችግርን የሚቀርፍ ንድፍ አውጥቷል ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ታጥቀን መሲህ እና የቤተክርስቲያን ራስ የሆነው ኢየሱስ ለድሆች ፍትህ እና ሰላም የሚያመጣውን መሲሃዊ ትንቢት እንዴት እንደሚፈጽም እንመለከታለን ፡፡ ኢየሱስ ጌታ እና የቤተክርስቲያን ራስ እንደመሆኑ መጠን ለእግዚአብሔር ህዝብ እና በሕዝቦቹ በኩል ለዓለም ሰላም/ሻሎም የሆነውን የእግዚአብሔርን ተልእኮ/ሚሽን መግለጹን ቀጥሏል ፡፡ የእግዚአብሔር አዲስ የቃል ኪዳን ማህበረሰብ የሆነችው ቤተክርስቲያን በኢየሱስ በማመን በሰላም ውስጥ እንድትኖርና ለራሷ አባላት እና በዓለም ላሉ የተጨቆኑ ሰዎች የእግዚአብሔርን ፍትህ ለማሳየት ተጠርታለች ፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው በአሁኑ ዘመን ለእግዚአብሔር ህዝብ ኃይልን በሚሰጥና በሚያስታጥቅ መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ አማኞች እንደመሆናችን መጠን እያንዳንዳችንና እያንዳንዱ ጉባኤ ፣ እርሱ ባስቀመጠን ስፍራ የእግዚአብሔርን እውነት በማወጅ እና በመኖር ሌሎችን እንድንዋጅ ነው ፡፡ በእውነት ክርስቲያን መሆን ሚሽን-ተኮር እና ሚሽን ላይ መመስረት ነው ፤ እኛ ከወልድ ጋር ዓለምን የማሸነፍን ሚሽን ከእግዚአብሔር ጋር አብረን እንድንሠራ ከላይ ተወልደናል (ሐዋ ሥራ 9.15) ፡፡ የእግዚአብሔርን አስደናቂ የክብር ታሪክ እና በልጁ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ዓለምን ወደራሱ በመጠቅለል ሚሽን ውስጥ አንተ የራስህን ድርሻ ትወጣ ዘንድ እግዚአብሔር ይህንን ጥናት ይጠቀም ዘንድ እመኛለሁ!
- ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ
/ 7
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የኮርሱ መስፈርቶች
• መጽሐፍ ቅዱስ (ለዚህ ትምህርት ዓላማ ሲባል የአንተ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መሆን አለበት [ለምሳሌ NIV, NASB, RSV, KJV, NKJV, ወዘተ] እና የትርጓሜ ሐረግ መሆን የለበትም [ለምሳሌ The Living Bible, The Message] • እያንዳንዱ የካፕስቶን ሞጁል በሙሉ ትምህርቱ የሚነበቡ እና የሚያወያዩ የመማሪያ መጽሀፎችን አካትቷል ፡፡ እነዚህን ከመምህርህ እና አብረው ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን እንድታነብ፣ እንድታሰላስል እና እንድትመልስ እናበረታታሃለን ፡፡ እነዚህ ጽሑፎች በበቂ ሁነታ መገኘት ባለመቻላቸው ምክንያት (ለምሳሌ ፣ በቂ የመጻሕፍቱ ሕትመት ካለመኖሩ የተነሳ) የካፕስቶን አስፈላጊ የመማሪያ መጽሐፍ ዝርዝራችንን በድረ-ገፃችን ላይ እናስቀምጣለን። የዚህን መጽሐፍ (ሞጁል) ጽሑፎች ወቅታዊ ዝርዝር ለማግኘት እባክህን www.tumi.org/booksን ጎብኝ። • የክፍል ውስጥ ሥራዎችን ለመስራት እና ማስታወሻዎችን ለመውሰድ ወረቀት እና ብዕር ፡፡ • Erickson, Millard J. Introducing Christian Doctrine. 2nd. ed. Grand Rapids: Baker Book House, 2001. • Phillips, Keith. Out of Ashes. Los Angeles: World Impact Press, 1996. • Winter, Ralph D, and Steven C. Hawthorne, eds. Perspectives on the World Christian Movement: A Reader. 3rd. ed. Pasadena: William Carey Library, 1992. • Yohannan, K. P. Revolution in World Mission. Carrollton, TX: GFA Books (a division of Gospel for Asia), 2004.
አስፈላጊ መጻሕፍት እና ቁሳቁሶች
የተጠቆሙ ንባቦች
8 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የግምገማዎች እና የምዘናዎች ድምር ውጤት በክፍል መገኘት እና የክፍል ውስጥ ተሳትፎ
የኮርሱ መስፈርቶች
30% 90 ነጥቦች
ፈተናዎች
10% 30 ነጥቦች
የቃል ጥናት ጥቅሶች
15% 45 ነጥቦች
የእክሴጀሲስ (የመፀሀፍ ቅዱስ ክፍሎች ትርጉም) ፕሮጀክት
15% 45 ነጥቦች
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት
10% 30 ነጥቦች
ንባቦች እና የቤት ስራዎች
10% 30 ነጥቦች
የማጠቃለያ ፈተና
10% 30 ነጥቦች
ጠቅላላ ድምር: 100% 300 ነጥቦች
አጠቃላይ ውጤት መመዘኛ መስፈርቶች በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ መገኘት የኮርሱ ቅድመ ሁኔታ ነው ፡፡ መቅረት በውጤትህ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል። በአስገዳጅ ምክንያት መቅረት ግድ በሚሆንበት ጊዜ እባክህ አስቀድመህ ለመምህርህ አሳውቅ ፡፡ ያመለጠህ ክፍለ ጊዜ ሲያጋጥም ያመለጠህን የቤት ሥራ መስራት እና ስለዘገየህበት ሁኔታ ከመምህሩ ጋር መነጋገር የአንተ ኃላፊነት ነው። ይህ ኮርስ ባብዛኛው በውይይት መልክ የሚካሄድ እንደመሆኑ መጠን የአንተ ንቁ ተሳትፎ በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የሚፈለግና የሚጠበቅ ይሆናል። እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚጀምረው ካለፈው ትምህርት መሠረታዊ በሆኑት ሀሳቦች ላይ በተመሰረተ አጭር ፈተና ይሆናል። ለፈተናው ለመዘጋጀት ደግሞ የተሻለው መንገድ ባለፈው ትምህርት ወቅት የተወሰዱ የተማሪውን መልመጃ (Student Workbook) እና የክፍል ማስታወሻዎችን መከለስ ነው ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አማኝ እና መሪ እንደመሆንህ መጠን በቃልህ ያጠናኸው ጥቅስ(ቃል) ለህይወትህ እና ለአገልግሎትህ መሰረት ነው ፡፡ በአንጻራዊነት ጥቅሶቹ ከቁጥር አንጻር ጥቂት ቢሆኑም በይዘታቸው ግን ጠቀሜታቸው የጎላ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የተሰጡትን ጥቅሶች (በቃል ወይም በፅሁፍ) ለመምህርህ እንድትናገር ወይም እንድታነብብ ይጠበቅብሃል ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች ለተጠሩበት የአገልግሎት ድርሻ ሁሉ ለማስታጠቅ የእግዚአብሔር ልዩ መሳሪያ ናቸው (2 ጢሞ. 3.16-17) ፡፡ ለዚህ ኮርስ የሚያስፈልጉትን መመዘኛዎች ለማጠናቀቅ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመምረጥ በንባቡ ላይ ተግባራዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ማለትም ፣ የትርጓሜ ጥናት) ማድረግ አለብህ ፡፡ ጥናቱ አምስት ገጾች ርዝመት ሊኖረው ይገባል (በድርብ የተከፋፈለ ፣ ታይፕ የተደረገ ወይም በጥሩ ሁኔታ በእጅ የተፃፈ) እና በዚህ ትምህርት ውስጥ ጎላ ብለው ከተነሱት የክርስቲያን ሚሽን መሠረተ-ትምህርቶች እና መርሆዎች
በክፍል መገኘት እና የክፍል ውስጥ ተሳትፎ
ፈተናዎች
የቃል ጥናት ጥቅስ
የእክሴጀሲስ ፕሮጀክት(የመፀሀፍ ቅዱስ ክፍሎች ትርጉም)
/ 9
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ውስጥ አንዱ ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል፡፡ ፍላጎታችን እና ተስፋችን ቅዱሳት መጻሕፍት የአንተን እና የምታገለግላቸውን ሰዎች ሕይወት በተጨባጭ ለመለወጥ ያላቸውን አቅም እንድትረዳ ነው። ኮርሱን በምትወስድበት ጊዜ የበለጠ ለማጥናት በምትፈልገው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ የንባብ ክፍል (በግምት ከ4-9 ቁጥሮች) ለማጥናት አታመንታ፡፡ የፕሮጀክቱ ዝርዝሮች በገጽ 10-11 ላይ የተካተቱ ሲሆን በዚህ ትምህርት መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ እኛ የምንጠብቀው ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሕይወታቸው ውስጥ እና በአገልግሎት ድርሻቸው ላይ በተጨባጭ እንዲተገብሩት ነው ፡፡ ተማሪው የተማራቸውን መርሆዎች ከተግባራዊ አገልግሎት ጋር አጣምሮ የሚኒስትሪ ኘሮጀክት የማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት ፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዝርዝሮች በገጽ 12 ላይ የተገለጡ ሲሆን በትምህርቱ መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ የክፍል ሥራ እና የተለያዩ ዓይነት የቤት ሥራዎች በክፍል ትምህርት ወቅት በመምህርህ ሊሰጡህ ወይም በተማሪው መልመጃ (Student Workbook) ውስጥ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ ስለሚፈለገው ነገርም ሆነ የቤት ስራ ስለ ማስረከቢያው ጊዜ ጥያቄ ካለህ መምህርህን ጠይቅ። ለክፍል ውይይት ለመዘጋጀት ተማሪው የተመደበውን ንባብ ከጽሑፉ እና ከቅዱሳት መጻሕፍት ማንበቡ አስፈላጊ ነው ፡፡ እባክህ በየሳምንቱ ከአንተ የተማሪው የመልመጃ መጽሐፍ ውስጥ “የንባብ ማጠናቀቂያ ቅጽ” ን ተመልከት። ለሚደረጉ ተጨማሪ ንባቦች ተጨማሪ ዋጋ/ነጥብ የማግኘት እድል ይኖራል ፡፡ በትምህርቱ መጨረሻ ላይ መምህርህ በቤት ውስጥ የሚጠናቀቅ የመጨረሻ ፈተና (የተዘጋጀ ጥራዝ) ይሰጥሃል። በትምህርቱ ውስጥ የተማርከውን እና በአገልግሎትህ ላይ ያለህን አስተሳሰብ ወይም አሠራር እንዴት እንደሚቀይረው አንድታሰላስል የሚረዳ ጥያቄ ትጠየቃለህ፡፡ ስለ መጨረሻው ፈተና እና ሌሎች ጉዳዮች መምህርህ አስፈላጊውን መረጃዎች ይሰጥሃል።
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት
የክፍል እና የቤት ሥራ ምደባዎች
ንባቦች
ከቤት-የሚሰራ የማጠቃለያ ፈተና
ውጤት አሰጥጥ የሚከተሉት ውጤቶች በክፍለ-ጊዜው መጨረሻ ላይ በዚህ ክፍል ውስጥ ይሰጣሉ እናም በእያንዳንዱ ተማሪ መዝገብ ላይ ይቀመጣሉ።
A - የላቀ ሥራ
D - የማለፊያ ሥራ
B - በጣም ጥሩ ሥራ
F - አጥጋቢ ያልሆነ ሥራ
C - አጥጋቢ ሥራ
I - ያልተሟላ
ለእያንዳንዱ የመጨረሻ ክፍል አግባብነት ያላቸው ውጤቶች ይሰጣቸዋል ፣ ለእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚሰጠው የክፍል ነጥብ በጠቅላላው አማካይነት ውጤት ላይ የሚታሰብ ይሆናል። ያልተፈቀደ የስራ መዘግየት ወይም ሥራዎችን አለማስረከብ በውጤትህ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ፣ ስለሆነም እባክህ አስቀድመህ አቅደህ ከመምህርህ ጋር ተነጋገር።
1 0 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የኤክሴጄሲስ ፕሮጀክት(የመ.ቅዱስ ክፍሎች ትርጉም) በካፕስቶን ፋውንዴሽን የክርስቲያናዊሚሽን የጥናትሞጁል ተሳታፊ እንደመሆንህ መጠን ከሚከተሉት ንባቦች በአንዱ ላይ የክርስቲያን ሚሽን እና የከተማ አገልግሎት ምንነት ላይ ኤክሴጄሲስ (ኢንደክቲቭ ጥናት) እንድትሰራ ትጠየቃለህ። ማቴ 28.18-20 A2 ቆሮንቶስ 6.1-10 ሉቃስ 4.16-22 A2 ጢሞቴዎስ 4.1-5 ማቴዎስ 5.13-16 ቆላስይስ 1.24-29 የዚህ የትርጓሜ ፕሮጀክት (እክሴጀሲስ) ዓላማ ስለ ክርስቲያናዊ ሚሽን ምንነት እና አሠራር የዋና ምንባብ ዝርዝር ጥናት ለማካሄድ እድል ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሚሽነሪ አምላክ መሆኑን ማየት ለእያንዳንዱ የከተማ አገልግሎት ደረጃ መሠረታዊ ነው፡፡ ሚሽን ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ወደ ባህር ማዶ ሄደው ለተወሰነ ወቅት ብቻ የሚሰሩት ሥራ አይደለም፡፡ ይልቁንም ሚሽን እግዚአብሔር በዚህ ምድር ላይ የሚሰራው ስራ እስትንፋስና የአይሁድ-ክርስቲያናዊ የዓለም ምልከታ መሰረት ነው። በአንድ በኩል ጠቅላላው የክርስትና ታሪክ እግዚአብሔር የርሱ የሆኑትን ከአለም ወደራሱ ለመሳብ ያደረገውን መመልከት እንችላለን፤ ሚሽን የኛ ስራ የመሆኑን ያህል የእግዚአብሔርም ስራና የልቡ ፈቃድ ነው። የዚህ ጥናት ዓላማ አንተ ከላይ ከተጠቀሱት ፅሁፎች አንዱን በመምረጥ ስለ ሚሽን - መሠረቱን ፣ አሰራሩን እና ለከተሞች ክርስቲያናዊ አመራር ያለውን ጠቀሜታ በጥልቀት ለመመልከት እንደ መነፅር እንድትጠቀምበት ነው፡፡ ከእነዚህ ንባቦች ውስጥ አንዱን ስታጠና (ወይም አንተ እና የአንተ መምህር የተስማማችሁበትን) ለክርስቲያናዊ ሚሽን መሠረት የሆነውን ቁልፍ ገጽታ እንደምትገነዘብ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን ከራስህ የግል የደቀመዝሙርነት ጉዞ ጋር እንዲሁም እግዚአብሔር በቤተክርስቲያንህ እና በአገልግሎትህ ውስጥ ከሰጠህ የመሪነት ሚና ጋር በቀጥታ እንዴት እንደምታዛምደው መንፈስ ቅዱስ ጥልቅ መረዳት እንዲሰጥህ እንመኛለን ፡፡ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት እንደመሆኑ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄሲስ) ለመስራት የጥናት ክፍሉን በአውዱ ውስጥ መረዳት ያስፈልጋል። በመቀጠልም ዋናውን ትርጉም ከተረዳህ በኋላ ለሁላችንም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መርህ ማውጣትና ይህንም በተጨባጭ ከህይወት ጋር ማዛመድ ይኖርብሃል። ይህን የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥናት በምታደርግበት ወቅት እነዚህ ሶስት ደረጃዎች ሊያግዙህ ይችላሉ:- 1. በተሰጠው ምንባብ ውስጥ ለተጠቀሱት ዋና አድማጮች እግዚአብሔር መናገር የፈለገው ምንድነው? 2. ከዚህ ምንባብ ልንማረው የምንችለውና ለሁሉም ዘመንና በየትኛውም ቦታ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ልንወስደው የምንችለው መርህ ምንድነው? 3. ዛሬምመንፈስ ቅዱስ እኔን ከተማርኩትመርህ በመነሳት ምን እንዳደርግ ነው የሚፈልግብኝ? እንግዲህ እነዚህን ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ከመለስክ በቀጣይ አሳይመንት ስራህ የግልህን መረዳት ለማቅረብ ዝግጁ ነህ ማለት ነው። አሳይመንት ስራህ ይህን ቅደም ተከተል ተከትሎ መስራት ይረዳሃል፥
ዓላማ
ዝርዝር መግለጫ እና አወቃቀር
/ 1 1
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
1. የመረጥከው የንባብ ክፍል ዋና ጭብጥ ወይም ሃሳብ ምን እንደሆነ ለይተህ አስቀምጥ። 2. የምንባቡን ዋና ትርጉም በአጭሩ ግለጽ (ይህን በሁለት ወይም በሶስት አንቀጽ ልታስቀምጠው ትችላለህ ወይም ደግሞ በእያንዳንዱ ቁጥር አጫጭር ማጣቀሻ ወይም ማመሳከሪያ እየተጠቀምክ መሄድ ትችላለህ።) 3. ይህ የምንባብ ክፍል ሊሰጠን የሚችሉ ከአንድ እስከ ሶስት የሚደርሱ የክርስቲያን ሚሽን መርሆዎችን ዘርዝር። 4. ከመርሆዎቹ ውስጥ አንዱ፣ የተወሰኑት ወይም በጠቅላላው ከሚከተሉት ነጥቦች ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ አሳይ፥ ሀ. ከአንተ የግል መንፈሳዊ ህይወት እና ከጌታ ጋር ካለህ ጉዞ ጋር ሐ. ባለህበት ማህበረሰብም ሆነ በጠቅላላው ህብረተሰብ ውስጥ ከሚንጸባረቁ ሁኔታዎችና ችግሮች ጋር የዚህን ትምህርት (ሞጁል) መጽሐፍ እና ማጣቀሻዎችን እንደ መመሪያና እንደ መርጃ ለመጠቀም ነጻነት ይኑርህ፤ ይህን በምታደርግበት ወቅት ግን የሌላን ሰው ምልከታ ከተዋስክ ወይም በዛ ምልከታ ላይ የራስህን ከመሰረትክ ለባለሃሳቡ ዕውቅና መስጠትን መዘንጋት የለብህም። ለዚህም የጽሁፍ ውስጥ ማጣቀሻዎችን፣ የግርጌ ማስታወሻዎችን፣ ወይም የመጨረሻ ማስታወሻዎችን ተጠቀም። የተጠቀምከው የማስታወሻ ዘዴ ተቀባይነት የሚኖረው 1) በጠቅላላው የጽሁፍ ስራህ ውስጥ ወጥነት ያለው ሲሆንና 2) የተጠቀምከውን የሌላን ሰው ሃሳብ በትክክል የሚያመለክት ሲሆንና ተገቢውን እውቅና ሲሰጥ ብቻ ነው ፡፡(ለተጨማሪ መረጃ ከአባሪዎች ገጽ ላይ Documenting Your Work : A guide to Help You Give Credit Where Credit is Due ተመልከት ፡፡) የትርጓሜ ጥናቱ (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክቱ) የሚከተሉትን መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆኑን አረጋግጥ:- • በአግባቡ መጻፉን(ታይፕ መደረጉን) • ከላይ ከተሰጡት ምንባቦች የአንዱ ጥናት መሆኑን • ሳይዘገይ በቀኑና በሰኣቱ ገቢ መደረጉን • ርዘመቱ 5 ገጽ መሆኑን • ከላይ የተሰጠውን መመሪያ ተከትሎ መሰራቱንና አንባቢው በቀላሉ ተከትሎ ሊረዳው የሚችል መሆኑን • ምንባቡ ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ያላቸውን ዝምድና የሚያሳይ መሆኑን እነዚህን መመሪያዎች አይተህ አትደናገጥ፤ ይህ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት ነው፤ ማድረግ የሚያስፈልግህ ምንባቡን በደንብ ማጥናት፤ ከምንባቡ ውስጥ ትርጉም መፈለግ፤ ከዚያም ቁልፍ የሆኑ መርሆዎችን ከምነባቡ ማውጣት እና መርሆዎቹንም ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ማዛመድ ናቸው፡፡ ለ. በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ካለህ አገልግሎት ጋር
1 2 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ምዘና
ይህ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት) የ45 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 15% ይይዛል፡፡ ስለዚህ በተቻለህ መጠን ስራህን የላቀና አስተማሪ አድርገሀ ለማቅረብ ሞክር፡፡
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤” (ዕብራውያን 4፡12)፡፡ ሐዋሪያው ያዕቆብ ሰሚዎች ብቻ ሳይሆን አድራጊዎችም ጭምር እንድንሆን አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል፡፡ ቃሉን በተግባር ላይ እንድናውለውም ይመክረናል፡፡ ይህን ልምምድ መዘንጋት የተፈጥሮ ፊታችንን በመስታውት ውስጥ ተመልክተን ወዲያው ማንነታችንን ከመርሳት ጋር ያመሳስለዋል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያደርግ ሰው በነገር ሁሉ ይባረካል (ያዕቆብ 1፡22-25)፡፡ እኛም መሻታችን የምንቀስመውን ትምህርት በግል ህይወትህ፣ በአገልግሎትህና በቤተክርስቲያንህ ውስት ካሉ ተጨባጭ ሁኔታዎችና ፍላጎቶች ጋር በማዛመድ በተግባር ስታውለው መመልከት ነው፡፡ በመሆኑም የዚህ ትምህርት (ኮርስ) ዋና ዓላማ ከዚህ ኮርስ የተማርካቸውን ነገሮች ከሌሎች ጋር ልትከፋፈልበት የምትችልበት የሚኒስትሪ ፕሮጀክት መቅረጽ እንድትችል ነው፡፡ የዚህን ጥናት መመዘኛዎች ለማሟላት ብዙ አማራጮች አሉህ፡፡ ከሰንበት ትምህርት ቤት የወጣቶች ወይም አዋቂዎች የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ወይም ማንኛውም አገልግሎት ዘርፍ ላይ ተመስርተህ አጠር ያለ ጥናት ማካሄድ ትችላለህ፡፡ እዚህ ጋር የግድ ማድረግ የሚኖርብህ ነገር ቢኖር ከነበረህ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የተማርካቸውን ነጥቦች ከአድማጭህ ጋር መወያየት ነው፡፡ (በእርግጥ የምታካፍላቸውን ነጥቦች ከትርጓሜ ጥናትህም መውሰድ ትችላለህ፡፡) በእያንዳንዱ የፕሮጀክት ስራህ ነጻነትህን ተጠቅመህ ሳቢና ግልፅ ለማድረግ ሞክር፡፡ በዚህ ኮርስ መጀመሪያ ሀሳብህን የምታካፍልበትን ሁኔታ (አውድ) በመወሰን ለመምህርህ ማሳወቅ ይኖርብሃል፡፡ ለዚህም ፕሮጀክትህ ይህን ዝርዝርና ቅደም ተከተል በመጠቀም ሊዘጋጅ ይችላል፡፡
ዓላማ
እቅድ እና ማጠቃለያ
1. ሙሉ ስም 2. የት እና ከማን ጋር የመከፋፈል ጊዜ እንደነበረህ 3. ስለነበራቹ ጊዜ ምን እንደተሰማህና ስለነሱ ምላሽ አጠር ያለ ማብራሪያ 4. ከነበራቹ ጊዜ ስለተማርከው ነገር
ምዘና
ይህ የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የ30 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 10% ይይዛል፡፡ ስለዚህ ሃሳብህን በልበ ሙሉነት ማካፈልህንና ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ማቅረብህን እርግጠኛ መሆን ይኖርብሃል፡፡
/ 1 3
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የክርስቲያን ሚሽን ራዕይ እና መጽሀፍ ቅዱሳዊ መሰረት - ክፍል 1
ት ም ህ ር ት 1
የትምህርቱ አላማ
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! በዚህ ትምህርት መጨረሻ ላይ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ • ጠቅለል ያለ “ፕሮሌጎሜና” (“የመጀመሪያ ቃል”) ወይም የሚሽንን ትልቁን ምስል ትረዳለህ፡፡ • ሚሽን “እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትና ስራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት ለሰው ልጆች ሁሉ ያዘጋጀው የድነትና የቤዛነት ዓዋጅ” እንደሆነ ትገነዘባለህ፡፡ • በክርስቶስ ኢየሱስ ሰውነትና ስራ ላይ በተመሰረተውና በምስሎች፥ በስዕሎችና በታሪኮች ውስጥ በቀረበው የታሪክ ሂደት አማካኝነት እግዚአብሔር ለፍጥረታት ሁሉ ስላለው ሚሽን በአግባቡ ትረዳለህ፡፡ • አራቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሚሽን ማዕቀፎች/ምስሎች ማስቀመጥ ትችላለህ፥ ማለትም ሚሽን እንደ ዘወትር ክስተት (በታሪኩ ውስጥ እግዚአብሔር እንደ ዋና ገፀ ባህሪ) ፤ እንደ መለኮታዊ ቃል ኪዳን ውሳኔ (የእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ኪዳን መጠበቅ)፤ እንደ ዘመናት የፍቅር ግንኙነት ( እግዚአብሔር ለተዋጀው ህዝቡ እንደ ሙሽራ) እና እንደ አማጵያን ጦርነት (እግዚአብሔር በፍጥረት አለም ላይ መንግስቱን በ ድጋሚ እንደሚመሰርት ጦረኛ)፡፡ • ከእግዚአብሔር የማይታጠፈው አላማ በመነሳት በዘወትር ክስተት ውስጥ ያሉትን ዋና ዋና ነገሮች ማሳየት ትችላለህ። ከዘመን በፊት (የእግዚአብሔር ቅድመ ህልውና እና አላማ ፣ የአመፃን ምስጢርና የኢ-ፍትሃዊነትን ኃይል የሚያሳይ)፤ የጊዜ መጀመሪያ (የአጽናፈ አለሙንና የሰው ልጅ ፍጥረትን ውድቀትና እርግማን ፕሮቶኢቫንጌሊየምን፤ የኤደን መጨረሻ፤ የሞትን አገዛዝና የመጀመሪያዎቹን የጸጋ ምልክቶች ያጠቃልላል)፤ የጊዜ መገለጥ (አብርሃማዊውን ተስፋ፣ ዘጸአትን፣ የመሬትን ምርኮ፣ የከተማ - መቅደስ - ዙፋን፣ የግዞት እና የቅሬታዎችን መመለስ ያጠቃልላል።) • ስለ ዘመን ፍጻሜ የማይታጠፈው የእግዚአብሔር ተስፋ፤ የኢየሱስን ስጋ መልበስ፤ የመንግስቱን መገለጥ፤ የኢየሱስን ህማማት፤ ሞት፤ ትንሳኤና እርገት እንደሚያጠቃልል ትገነዘባለህ፡፡ ስለመጨረሻው ዘመን ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ፤ የቤተክርስትያንን ተሀድሶ፤ የአህዛብን መካተትና የአለማቀፋዊውን ሚሽን ማጠቃለል ትረዳለህ፡፡ • እንዴት የእግዚአብሔር ኡአላዊ አላማ የሰው ልጆችን ታሪክ እንደሚጽፍ ፤ በመለኮታዊ የታሪክ ሂደት ውስጥ የእግዚአብሔር እንደ ዋና ገፀ ባህሪ መሆን፤ ሚሽን በዘመን መጀመሪያ የጠፋውን እንደማደስ ፤ እና እግዚአብሔር የሰጠንን ድርሻ ለመወጣት አህዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት በማድረግ ሚሽን እንደ ዘወትር ክስተት የሚኖረውን ምልከታ ትረዳለህ፡፡
1
1 4 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
• ሚሽንን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚያብራሩት አራት ዋነኛ ኃሳቦች ወይም ጭብጦች አንዱ ሚሽን እንደ መለኮታዊ የተስፋ ቃል ፍጻሜ የሚለው መሆኑን ትገነዘባለህ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ስናየው ቃል ኪዳን ማለት በሁለት ወገኖች መካከል በግለሰቦች፣ በጎሳዎች ወይም ህዝቦች መካከል የሚደረግ ስምምነት ሲሆን ይህም ስምምነት ለሁለቱም ወገኖች የሚገቡትን ግዴታና የሚያኙትን ጥቅም ያካትታል፡፡ • መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኪዳኖች የሚጋሯቸው የጋራ የሆኑ ባህሪያት ሲኖራቸው ይህም ውሎች እና ስምምነቶች በምስክሮች ፊት መካሄዳቸውን እና ውል መጣስ የሚያስከትለውን ውጤት (ማለትም ውሎችን መጣስ እንደ ከባድ ስነምግባራዊ ጥሰት ይቆጥራል) ያካተተ መሆኑን ትረዳለህ፡፡ ቃልኪዳኖች የሚሰጡት ስጦታ በመስጠት፣ ምግብ በመመገብና ብዙ ጊዜ ደግሞ የማስታወሻ ድንጋይ በማስቀመጥ ነው፡፡ የሚረጋገጡት ደግሞ በመስዋዕት በሚደረገግ መሃላ ነው፡፡ • ጋብቻን ጨምሮ ምናልባትም የመጽሐፍ ቅዱሳዊው ኪዳን ዋና ማሳያዎች ማጤን ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ እግዚአብሔር ከኖኅ ጋር ያደረገው ኪዳንና እግዚአብሔር በሲና ከእስራኤል ልጆች ጋር ያደረገው ኪዳን ማንሳት ትችላለህ፡፡ ስለዚህም የእግዚአብሔር ኪዳን በጠቅላላው በእግዚአብሔርና በግለሰቦች ወይም በህዝቡ መካከል በጥንቃቄ የሚደረግ ስምምነት መሆኑን ትረዳለህ፡፡ • ሚሽን እንደ መለኮታዊ የተስፋ ቃል ፍጻሜ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባውቃል ኪዳን ላይ በማስደገፍ ልታየው ትችላለህ፤ ከሀገርና ከወገኖቹ ተለይቶ መውጣቱ፣ በዚህም የተነሳ የሚያገኘው የእግዚአብሔር በረከት፤ እግዚአብሔር ታላቅ ህዝብ ያደርገዋል፤ ስሙንም ታላቅ ያደርገዋል፣ የሚባርኩትን ይባርካል፥ የሚረግሙትንም ይረግማል፣ ከእርሱም የተነሳ አህዛብን ሁሉ ይባርካል የሚለውን ሃሳብ ትረዳለህ፡፡ • እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ለአህዛብ የሚተርፍ የዘር ተስፋ የታደሰውና የተረጋገጠው በልጆቹ በይስሐቅና ያዕቆብ በኋላም መሲሁ በሚመጣበት ነገድ በይሁዳ ግልጽ ሆኖ ተለይቷል፡፡ ከይሁዳ ወገን የዳዊት ቤት ለአብርሃም የተገባው የንጉስ ዘር የሚመጣበት ለመሆን ተመርጧል፡፡ የዳዊትም ወራሽ ለዘላለም በእስራኤል ላይ ይነግሳል፣ ለአህዛብም በረከት ይሆናል፡፡ • እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዳዊት የሰጠው ተስፋ በአብርሃም ዘርነት እና የእግዚአብሔር አገዛዝ በሚመሰረትበት በዳዊት ልጅነት አማካኝነት በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት በኩል መፈጸሙን ትገነዘባለህ፡፡ በኢየሱስ ሕይወት፣ ሞት፤ ትንሳኤና እርገት በኩል ደግሞ የእግዚአብሔር ኪዳን ተፈጽሟል፡፡ • ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ኪዳኑን የመጠበቁን የምስራች ማረጋገጥና ማወጅ ሲሆን ታላቁ ተልዕኮ ደግሞ ይህን የተፈጸመ ተስፋ ከእስራኤል ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ለሰው ልጆች ሁሉ የማወጅና የማስተማር ተልዕኮ መሆኑን ትረዳለህ፡፡
1
/ 1 5
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
• በዚህ ዘመን በሚሽን ሚና እና በናዝሬቱ በኢየሱስ ፊት የአብርሃምና የዳዊት ተስፋ እንደተፈጸመ በመግለጽ መካከል ያለውን ትስስር ማሳየት ትችላለህ፤ አሁንም በተልእኮው የወንጌል አዋጅ አማካይነት ለአህዛብ በሚደረግ የመስቀሉ ስብከት በኩል የአዲሱ ሕይወት ተስፋ መሰጠቱን ትገነዘባለህ፡፡
“ሁልጊዜም የታሪክ ጊዜ ነው” የእግዚአብሔር ክብር ታሪክ እና የሚሽን ጥሪ
ጥሞና
ሮሜ 16፡25- 27 “እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥ ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።” ምናልባትም “ከእለታት አንድ ቀን” ወይም የሱ ዘመድ የሆነው “በደስታና በተድላ አብርረው ኖሩ” እንደሚሉት ሀረጎች ትኩረትን የሚስብ ላይኖር ይችላል፡፡ ብዙዎቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ የሰማናቸው ተረቶች የመጀመሪያ ሀረጎች ናቸው፡፡ እነዚህን ቃላት መስማት ወድያው ቆም ብለን ራሳችንን እንድናዞርና ታሪኩ ከየት ተነስቶ ወዴት እንደሚሄድ የማወቅ ጉጉት ይፈጥርብናል፡፡ እንግዲህ እኛ ሰዎች ሶቅራጥስ እንደሚለው ምክንያታዊ ፍጥረቶች ብቻ ሳንሆን ታሪክ ተናጋሪዎችም ጭምር ነን፡፡ ራሳችንን በምንነጋገራቸው ታሪኮች ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ሁላችንም ስለሀገራችን፣ ስለቤተሰባችን፣ ስለራሳችን በምንናገራቸው ታሪኮች ውስጥ የተሻለ የራስ ግንዛቤ እና በራስ መተማመን ይፈጥሩልናል። የታሪኮቻችን ገፀ ባህሪያት፣ ጭብጦችና ሴራዎች የምንኖርበትን እውነታ ሞራልና ዕሴቶች ይወስኑልናል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የራሱ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ሃገራዊ የፍልስፍና ታሪክ በገዛ በራሱ ታሪክ ውስጥ የሚመለከት ግለሰብ፣ ቤተሰብ፣ ጎሳ፣ ባህል ወይም ህዝብ ማግኘት እጅግ ያስቸግራል፡፡ ሆኖም ግን የእውነት የምንኖረው በምንናገራቸው፣ በምናምንባቸውና ህይወታችንን በመሰረትንባቸው ታሪኮች ውስጥ ነው፡፡ ይህ የታሪኮች ማህበራዊም ሆነ ግለሰባዊ ሚና (ታሪካዊ ወይም ልብ ወለዳዊ ሊሆኑ ይችላል) በዚህ ዘመን ባሉት አብዛኛው አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የተዘነጋ ይመስላል፡፡ ብዙውን ጊዜ በየቤተክርስቲያኖቻችን ትኩረት የምንሰጠው ለቀረበው እውነት፣ ለእምነት አቋም መግለጫዎች እና ጥሩ ተደርገው ለተዋቀሩና በቀላሉ አንብበንና ሸምድደን ለምናልፋቸው የወንጌል ታሪኮች ነው፡፡ ምንም እንኳን እንዲህ አይነቱ ስነመለኮት ጠቃሚ ቢሆንም የወንጌል ልብ ትርታና መሰረት ግን በዚህ መልክ በቀላሉ ሊጠቃለል በሚችለው በኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ የተመሰረተ ነው፡፡ ይልቁንም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ መልበስ፤ በቀራንዮ መሰቀል፤ በትንሳኤው ድል፤ በእርገቱና በአባቱ ቀኝ በመቀመጡ አማካኝነት እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ፍቅሩን የገለጸበትን ታሪክ በታላቅ ደስታ መነሳሳትና መደነቅ መናገር ይኖርብናል፡፡ በእርግጥ የኢየሱስ ክርስቶስን ሃይልና ጸጋ በእምነት መግለጫዎች ብቻ መለማመድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ቃልና በቅዱስ ቁርባንም ጭምር መጽደቅ እና መነገር ይኖርበታል። ይህን ታሪክ
1
1 6 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ደግሞ ደጋግሞ መናገር የክርስትና እምነት ባህሪይ ነው። እኛ የዳንነው “ታላቅ ደስታ” በሆነው “የምስራቹ ቃል” ላይ ህይወታችንን ስለቀረጽንና ስላጸናን ነው። የክርስቲያን ሚሽንን ተፈጥሮ ሊሰሙት ለሚገባቸው ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ መንገር ነው የሚል ትርጓሜ መስጠት አስገራሚ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሁልጊዜም ቢሆን ሚሽን ማለት ወንጌልን ወዳልሰሙት በመሄድ ለሰሚዎቹ ግልጽና ተስማሚ በሆነ መንገድ በናዝሬቱ ኢየሱስ በኩል ስለተገለጠው የእግዚአብሔር የፍቅር ቃል መንገር ነው። የሰሚዎቹን ቋንቋ፣ ባህልና ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእነርሱ ተስማሚ በሆነ መንገድ የእግዚአብሔርን የጸጋውን ወንጌል ማድረስ ያስፈልጋል። በመሆኑም ሁልጊዜም ቢሆን ሚሽን ማለት በክርስቶስ በኩል ስለ እግዚአብሔር ክብር ደግሞ ደጋግሞ መናገር ነው። ዋናው አላማ ይህን ታሪክ ላልሰሙት ሁሉ እስከ ምድር ጫፍ ድረስ በማድረስ ሰምተው የተቀበሉት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር በመታረቅ የዘላለምን ህይወት ይወርሱ ዘንድ ነው። ግልጽና ቀጥተኛ በሆነ ቋንቋ ለማስቀመጥ ያህል ከክርስቲያናዊ ሚሽን መሰረቶች አንዱን ይወክላል - የቆየውን በጣም የቆየውን የኢየሱስን እና የፍቅሩን ታሪክ መንገር። እንዳለመታደል ሆኖ በዛሬዎቹ ክርስቲያኖች ዘንድ ይህን የተከተለ የቃሉ ህይወት፣ የጌታ ኢየሱስ ወንጌል እና ይህን ታሪክ ያማከለ የሚሽን አካሄድ ችላ ተብሎ ሳይንሳዊ ዘዴን ያማከለ የሚሽን ስራ ሲተገበር ይታያል። ብዙ ክርስቲያኖች ይበልጥ ሳይንሳዊ ለሆነው ዘዴ ሲሉ ታሪክን የመንገርን ሃይል ችላ ይሉታል፤ በዚህም ምክንያት በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ በመናገር ውስጥ ያለውን ድንቅ ነገር አጥተናል። አንድ የፍልስፍና ወይም ሳይንሳዊ ጽሑፍ ሊገልጠው በማይችለው ልክ ታሪክ መናገር አንድን እውነታ በተጨባጭ የማሳየትና በአጥንት የማስቀረት አቅም አለው። በደንብ በተጠኑ ስብከቶች፣ ሳይንሳዊ ተዓማኒነትን ባተረፉ የቃሉ ትርጉም ዘዴዎች ላይ በመመርኮዝ ብዙዎች የራሳቸውን ቋንቋ በመተው ለደረቅ፣ ከአዕምሮ ለሆነና እርባና ለሌለውወንጌል ተላልፈው ተሰጥተዋል፤ እነዚህ ሰዎች ምንም እንኳን ምድራዊውን ዘዴ ቢመርጡም ያን ያህል አሳማኝ አይደለም። ታሪኩን በደንብ አድርገን መናገርን በተቃወምን መጠን የናዝሬቱ ኢየሱስን ታሪካዊ ዕውነታዎች በወንጌል “ዋና ቋንቋ” አለመግለጻችን ብቻ ሳይሆን አሳማኝም አይደለንም። እንዳብዛኛዎቹ የዘመኑ ወንጌላውያን ምሁራን ሊላንድ ራይከንም የመጽሐፍ ቅዱስን ምስላዊና ታሪካዊ የትረካ ዘዴ አስተውለዋል። የኢየሱስን መልዕክት በማስረጃ ተደግፎ እንደቀረበ ስነመለኮታዊ ሳይንስ ብቻ አድርጎ የመመልከት አደጋውን ያስረዳሉ። ክርስትያኖች መጽሐፍ ቅዱስን በማስረጃ ተደግፎ የቀረበ ስነ መለኮታዊ መመሪያ ብቻ አድርገው ከመመልከታቸው የተነሳ ወደ ስህተት ማምረታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ከማብራሪያዎቹና ከሀሳቦች ይልቅ ምስሎችና የምናባዊ ጭብጦች መጽሐፍ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ሰባኪያንና የስነ መለኮት ምሁራን በቀላሉና ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ወደ መልዕክቶች መጽሐፍት ሲሳቡ እንመለከታለን፡፡ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር እንዳሉት መጽሐፍ ቅዱስ በስፋት የሚናገረው በምስሎች አማከኝነት ነው፡፡ የመጽሀፍ ቅዱሰ ታሪኮች፤ ምሳሌዎች፤ የነቢያት ስብከቶች፤ የጥበበኞቹ ምልከታ፤ የመጪው ዘመን ምስሎች፤ ያለፉት ክስተቶች ትርጓሜዎች በሙሉ ከልምምድ በመነጩ ምስሎች ይገለጻሉ፡፡
1
~ Leland Ryken. Dictionary of Biblical Imagery. (electronic ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2000.
/ 1 7
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
1 በወንጌል ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔርን ታሪክ ግልጽና ጉልህ በሆነ መንገድ ተስሎ እንመለከታለን፤ የእግዚአብሔር በግ ለአለም ሃጥያት ምትክ መስዋዕት ሆኖ እንጨት ላይ ተንጠልጥሏል፡፡ ይህ የሞተው፤ በሶስተኛው ቀን ከሙታን የተነሳው ክርስቶስ እንደሆነ የሚያምን ከኃጥያቱ ነጻ ይወጣል፤ በዚህ አለም በሚኖረው ህይወት በውስጡ የሚኖርና በመጨረሻውም ቀን ከሙታን የሚያስነሳውን መንፈስ ቅዱስን ይቀበላል፡፡ ይህ ታሪክ ለሰው ልጆች ሁሉ ድነትና ሕይወት የምስራች እንደሆነ ለተቀበሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ጎልማሶችና ወንዶችና ሴቶች ልጆች ከ2000 አመታት በላይ ተደጋግሞ በመነገር ላይ ይገኛል፡፡ ሚሽን የዚህ ታሪክ ዋነኛ ተዋናይ ስለሆነው ስለእግዚአብሔር ፍቅርና ጸጋ ለአለም ሕዝቦች በሚረዱትና በሚያደንቁት መንገድ ታሪኩን መናገር ነው፡፡ እግዚአብሔር የራሱ ታሪክ ጀግና ነው፤ የመዳንም ታሪክ ቢሆን “ከእርሱ ታሪክ” ውጪ ምንም አይደለም፡፡ እኛም በርግጥ በእውነት ከተቀበልነው የእግዚአብሔር የፍቅር ታሪክ የእኛም የራሳችን ታሪክ ሊሆን ይችላል፡፡ የክርስትናን መልዕክት እንደ ታሪክ መልሶ ማግኘት በጣም ረጅም ጊዜ የሚፈልግ ነገር ነው፡፡ የክርስትናዊ ደቀ መዝሙርነትና የሚሽን መሰረቶችን ለመረዳት የ”ስቶሪ ቴዎሎጂ” እና የ”ናሬቲቭ ቴዎሎጂ” ምልክቶች ቀድሞ ወደ ነበሩበት መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ የእምነታቸን መሰረት እግዚአብሔር አባቴ ነው በሚል አንድ አይሁዳዊ ተጓዥ ሰባኪ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ነው የሚለውን ታሪክ ያመንን ሁላችን ህይወታችንን፤ ተስፋችንን እና አገልግሎታችንን ሁሉ ከዚያ ጋር አጣብቀናል፡፡ እንግዲህ “ከዕለታት አንድ ቀን” ብሎ የጀመረው ታሪካችን “በደስታና በተድላ አብረው ኖሩ” የሚል ፍጻሜ እንደሚኖረው መዘንጋት የለብንም። በመሆኑም በአካባቢያዊም ሆነ በአለምአቀፋዊ ሚሽን መሳተፍ ማለት ሌሎቹ ከመስማታቸው በፊት እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ የሚፈጽመውን የእግዚአብሔርን ታሪክ ላልሰሙት ማወጅ ነው።
በአለምአቀፍ የሚሽን አለም ውስጥ ሁልጊዜም የታሪክ ጊዜ ነው።
የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ እኛና መላው አለም የእርሱን ድንቅ ስራዎች እናስተውል ዘንድ የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥሪ በፍጥነት እንድንመልስና ለሰዎች ሁሉ የማዳኑን የምስራች እንድናውጅ ጌታ ሆይ ጸጋን ስጠን፤ እርሱም ከአንተና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚኖርና የሚነግስ አንድ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም። አሜን! ~ Episcopal Church. The Book of Common Prayer and Administrations of the Sacraments and Other Rites and Ceremonies of the Church, Together with the Psalter or Psalms of David. New York: The Church Hymnal Corporation, 1979. p 215
የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት
1 8 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ይህ ትምህርት ፈተና የለውም
ፈተና
ይህ ትምህርት የቃል ጥናት ጥቅስ የለውም
የቃል ጥናት ጥቅስ ምዘና
የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ
ይህ ትምህርት የቤት ስራ/መልመጃ የለውም
1
CONTACT
የታሪክ አምላክ እና የእግዚአብሔር ትእይንት ክርስትናን እንደ ግል እና ዝም ብሎ እንደሚኖር ነገር አድርጎ በሚመለከት አለም ውስጥ ብዙ ክርስቲያኖች ክርስትናን እንደ ታሪካዊ እምነት መጠበቅን ትተዋል። በርካታ የሊበራል ክንፍ ዋና ዋና ቤተ እምነቶች ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ የተናገሩትን “ታሪካዊነት” ክደዋል። ለምሳሌ፥ የኢየሱስ ሴሚናር (ማለትም በጣም የተደራጀው የምሁራን የምርምር ቡድን በወንጌላት ውስጥ ከሚገኙት የኢየሱስ ንግግሮች በርግጥ በትክክል በኢየሱስ የተነገሩት የትኞቹ እንደሆኑ የመለየትን ስራ ሰርቶአል።) ተበታትነው ከሚገኙት በርካታ የኢየሱስ ንግግሮች ውስጥ በትክክል በኢየሱስ መነገራቸውን ለመቀበል የፈቀዱት ጥቂቶች ብቻ ነበሩ። በርካታ ሴሚናሪዎች ክርስትያኖች ባለፉት ብዙ ምዕተ አመታት ይዘውት የቆዩትንና ሲያምኑበት የኖሩትን ሳይሆን ሳይንስ በገዛ ፍቃዱ ክርስትና እንዲህ ነው ብሎ ያስቀመጠውን ሳይንሳዊ የሀይማኖት ጥናት መርጠው እናያለን፡፡ እነዚህና እንዚህን የመሳሰሉ ጥናቶችን ብዙዎች እንደ ታሪካዊ እንዲሁም ትንሳኤን እንደ እውነት አዋጅ አድርገው እንዳይቀበሉ አዳጋች አድርጎባቸዋል። ሚሽን ሁልጊዜም ቢሆን ወደ ሌሎች ከመወሰዱ በፊት ስለ ክርስትና እምነት ታሪካዊ ዳራ መረዳት ለምን አስፈላጊ ይመስልሃል? የጳውሎስ ትንሳኤን እንደ የእውነተኛ የክርስቶስ ስብከትና ትምህርት መሰረት መመልከት የትኛውንም ወገን ክርስትና የወንጌልን ታሪካዊ ዋጋ እንደማይቀበል አድርጎ እንዲመለከት አለመፍቀዱ ለምን ይመስልሃል? የባህል ምልክቶችን ሙሉ በሙሉ እየተሳሳቱ ናቸውን? ሆሊውድ በታላላቅ አስገራሚ አፈ ታሪኮችና ተረቶች( gladiators. the lord of the rings, the chronicles of the narina, etc) በፈነዱበት በዚህ ወቅት በርካታ የክርስተያን መድረኮች በሶስት ነጥብ ግጥም እና ጸሎት ላይ ተወስነው የስብከት አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ይህ አይነቱ ስብከትና የአቀራረብ ታሪክ በህብረተሰባችን ላይ ያለውን ኃይል ችላ ያለ ይመስላል፡፡ በርካታ ሰባኪያንና ክርስቲያን ምሁራን ታሪክ መንገር በክርስተያናዊ አገልግሎትና በሚሽን ስራ ላይ ያለውን ወሳኝ ድርሻ ዘንግተው ይልቁን “ፍርድን የሚጠይቁ ማስረጃዎች” ላይ ስለተመሰረቱ የክርስትና ማስረጃዎችና ትንታኔዎች ለይ ሲጨነቁ ይታያል፡፡ በዚህ ዲጂታል ዘመን መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ሆሊውድ የሚዳስሷቸው እንደ ሞራልና ማህበራዊ ለውጦች ስላሉ “ዘመናዊ” ጉዳዮችን ለማስተማር ምስልን፤ ትንቢትን፤ ስነጽሁፍና ታሪክን የመሳሰሉ
1
2
/ 1 9
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋ የብዙዎችን ልብና አዕምሮ ለመንካት ሲባል ችላ ተብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ያለው ስነ ምግባራዊ ትምህርትና በቀጥታ ለቀረበው ስነ መለኮታዊ ይዘት የተሰጠው ትኩረት ባህልን በተሳሳተ መነገድ ከመረዳት የመጣ ይመስልሃል? አንተ ምን ይመስልሃል -ባህል ትኩረታቸውንና ዕይታቸውን የሚይዘ ታሪክ እየፈለገ ነው ወይስ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚችል ማብረሪያ? አብራራ
በዚህ ዘመን ማንም ቃሉን አይጠብቅም የተስፋን ቃል እንደቁምነገር በማይወስዱት ህብረተሰብ ውስጥ እንዴት የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ግልጽና አሳማኝ ማድረግ እንችላለን? ቃል ኪዳኖች አስገራሚ በሆነ መንገድ ሲበሰሩ እየተመለከትን ነው፤ የጋብቻ ቃል ኪዳኖች በአስፈሪ መነገድ በፍቺ እተጠናቀቁ ነው፤ ፖለቲከኞች በሙስና ምክንያቶች ቃል ኪዳናቸውን ይሰብራሉ፤ ሰባኪያን ስለ አሳፋሪው የለሊት ስራቸው (ከተያዙ ብቻ) የፀፀት የአዞ እነባቸውን ሲያፈሱ ይታያሉ፡፡ በዚህ ዘመን ቃልኪዳንን የመጠበቅን ዋጋና ኃይል የተገነዘቡ እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ይመስላሉ፡፡ ይሁን እንጂ የክርስትና እምነት ሙሉ በሙሉ የተመሰረተው የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል አስፈላጊነትና የተስፋ ቃሉንም በክርሰቶስ በኩል መፈጸሙን በመገንዘብ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ እኛ እንዳለንበት አይነት ህብረተሰብ ውስጥ የተስፋ ቃልም መስጠትና መጠበቅ የክርስትናን እምነት ከመረዳት አንጻርና አገልግሎትና ሚሽንን ከማከናወን አንፃር የሚኖረው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? ህብረተሰባችን ውስጥ ያለው ታማኝነት የጎደለው አኗኗር እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ባደረገልን ማዳን ያሳየውን ታማኝነት እንድንረዳና እንድናደንቅ ተጽዕኖ ሳድራል ብለህ ታምናለህ? አብራራ
3
1
የክርስቲያን ሚሽን ራዕይና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት - ክፍል1 ክፍል 1: ሚሽን እንደ ሁል ጊዜ ክስትት
CONTENT
ሬቨረንድ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ
ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትና ስራ እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለሰው ልጆች ሁሉ ያረገውን ማዳን እና ቤዛነት ማወጅ ነው፡፡ ይህን ከእግዚአብሔር አንጻር ስንመለከተው ከዘመን መጀመር አስቀድሞ ከዘመን ፍጻሜ በኋላ ድረስ እግዚአብሔር ስላሴ ነገሮችን ሁሉ ለራሱ ክብርና ለእኛ ጥቅም በሚሆን ሚሽን ላይ እንዳለ እንረዳለን፡፡ ለዚህም ሚሽን እንደ ሁል ጊዜ ክስተት ለተሰኘ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት እንድንችል ነው:- • “ፕሮሌጎሜና” ማለት “የመጀመሪያው ቃል” ማለት ሲሆን ለሚሽንም ፕሮሌጎሜና መጀመር ያለበት እግዚአብሔር በናዝሬቱ ኢየሱስ ክርሰቶስ አማካኝነት በዚህ ምድር ላይ ሚሰራውን ስራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕይታ መመልከት ነው፡፡
የክፍል 1 አጭር ማብራሪያ
2 0 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
• ሚሽን “እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትና ስራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት ለሰው ልጆች ሁሉ ያዘጋጀው የድነትና የቤዛነት ዓዋጅ” እንደሆነ እንደሆነ መተርጎም እንችላለን። • መጽሐፍ ቅዱሳዊው የሚሽን መረዳት ከቅዱሳት መጽሐፍት የሚቀዱ ነጥቦችን አጠቃሎ ይይዛል፡፡ ሚሽን መመስረት ያለበት ስለ እግዚአብሔርና ለፍጥረት ሁሉ ስላለው አላማ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ በመያዝ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊው የሚሽን ምልከታ መመስረት ያለበት መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ስለ ኢየሱስ ማንነትና ስራ በሚናገረው ላይ ሆኖ ይህም በምስል፣ በስእሎች እና በታሪኮች መተረክ ያስፈልገዋል፡፡ • አራቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሚሽን ማዕቀፎች/ምስሎች ማለትም ሚሽን እንደ ዘወትር ክስተት (በታሪኩ ውስጥ እግዚአብሔር እንደ ዋና ገፀ ባህሪ) ፤ እንደ መለኮታዊ ቃል ኪዳን ውሳኔ (የእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ኪዳን መጠበቅ)፤ እንደ ዘመናት የፍቅር ግንኙነት እግዚአብሔር ለተዋጀው ህዝቡ እንደ ሙሽራ) እና እንደ ሽፍቶች ጦርነት (እግዚአብሔር በፍጥረት አለም ላይ መንግስቱን በ ድጋሚ እንደሚመሰርት ጦረኛ) እንገነዘባለን፡፡ • ከዘመን በፊት (የእግዚአብሔር ቅድመ ህልውና እና አላማ ፣ የአመፃን ምስጢርና የኢ ፍትሃዊነትን ኃይል የሚያሳይ)፤ የጊዜ መጀመሪያ (የአጽናፈ አለሙንና የሰው ልጅ ፍጥረትን ውድቀትና እርግማን ፕሮቶኢቫንጌሊየምን፤ የኤደን መጨረሻ፤ የሞትን አገዛዝና የመጀመሪያዎቹን የጸጋ ምልክቶች ያጠቃልላል)፤ የጊዜ መገለጥ (አብርሃማዊውን ተስፋ፣ ዘጸአትን፣ የመሬትን ምርኮ፣ የከተማ - መቅደስ - ዙፋን፣ የግዞት እና የቅሬታዎችን መመለስ ያጠቃልላል።) • ስለዘመንፍጻሜየማይታጠፈውየእግዚአብሔርተስፋ፤ የኢየሱስንስጋመልበስ፤ የመንግስቱን መገለጥ፤ የኢየሱስን ህማማት፤ ሞት፤ ትንሳኤና እርገት ያጠቃልላል፡፡ የመጨረሻው ዘመን ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ፤ የቤተክርስትያንን ተሀድሶ፤ የአህዛብን መካተትና የአለማቀፋዊውን ሚሽን ያጠቃልላል፡፡ • የዘመን ፍጻሜ (የአለም አቀፉን ስብከተ ወንጌል ማብቃት፤ የቤተክርስተያንን ክህደት፤ የታላቁን መከራ፤ ፓሩሲያን፤ በምድር ላይ የክርስቶስ አገዛዝ መምጣትን፤ ታላቁን ነጩን ዙፋን፤ የእሳት ባህሩንና የኢየሱስ ክርስቶስ መንግስቱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠትን ያጠቃልላል)፡፡ ከዘመን ፍጻሜ በኋላ (አዲሱን ሰማይና አዲሱን ምድር፣ የአዲሲቷን ኢየሩሳሌም የመታደስ ዘመን እና ሊመጣ ስላለው ዘመን ያጠቃልላል።) • የእግዚአብሔር ሉአላዊ አላማ የሰው ልጆችን ታሪክ እንደሚጽፍ፤ በመለኮታዊ የታሪክ ሂደት ውስጥ እግዚአብሔር እንደ ዋና ገጸ ባህሪ መሆን፤ ሚሽንን በዘመን መጀመሪያ የጠፋውን እንደ ማደስና፤ እግዚአብሔር የሰጠንን ድርሻ ለመወጣት አህዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት በማድረግ ሚሽን እንደ ሁልጊዜ ክስትት የሚኖረውን ማዕቀፍ ያስረዳል፡፡
1
/ 2 1
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ቪድዮ ሴግመንት 1 ዝርዝር
I. ፕሮሌጎሜና ለሚሽን: ትልቁ ምስል
የእግዚአብሔር ሚሽን ስለክርስቶስ አካል ነው፡፡ ሁሉን አቀፍ አካል የተሰቀለው ክርስቶስ ስጋና ኤክሌሽያዊው አካል (ቤተ ክርስትያን) መነጣጠል አይችሉም፡፡ ለዚህ ምስል በርካታ የሆኑ ውጤቶችን ልናገኝ እንችላለን፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ቀደም ባሉ መልዕክቶች፤ በተለይም በቆሮንቶስና በሮሜ መጻህፍት ትኩረቱ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን አንድነትን በተሰቀለውና ህያው በሆነው በክርስቶስ ላይ ማድረጉ ነው፡፡ ነገር ግን በኋለኞቹ መልእክቶች ቆላስይስና ኤፌሶን ይሄ ምስል ሰፋ ብሎ ዓለም አቀፉን ቤተክርስትያን ሲያቅፍ እንመለከታለን (ቆላ1፡48፣2፡19 ፤ ኤፌ1፡22-23፣4፡16)። ክርስቶስ የአካሉ “ራስ” ነው፤ ይህ ደግሞ ከአንድ አጥቢያ እምነት ማህበረሰብ የሰፋ ነው፡፡ ይህ የምስል ለውጥ ደግሞ እጅግ አስፈላጊ የሚሆንበት ምክንያት ቤተክርስቲያን “ፍሬ እንድታፈራ እና እንድታድግ… በአለም ሁሉ ላይ” (ቆላ 1፡6) የሚሽን ጥሪ መቀበሏንና ይህም ጥሪ የአጥቢያን የእምነት ማህበረሰብም የሚያንጽ እንደሆነ እንድንገነዘብ ይረዳናል፡፡
1
~ Leland Ryken. Dictionary of Biblical Imagery. (electronic ed.) Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2000, p. 109.
ሀ / ትርጓሜ: - ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት እና ሥራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለሰው ልጆች ሁሉ ያደረገውን ማዳን እና ቤዛነት ማወጅ ነው።
1. የእግዚአብሔር የማዳን እና የመቤዠት አዋጅ - ሚሽን የእግዚአብሔርን ዓላማዎች እና የእርሱን የጸጋ እና የይቅርታ አቅርቦትን ይመለከታል ፡፡
ሀ. 2 ጢሞ. 1.8-10
ለ. ሮሜ. 5.8
ሐ. ኤፌ. 1.6-8
መ. ኤፌ. 2.7
2 2 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
2. በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት እና ሥራ አማካኝነት - የናዝሬቱ ኢየሱስ በምድር ላይ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ማዕከል ነው።
ሀ. ሐዋ. ሥራ 10.42-43
ለ. 1 ቆሮ. 3.11
ሐ. 1 ጢሞ. 2.5-6
1
መ. 1 ዮሐንስ 5.11-12
3. በመንፈስ ቅዱስ ኃይል - የመንፈስ ቅዱስ አካል የሚሽን ሥራ ኃይል ነው ፡፡
ሀ. ዘካ. 4.6
ለ. ዮሐንስ 16.13-15
ሐ. ሉቃስ 24.49
መ. ሐዋ. ሥራ 1.8
ሠ. ሐዋ. ሥራ 2.1-4
4. ለሰው ልጆች ሁሉ - በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተደረገው የእግዚአብሔር የማዳን ወንጌል ከኢየሩሳሌም ጀምሮ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለፍጥረት ሁሉ (ለሕዝቦች ሁሉ) ሊታወጅ ይገባል ፡፡
ሀ. ሐዋ ሥራ 1.8
/ 2 3
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ለ. ማርቆስ 16.15
ሐ. ሉቃስ 24.46-47
ለ / ስለ ሚሽን የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤ ነጥቦች
1. ስለ እግዚአብሔር እና እርሱ ስለ ፍጥረታት ያለውን ዓላማ በግልጽ በመረዳት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት ፣ 2 ጢሞ. 1.8-10 ፡፡
1
2. የታሪክ ዝርዝሮችን ሁሉ ከአንድ ወጥ የሆነ ሙሉ ታሪክ ጋር ማዛመድ አለበት ፣ ሮሜ. 8.29-30 ፡፡
3. በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት ፣ ዮሐንስ 5.39-40; ሉቃስ 24.44-48 ፡፡
4. በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነትና ሥራ ላይ መመስረት አለበት ፣ ሥራ 4.12; 1 ዮሐንስ 5.11-13.
5. መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የሚሽን አተያይ በሚገባ መከተል አለበት - በምስል ፣ በስዕል እና በታሪክ ፡
ሐ / በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚሽን አራት ምስሎች
1. ሚሽን የሁልጊዜ ክስተት ነው - በሁልጊዜውም በታላቁ ታሪክ ውስጥ እግዚአብሔር ዋና ገጸ-ባህሪ ነው ፡፡
2. ሚሽን የመለኮታዊው ተስፋ ፍጻሜ ነው - የቃል ኪዳኑ አምላክ እግዚአብሔር እንደ ታማኝነቱ የገባውን ቃል ይፈጽማል ፡፡
2 4 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ሥነ-መለኮት በመጀመሪያ ስለ እግዚአብሔር የማሰብ እና የመናገር (ሥነ-መለኮት) እንቅስቃሴ ነው ፣ ሁለተኛው ደግሞ የዚያ እንቅስቃሴ ውጤት (የሉተር ሥነ መለኮት ፣ ወይም የዌስሌይ ፣ ወይም የፊንኔይ ፣ ወይም የዊምበር ፣ ወይም የፓከር ፣
3. ሚሽን የዘመናት ፍቅር ነው - እግዚአብሔር የተቤዠው ህዝቡ ሙሽራ ነው ፡፡
4. ሚሽን የወንበዴዎች ጦርነት ነው - እግዚአብሔር በአጽናፈ አለሙ ላይ አገዛዙን እንደገና እንደሚያቋቁም ተዋጊ
ወይም የማንም ሊሆን ይችላል) መሆኑ ነው፡ ፡ እንደ አንድ ተግባር ፣
II. ሚሽን እንደ ዘወትር ትዕይንት ከዘመን በፊት እስከ ወዲያኛው ከ Suzanne de Dietrich, God’ Unfolding Purpose (Philadelphia: Westminster Press, 1976) የተወሰደ
ሥነ-መለኮት የተለያዩ ግን እርስ በርሳቸው የተዛመዱ የትምህርቶ ዘርፎች ትሥሥር
1
መመልከት፣ ጽሑፎችን ማብራራት (ትርጓሜ) ፣
ሀ / ከዘመን በፊት (ያለፈው ዘላለም) ፣ መዝ. 90.1-2 ፣ “አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን። ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ።”
በሚሰሯቸው ነገሮች ላይ ምን እንደሚሉ መቀመር (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥነ-መለኮት) ፣ ቀደም ሲል እምነት እንዴት እንደተገለጸ በማየት ፣ ለዛሬ መቀመር (ስልታዊ ሥነ-መለኮት) ፣ ለሥነ ምግባር ያለውን አንድምታ መፈለግ ፣ እንደ እውነት እና ጥበብ (አመክንዮአዊ ምልከታ) ማወደስና መጠበቅ ፣ በዓለም ላይ ያለውን ክርስቲያናዊ ተግባር መግለፅ (ሚስዮሎጂ) ፣ በክርስቶስ ውስጥ ለሕይወት የሚሆን ሀብትን ማከማቸት (መንፈሳዊነት) እና የኮርፖሬት አምልኮ (ሥነ-አምልኮ) እና አሰሳዊ አገልግሎት (ተግባራዊ ሥነ-መለኮት) ነው፡፡
1. ዘላለማዊው ሥላሴ አምላክ ፣ መዝ. 102.24-27
2. የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዓላማ ፣ 2 ጢሞ. 1.9; ኢሳ. 14.26-27
ሀ. በፍጥረት ውስጥ ስሙን ለማክበር ፣ ምሳ. 16.4; መዝ. 135.6; ኢሳ. 48.11
ለ. በአጽናፈ ዓለም ውስጥ የእርሱን ፍጽምና ለማሳየት ፣ መዝ. 19.1
ሐ. ሕዝብን ለራሱ ለማውጣት፣ ኢሳ. 43.7 ፣ 21
~J. I. Packer, Concise Theology: A Guide to
Historic Christian Beliefs. (electronic ed.). Wheaton,
3. የግፍ ምስጢር - የ”ንጋት ኮኮብ” (ሉሲፈር) አመፅ ፣ ኢሳ. 14.12-20; ሕዝ. 28.13-17
IL: Tyndale House Publishers, 1995.
4. አለቆች እና ስልጣናት ፣ ቆላ 2.15
/ 2 5
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ለ / የጊዜ መጀመሪያ (ፍጥረት) ፣ ዘፍ 1-2
1. የሥላሴ አምላክ የመፍጠር ቃል ፣ ዘፍ. መዝ. 33.6,9; መዝ. 148.1-5
2. የሰው ልጅ መፈጠር - ኢሜጆ ዲ ፣ ዘፍ 1.26-27
ሐ / የጊዜ መጀመር (ውድቀት እና መርገም) ፣ ዘፍ 1-2
1
1. ውድቀት እና መርገም ፣ ዘፍ. 3.1-9
2. ዘ ፕሮቶኢቫንጀሊየም (The Protoevangelium) - የተስፋው ዘር፣ ዘፍ 3:15
3. የኤደን ፍጻሜ እና የሞት አገዛዝ ፣ ዘፍ 3.22-24
4. የመጀመሪያ የጸጋ ምልክቶች; ዘፍ. 3.15, 21
መ / የጊዜ መፈታት (የእግዚአብሔር እቅድ በእስራኤል በኩል መገለጥ)
1. የአብርሃማዊ ተስፋ እና የያህዌ ቃል ኪዳን (አባቶች); ዘፍ 12.1-3; 15; 17; 18.18; 28.4
2. ዘፀአት እና ኪዳን በሲና ፣ ዘፀዓት
3. የነዋሪዎች ድል እና የተስፋይቱ ምድር፣ ኢያሱ -2 ዜና መዋዕል
4. ከተማው ፣ መቅደሱ እና ዙፋኑ ፣ መዝ. 48.1-3; 2 ዜና. 7.14; 2 ሳሙ. 7.8
ሀ. የነቢዩ ሚና - የጌታን ቃል ለማወጅ ፣ ዘዳ. 18.15
2 6 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ለ. የካህኑ ሚና - እግዚአብሔርን እና ሰዎችን ለመወከል ፣ ዕብ. 5.1 - “ሊቀ ካህናት ሁሉ ስለ ኃጢአት መባንና መስዋዕትን ሊያቀርብ ከሰው ተመርጦ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾማልና፤”
ሐ. የንጉሱ ሚና ፣ በእግዚአብሔር ፋንታ በፅድቅ እና በፍትህ እንዲገዛ ፣ መዝ. 72
5. ምርኮ ፣ ዳንኤል ፣ ሕዝቅኤል ፣ ሰቆቃወ ኤርምያስ
1
6. የቅሬታዎቹ መመለስ ፣ ዕዝራ ፣ ነህምያ
ሠ/ የዘመን ፍጻሜ (የመሲሑ ሥጋ መልበስ/ትስጉት) ፣ ገላ. 4.4-6
1. ቃል ሥጋ ሆነ ፣ ዮሐንስ 1.14-18; 1 ዮሐንስ 1.1-4
2. የመጥምቁ ዮሐንስ ምስክርነት ፣ ማቴ. 3.1-3
3. በናዝሬቱ ኢየሱስ ሰውነት በኩል የመንግሥቱ መምጣት፣ ማርቆስ 1.14-15; ሉቃስ 10.9-11; 10.11; 17.20-21; ማቴ. 12.28-29 ፡፡
ሀ. በሰውነቱ ተገለጠ ፣ ዮሐንስ 1.18
ለ. በሥራዎቹ ታየ ፣ ዮሐንስ 5.36; 3.2; 9.30-33; 10.37-38; የሐዋርያት ሥራ 2.22; 10.38-39
ሐ. በምስክርነቱ ተተረጎመ ፣ ማቴ. 5-7
4. የመንግሥቱ ምስጢር ተገለጠ ፣ ማርቆስ 1.14-15
/ 2 7
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ሀ. መንግሥቱ እነሆ መጥቷል ፣ ማቴ. 12.25-29 ፡፡
ለ. መንግሥቱ ገና አልተጠናቀቀም ፣ ማቴ. 25.31-46 ፡፡
5. የተሰቀለው ንጉሥ ሕማምና ሞት ፣ ማቴ. 26.36-46; ማርቆስ 14.32-42; ሉቃስ 22.39-46; ዮሐንስ 18.1 ራ.
ሀ. የዲያብሎስን ሥራ ለማጥፋት - ክሪስቶስ ቪክተር ፣ 1 ዮሐንስ 3.8; ዘፍ 3.15; ቆላ 2.15; ሮም. 16.20; ዕብ. 2.14-15
1
ለ. ለኃጢአት ማስተሰረያ ለማድረግ - ክሪስቶስ ቪክተር ፣ 1 ዮሐንስ 2.1-2; ሮም. 5.8-9; 1 ዮሐንስ 4.9-10; 1 ዮሐንስ 3.16
ሐ. የአብን ልብ ለመግለጥ ዮሐ 3.16; ቲቶ 2.11-15
6. ክሪስቶስ ቪክተር - የከበረው የሕይወት ጌታ ትንሣኤ ፣ ማቴ. 28.1-15; ማርቆስ 16.1 11; ሉቃስ 24.1-12; ዮሐንስ 20.1-18; ዝ.ከ. 1 ቆሮ. 15
ረ / የመጨረሻው ዘመን (የመንፈስ ቅዱስ መውረድ እና ዘመን)
1. የእግዚአብሔር አረቦን: መንፈስ እንደ መንግሥቱ ቃል ኪዳን እና መገኘት ምልክት፣ ኤፌ. 1.13-14; 4.30; የሐዋርያት ሥራ 2.1-47; 2 ቆሮ. 1.22; ሮም. 8.14-16
2. “ይህ ያ ነው” -ጴጥሮስ ፣ ጴንጤቆስጤ እና የወደፊት መኖር
ሀ. ቤተክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር መንግስት ቅምሻ እና ወኪል ፣ ፊል. 2.14-16; 2 ቆሮ. 5.20
2 8 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ለ. የመሲሑ ኢየሱስ አገዛዝ በአሁኑ ዘመን፣ 1 ቆሮ 15.24-28; የሐዋርያት ሥራ 2.34; ኤፌ. 1.20-23; ዕብ. 1.13
ሐ. የእግዚአብሔር መንግሥት ማኅበረሰብ አገልግሎት “በዘመናት መካከል”፣ ሮም. 14.7
3. የመሲሑ የኢየሱስ ቤተክርስቲያን - የመጣው እና ገና ያልተጠናቀቀው መንግሥት እንግዶች
1
ሀ. ታላቁ የአዋጅ ቃል - ኢየሱስ ጌታ ነው ፣ ፊል. 2.9-11 ፡፡
ለ. ታላቁ ተልእኮ - ወደ አሕዛብ ሁሉ ሂዱና ደቀ መዛሙርት አድርጒቸው፣ ማቴ. 28.18-20; ሥራ 1.8.
ሐ. ታላቁ ትእዛዝ - እግዚአብሔርን ውደድ እንዲሁም ሰዎችን ውደድ ፣ ማቴ. 22.37-39 ፡፡
4. የምሥጢሩ መታወቅ - አሕዛብ የተስፋው ቃል አብሮ ወራሾች መሆን ፣ ሮሜ. 16.25 27; ቆላ 1.26-28; ኤፌ. 3.3-11
ሀ. ኢየሱስ እንደ መጨረሻው አዳም ፣ 1 ቆሮ. 15.45-49
ለ. የእግዚአብሔር ከዚህ ዓለም አዲስን ሰው ማውጣት ፣ ኤፌ. 2.12-22
5. በዘመናት መካከል - የሰንበት እና የኢዮቤልዩ ዘመን ምልክቶች ፣ የሐዋርያት ሥራ 2.17፣ ኢዩኤል 2; አሞጽ 9; ሕዝ. 36.25-27; መዝ. 110.1
/ 2 9
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ሰ / የዘመኑ መፈጸም (ዘ ፓሮሲያ ኦፍ ክራይስት) ፣ 1 ተሰ. 4.13-17
1. የዓለም ተልእኮ መጠናቀቅ - ሁሉንም የዓለም ህብረተሰብ በወንጌል መድረስ ፣ ማቴ. 24.14; ማርቆስ 16.15-16; ሮሜ. 10.18; 15.18-21; ቆላ 1.23
2. የቤተክርስቲያን ክህደት ፣ 1 ጢሞ. 4.1-3; 2 ጢሞ. 4.3; 2 ተሰ. 2.3-12
3. ታላቁ መከራ ፣ ማቴ. 24.21; ሉቃስ 21.24
1
4. ዘ ፓሩሲያ - የኢየሱስ ዳግም ምፅዓት ፣ 1 ተሰ. 4.13-17; 1 ቆሮ. 15.50-58; ሉቃስ 21.25-27; ዳን. 7.13; ማቴ. 26.64; ማርቆስ 13.26; ሐዋ ሥራ 1.9-11
5. የኢየሱስ ክርስቶስ ግዛት በምድር ፣ ራዕ. 20.1-4
6. ታላቁ ነጭ ዙፋን እና የእሳት ባህር ፣ ራዕይ 20.11-15
7. “ሊነግሥ ይገባል”: - በመጨረሻም የጠላቶች ሁሉ በክርስቶስ እግር ስር መውደቅ ፣ 1 ቆሮ. 15.24-28
ሸ - ጊዜ ሲያበቃ (የዘላለም ሕይወት)
1. የአዲስ ሰማይና የአዲስ ምድር መፈጠር ፣ ራዕ 21.1; ኢሳ. 65.17-19; 66.22; 2 ጴጥ. 3.13
2. የአዲሲቱ ኢየሩሳሌም መውረድ - የእግዚአብሔር ማደሪያ ወደ ምድር መምጣት ፣ ራእይ 21.2-4
3. የመታደስ ጊዜያት - የእግዚአብሔር ልጆች የክብር ነፃነት ፣ ሮሜ. 8.18-23
3 0 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
4. ጌታ ክርስቶስ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር አብ ይሰጣል ፣ 1 ቆሮ. 15.24-28
5. ሊመጣ ያለው ዘመን - ሥላሴ እግዚአብሔር እንደ ሁሉ በሁሉ
ሀ. ዘካ. 14.9
ለ. ኤር. 23.6
1
ሐ. ማቴ. 1.23
መ. መዝ. 72.8-11
ሠ. ሚክ. 4.1-3
ረ. ዘካ. 2.10
III. የሚሽን እንደ ዘወትር ትዕይንት አንድምታ
ሀ / የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ዓላማ ሁሉንም የሰው ልጆች ታሪክ ይጽፋል
1. የወደደውን ሁሉ ያደርጋል ፣ መዝ. 135.6.
2. የእግዚአብሔር ምክር እና ዕቅድ በሁሉም ትውልዶች እስከመጨረሻው ይጸናል።
ሀ. መዝ. 33.11
/ 3 1
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ለ. መዝ. 115.3
3. እግዚአብሔር የነገርን ሁሉ ፍጻሜ ከመጀመሪያው ያውጃል ፣ ኢሳ. 46.10.
4. የእግዚአብሔርን የማዳን እና የመቤዠት ዕቅድ መቋቋም የሚችል ምንም እና ማንም የለም ፣ ዳን. 4.35.
ለ / በመለኮታዊው ትእይንት ውስጥ እግዚአብሔር ማዕከላዊው ገጸ ባሕርይ ነው ፣ ኤፌ. 1.9 11 ፡፡
1
ሐ ሚሽን በጊዜ መጀመሪያ የጠፋውን መልሶ ማግኘት ነው።
1. የእግዚአብሔር ሉዓላዊ አገዛዝ ፣ ማርቆስ 1.14-15
2. የሰይጣን ውስጣዊ አመፅ ፣ ዘፍ 3.15 ከኮሌ 2.15 ጋር; 1 ዮሐንስ 3.8
3. የሰው ልጅ አሳዛኝ ውድቀት ፣ ዘፍ. 3.1-8 ዝ.ከ. ሮም. 5.5-8
መ / ሁሉንም ህዝቦች ደቀ መዛሙርት ማድረግ በልዑል እግዚአብሔር የድርሰት ጽሑፍ ውስጥ የእኛን ድርሻ መወጣት ነው!
ማጠቃለያ
» ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት እና ሥራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለሰው ልጆች ሁሉ ያደረገውን ማዳን እና ቤዛነት ማወጅ ነው። » እንደ እግዚአብሔር ድራማ እና ታሪክ የታየ ፣ የተልእኮ ታሪክ በአንድ ጊዜ እግዚአብሔር እንደ ሉዓላዊ አምላክ ሆኖ ሁሉንም ነገር ለራሱ ክብር እና ለእኛ መልካም አብሮ በመስራት ላይ ነው።
3 2 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
እባክህ በነዚህና በሌሎችም በዚህ ቪዲዮ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ጊዜ ወስደህ ምላሽ ለመስጠት ሞክር፡፡ በዚህ ክፍል መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ሚሽን በመለከተ “ፕሮሌጎሜና” ወይም “የመጀመሪያ ቃል” እንደ ማዕቀፍ አቅርበናል፤ በተጨማሪም ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትና ስራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት ለሰው ልጆች ሁሉ ያደረገውን ማዳንና ቤዛነቱን ማወጅ እንደሆን ትረጓሜ ሰጥተናል፡፡ ይህን እንደ እግዚአብሔር ታሪክና ትዕይንት ስንመለከተው ገና ከዘመን መጀመሪያ በፊትም ሆነ ከዘመን ፍጻሜ ባሻገር አምላከ ስላሴ እንዴት እንደሚያደረገው እንገነዘባለን፡፡ እንግዲህ በዚህ ሞጁል (ትምህርት) ማከናወን የምንፈልገው “ትልቁ ምስል” የሆነውን የሚሽን ተፈጥሮ እንደሚወስንና የመጀመሪያውም ደረጃ በዚህ ክፍል ውስጥ የተካተቱትን ዋና ዋና ለመቃኘት ሞክር፡፡ መልሶችህን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አስደግፍ፡፡ 1. “ፕሮሌጎሜና” ማለት ምን ማለት ነው? እግዚአብሔር በናዝሬቱ ኢየሱስ በኩል በምድር ላይ ላለው ሚሽን የሚነሳውን “ፕሮሌጎሜና ሚሽን” የሚለው አተያይ ለምን ያስፈልገናል? 2. ለ”ሚሽን” ትርጓሜ ስጥ፤ ለመጽሐፍ ቅዱሳዊው የሚሽን ግንዛቤ የሚረዱን ዝርዝሮች ስለ ሚሽን ሊኖረን የሚገባውን እይታ ከራሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ መሆን ያለበት ለምንድነው? ለምን ከሚሽነሪዎችና የሚሽን ድርጅቶች አይሆንም? 3. መጽሐፍ ቅዱሳዊው ሚሽን ራሱ በኢየሱስ ማንነትና ስራ ላይ መመስረት ያለበትና መጽሐፍ ቅዱስ ሚሽንን ለማስረዳት የሚከተለውን ምስሎችን፣ ስእሎችን እና ታሪኮችን መጠቀም ያስፈልገው ለምንድነው? 4. አራቱ ዋና ዋና የስነመለኮታዊ ማዕቀፎች /ምስሎች ምንድር ናቸው? የእያንዳንዱን ትርጓሜ ስጥ፡፡ 5. የሁል ጊዜ ትዕይንት ዋና አካላት ዝርዝር በተለያዩ በተለይም ከዘመን በፊት፣ የዘመን ጅማሬና የዘመን መጠቅለል የተመለከቱትን እያንዳንዳቸውን ማዕከላዊ ነጥቦች በማንሳት ሚሽንን ከመረዳት አንጻር የሚኖራቸውን አንደምታ አስቀምጥ፡፡ 6. ሚሽን እንደ ሁልጊዜ ትዕይንት በዘመን ሙላት፣ በዘመን ፍጻሜ፣ በዘመን ሙላትና ከዘመናት ባሻገር ስላለው የእግዚአብሔር የማይጠፋ አላማ አንጻር አስረዳ፡፡ በተጨማሪም እያንዳንዳቸውን ማዕከላዊ ነጥቦች በማንሳት ከአለማቀፋዊው ሚሽን ጋር ስለሚኖራቸው ዝምድናና በዚያ ውስጥ ስለሚኖራቸው ድርሻ ምን እንደሆነ አስረዳ፡፡ 7. የሚሽን እንደሁልጊዜ ትእይንትማዕቀፍ የእግዚአብሔር ሉአላዊ አላማና በመለኮታዊ ድራማ ውስጥ የሚኖረውን ሚና እንዴት ያስረዳል? ይሀ ማዕቀፍ ሚሽንን በዘመን መጀመሪያ የጠፋውን መልሶ እንደማግኘት እና ደቀ መዛሙርት ማድረግን ደግሞ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ትዕይንት ውስጥ የራሳቸውን ድርሻ ማበርከት እንደሆነ እንድንረዳ እንዴት ያግዘናል?
መሸጋገሪያ 1
የተማሪው ጥያቄዎችና ምላሾች
1
ሚሲዮሎጂ መደበኛው የቤተክርስትያን ሚሽን ጥናት ነው፡፡ በስነ መለኮት ጥናት መስክ ውስጥ የሚመደብ ሆኖ በውስጡ በርከት ያሉ ዘርፎችን አቅፎ ይይዛል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱሳዊው ጥናት የቤተክርስትያን ሚሽን መሰረት “ሚሲዮ ዲ” (የእስራኤል አለም ሁሉ ብርሃን የመሆን ጥሪ) (ኢሳ 49፡6) እና ኢየሱስ ለሐዋርያቱ እስከ ምድር ዳር ድረስ ምስክሮቹ ይሆኑ ዘንድ
/ 3 3
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የሰጣቸው ተልእኮ (ማቴ 28፡18—20፣ሐዋ ሥራ 1፡8) እንደሆነ ያሳያል፡፡ የታሪክ ጥናት ማህበረሰቦችና ጥናቶች ላይ ያመጣውን ተጽዕኖ ይዳስሳል፡፡ ሲስተማቲክ ቲዎሎጂ የክርስትና እምነት ከአለማዊው ፍልስፍና ርዕዮተ አለም እንዲሁም ከሌሎች የእምነት ዘርፎች ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያጠና ዘርፍ ነው፡፡ የስነ ምግባር ጥናቶችም የሚሲዮሎጂ አንድ አካል በመሆን ተካተዋል ቤተክርስቲያን ለሁለንተናዊው ህይወት የእግዚብሔርን ፍቃድ የማወጅ ኃላፊነት ስላለበት ፓስቶራል ቲዎሎጂ ለአዳዲስ ነፍሳት መመሪያ በመስጠት ከቤተክርስትያን ጋር እንዲዋሃዱ መንገዶች ይፈልጋል፡፡ ሚሲዮሎጂ ሰፊ እንደ መሆኑ መጠን ከሌሎች ስራዎች ጋር የሚኖረው ጥምረት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ የስነመለኮት ገጽታ የማይታለፍ ሚሲዮናዊ አቅጣጫ አለው ምክንያቱም እያንዳንዱ ያለው ለቤተክርስቲያን ሚሽን ሲባል ነው። ~ J. A. Kirk. “Missiology.” The New Dictionary of Theology. S. B. Ferguson, ed. (electronic ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2000. p. 434.
1
የክርስትያን ሚሽን ራዕይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት: ክፍል 1
ሴግመንት 2፡ ሚሽን እንደ መለኮታዊው ተስፋ ቃል ፍጻሜ
ሬቨረንድ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ
ሚሽን እንደ መኮታዊ የተስፋ ቃል ፍጻሜ የእግዚአብሔርን ስራ ለአብርሃምና ዳዊት እንደገባላቸው ቃል ኪዳን መፈጸም አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው የኪዳን ሚና ላይ እንደመመስረቱ ይህ ዋና ሃሳብ የሚነሳው እግዚአብሔር ለአብርሀም ከሰጠው ኪዳን ሲሆን፥ በልጆቹና በአባቶች ይጸናና በመቀጠልም በይሁዳ ነገድ ተለይቶ ይታወቃል፡፡ ይህ ትውልድን የመባረክ የዘር ተስፋ እግዚአብሔር ለዳዊት ከዙፋኑ ወራሽ እንደማይታጣ በገባለት ተስፋ ተብራርቶና ተስተጋብቶ እናገኘዋለን፡፡ እንግዲህ በተመሳሳይ በዚህ ዘመን እና በኢየሱስ ማንነት የአብርሀምና የዳዊት የተስፋ ቃል ተፈጽሟል፡፡ በተመሳሳይ በዚህ ዘመን በሚሽን አማካኝነት ወንጌል ሲታወጅ በመስቀሉ ስብከት አማካኝነት የአዲስ ህይወት ተስፋ ለሰዎች ሁሉ ተሰጥቷል፡፡ ለዚህ ሚሽን እንደ መለኮታዊው የተስፋ ቃል ፍጻሜ ለተሰኘ ሴግመንት አለማችን የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት ትችል ዘንድ ነው፡፡ • ሚሽንን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚያብራሩት አራት ዋነኛ ኃሳቦች ወይም ጭብጦች አንዱ ሚሽን እንደ መለኮታዊ የተስፋ ቃል ፍጻሜ የሚለው ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ስናየው ቃል ኪዳን ማለት በሁለት ወገኖች መካከል በግለሰቦች፣ በጎሳዎች ወይም ህዝቦች መካከል የሚደረግ የሚደረግ ስምምነት ሲሆን ይህም ስምምነት ለሁለቱም ወገኖች የሚገቡትን ግዴታና የሚያኙትን ጥቅም ያካትታል፡፡
የሴግመንት 2 ማጠቃለያ
3 4 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
• መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኪዳኖች የሚጋሯቸው የጋራ የሆኑ ባህሪያት ሲኖራቸው ይህም ውሎች እና ስምምነቶች በምስክሮች ፊት መካሄዳቸውን እና ውል መጣስ የሚያስከትለውን ውጤት (ማለትም ውሎችን መጣስ እንደ ከባድ ስነምግባራዊ ጥሰት ይቆጥራል) ያካትታል፡፡ ቃልኪዳኖች የሚሰጡት ስጦታ በመስጠት፣ ምግብ በመመገብና ብዙ ጊዜ ደግሞ የማስታወሻ ድንጋይ በማስቀመጥ ነው፡፡ የሚረጋገጡት ደግሞ በመስዋዕት በሚደረገግ መሃላ ነው፡፡ • ምናልባትም የመጽሐፍ ቅዱሰቀዊው ኪዳን ዋና ማሳያ የጋብቻ ስነ ስርዓት ሲሆን ሌላው ማሳያ ደግሞ የእስራኤል ታሪክ ውስጥ የምናየው ይሆናል፡፡ ለምሳሌ እግዚአብሔር ከኖኅ ጋር ያደረገው ኪዳንና እግዚአብሔር በሲና ከእስራኤል ልጆች ጋር ያደረገው ኪዳን፡፡ የእግዚአብሔር ኪዳን በጠቅላለው በእግዚአብሔርና በግለሰቦች ወይም በህዝቡ መካከል በጥንቃቄ የሚደረግ ስምምነት ነው፡፡ • ሚሽን እንደ መለኮታዊ የተስፋ ቃል ፍጻሜ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን ላይ ሊደገፍ ይችላል፤ ከሀገርና ከወገኖቹ ተለይቶ መውጣቱ፣ በዚህም የተነሳ የሚያገኘው የእግዚአብሔር በረከት፤ እግዚአብሄር ታላቅ ህዝብ ያደርገዋል፤ ስሙንም ታላቅ ያደርገዋል፣ የሚባርኩትን ይባርካል፥ የሚረግሙትንም ይረግማል፣ ከእርሱም የተነሳ አህዛብን ሁሉ ይባርካል፡፡ • እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ለአህዛብ የሚተርፍ የዘር ተስፋ የታደሰውና የተረጋገጠው በልጆቹ በይስሐቅና ያዕቆብ በኋላም መሲሁ በሚመጣበት ነገድ በይሁዳ ግልጽ ሆኖ ተለይቷል፡፡ ከይሁዳ ወገን የዳዊት ቤት ለአብርሃም የተገባው የንጉስ ዘር የሚመጣበት ለመሆን ተመርጧል፡፡ የዳዊትም ወራሽ ለዘላለም በእስራኤል ላይ ይነግሳል፣ ለአህዛብም በረከት ይሆናል፡፡ • እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዳዊት የሰጠው ተስፋ በአብርሃም ዘርነት እና የእግዚአብሔር አገዛዝ በሚመሰረትበት በዳዊት ልጅነት አማካኝነት በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት በኩል ተፈጽሟል፡፡ በኢየሱስ ሕይወት፣ ሞት፤ ትንሳኤና እርገት በኩል ደግሞ የእግዚአብሔር ኪዳን ተፈጽሟል፡፡ • ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ኪዳኑን የመጠበቁን የምስራች ማረጋገጥና ማወጅ ሲሆን ታላቁ ተልዕኮ ደግሞ ይህን የተፈጸመ ተስፋ ከእስራኤል ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ለሰው ልጆች ሁሉ የማወጅና የማስተማር ተልዕኮ ነው፡፡ • የሚሽን ዋና የልብ ትርታ የሚሆነው በናዝሬቱ ኢየሱስ አማካኝነት የዳዊት ተስፋ መፈጸም እንዲሁም ወንጌልን በማወጅ አማካኝነት ደግሞ በመስቀሉ ስብከት ለአህዛብ ሁሉ የተገባው ተስፋ ፍጻሜ ማግኘት ነው፡፡
1
/ 3 5
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የተስፋ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዕብራይስጥ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ተስፋ ስለመስጠት ፅንሰ-ሀሳብ ወይም ድርጊት የተለየ ቃል የለም። የእንግሊዝኛ ትርጉሞች አንድ ሰው ስለ አንድ ነገር ቃል እንደገባ በሚናገሩበት ቦታ ላይ ፣ ዕብራይስጡ በቀላሉ አንድ ሰው ወደፊት ስለሚያደርገው ነገር ያለው ወይም የተናገረው (‘amar ፣ dabar)’ እንደሆነ ይናገራል ፡፡ በአዲስ ኪዳን “ኤፓንጌሊያ” የተሰኘው ቃል በዋነኝነት ተጠቅሶ የምናገኘው በሐዋርያት ሥራ ፣ በገላትያ ፣ በሮሜ እና በዕብራውያን መጻሕፍት ውስጥ ነው፡፡ ቃል ኪዳን ገና ያልተፈጸመ ጊዜን የሚያሳይ ቃል ነው ፡፡ ቃል ሰጪውና ተቀባዩ ለወደፊቱ ቀጠሮ ከመያዛቸው በፊት ቀድሞ የሚመጣ ነው። የተስፋ ቃል አንድን ሰው ወክሎ ለሚቀጥል ወይም ለወደፊቱ ለሚከናወን ድርጊት ማረጋገጫ ሊሆን ይችላል፡ “ከእናንተ ጋር እሆናለሁ” ፣ “የሚያዝኑ ይጽናናሉ” ፣ “ኃጢአታችንን የምንናዘዝ ከሆነ እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ይለናል።” የተስፋ ቃልም እንደ ቃል ኪዳን ሁሉ ዘላቂ ፣ የጋራና በጥንቃቄ የሚደረግ ስምምነት ሊሆን ይችላል። የወደፊቱን ክስተት ማስታወቂያ ሊሆን ይችላል፡ “ሕዝቡን ከግብፅ ባመጣችሁ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ”። ~ J. W. L Hoad. “Promise.” The New Bible Dictionary. D. R. W. Wood, ed. (3rd ed., electronic ed.). Downers Grove: InterVarsity Press, 1996. p. 963.
1
ቪዲዮ ሴግመንት 2 መመሪያ
I. ሚሽን የመለኮታዊው ተስፋ ፍጻሜ ነው - እንደ ታማኝ አምላክ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን መፈጸም
ሀ / የቃል ኪዳን ትርጉም
1. ዕብራይስጥ ፣ “ብሪት/ brit ,” ፣ “መቁረጥ”። በእግዚአብሔር እና በሰው ልጆች መካከል እንዲሁም በሰዎችና በሰዎች መካከል ለተለያዩ ውሎች እና ግብይቶች የሚተገበር ቃል።
ሀ. የተሰጡ “አጋሮች” ፣ አብድዩ 1.7
ለ. ብሉይ እና አዲስ “ኪዳን/Testament” የሚለው ቃል “ኪዳን/Covenant” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው።
2. በግለሰቦች ፣ በጎሳዎች ወይም በህዝቦች መካከል ፥ በሁለት ወገኖች መካከል ውልን ሊያመለክት ይችላል
3 6 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ሀ. በህዝቦች መካከል ፣ ኢያሱ። 9.6; ኢያሱ 9.15
ለ. በከተሞች መካከል ፣ 1 ሳሙ. 11.1
ሐ. በግለሰቦች መካከል ፣ ዘፍ 21.27
3. ቃል ኪዳን ኪዳን የመጠበቅ ግዴታዎችን እና ከዚያም የተነሳ የሚገኙ ጥቅሞችን ያካትታል ፡፡
1
4. ቃል ኪዳን የማድረግ ተፈጥሮ
ሀ. እግዚአብሔር እንደ ምስክር ተጠርቷል ፣ ዘፍ. 31.52-53 ፣ በተጨማሪ 1 ሳሙ. 20.8; ኤር. 34.18-19; ሕዝ. 17.19.
ለ. ውልን ማፍረስ እንደ ከባድ ሥነ ምግባራዊ ክፋት ፣ እንደ ኃጢአትም ተደርጎ ይታሰብ ነበር ፣ ሕዝ. 17.12-20; ዝ.ከ. ሕዝ. 17.16.
ሐ. ቃል ኪዳኖች ስጦታ በመስጠት ወይም ድንጋዮችን ለማስታወሻነት በማኖር ፣ በምግብ ወይም በአሞሌ ጨው በመስጠት ይደረጉ ነበር (ዘፍ. 26.30 ፤ 31 ፤ 54 ፤ 2 ሳሙ. 3.12, 20)። (1) ዘፍ 21.30-31
(2) ዘፍ 31.52
5. ጋብቻ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገባ የጋራ ቃል ኪዳን ነው ፣ ምሳ. 2.17.
6. ቃል ኪዳኖች በመሃላ ይረጋገጡ ነበር (ዘፍ. 26.28 ፤ 31.53 ፣ ኢያሱ. ኤር 34.18-20) እርድ በማረድና ለሁለት እኩሌታ በመቁረጥ ፣ ሁለቱም ወገኖች በተጎጂው እርድ መካከል በማለፍ ያጸድቁ ነበር (ዘፍ. 15.9-10 ፣ 17-18 ፣ ኤር. 34.18-20)።
/ 3 7
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ሀ. በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ውል ያትማል
ለ. ተዋዋይ ወገኖች የገቡትን ቃል ካልፈጸሙ ምን እንደሚከሰት ማሳያ ይሆናል
ለ / በእግዚአብሔር እና በሌሎች ሰዎች መካከል የተገቡ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳን ምሳሌዎች
1. ቃል ኪዳን ከኖህ ጋር (በዝናብ የሚመጣ ፍርድ ዳግመኛ እንደማይከሰት እና የቀን እና የሌሊት እንዲሁም የወቅቶች ዑደት እንደማይቋረጥ) ፣ ዘፍ 9.8-13
1
2. የሲና ቃል ኪዳን ከእስራኤል ልጆች ጋር (አሥርቱን ትእዛዛት እና ሕጉን በሙሴ በኩል መስጠት ፣ ትእዛዛቱን በመጠበቅ ስላለ በረከት እና ባለመታዘዝ ስለሚመጣ ፍርድ)
ሀ. ዘፀ. 24.3
ለ. ዘፀ. 34.28
ሐ. ዘዳ. 4.13
መ. ዘዳ. 29.1
II. ሚሽን የመለኮታዊው ተስፋ ፍጻሜ ነው - እንደ ታማኝ አምላክ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን መፈጸም
ሀ / እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገባ - የአብርሃም ቃል ኪዳን - የዘር ተስፋ
1. የቃል ኪዳኑ ሁኔታ እና የአራት እጥፍ በረከት ፣ ዘፍ 12.1-3 ፣
3 8 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ሀ. ሁኔታ: - ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። ዘፍ 12፥1
ለ. በረከት
(1) ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ
(2) እባርክሃለሁ ስምህንም ታላቅ አደርገዋለሁ
(3) የሚባርኩህን እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ ፡፡
(4) በአንተ አህዛብ ሁሉ ይባረካሉ።
1
2. እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ቃልኪዳኑን አደሰ ፣ ከወንድ ልጅ ተስፋ እና ከማይቆጠር የዘር በረከት ተስፋ ጋር ፣ ዘፍ 15.4-6።
3. ኪዳኑ ከተደረገ ከአሥራ አራት ዓመታት በኋላ እንደገና ጸንቷል ፣ የአብርሃምን ስም በመለወጥ እና የመገረዝን ስርዓት እንደ ቃል ኪዳኑ ምልክት በማቋቋም ፣ ዘፍ. 17.1-10
4. አብርሃም ይስሐቅን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ለመሠዋት ፈቃደኛ ከሆነበት ፈተና በኋላ የተረጋገጠ ፣ ዘፍ 22.16-18
ለ / የተስፋው ቃል በአባቶች ተረጋግጧል
1. በይስሐቅ ተረጋግጧል ፣ ዘፍ 26.24-25
2. በያዕቆብ ተረጋግጧል ፣ ዘፍ. 28.13-14
3. እግዚአብሔር ከአብርሃም ፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ይታወቃል ፡፡
ሀ. መዝ. 105.8-11
/ 3 9
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ለ. ሚክ. 7.20
ሐ / የተስፋው ቃል ተለይቶ ታወቀ - የይሁዳ ነገድ-የአብርሃም ዘር ከይሁዳ ነገድ ይወጣል ፣ ዘፍ 49.8-10።
1. የትንቢታዊ ቃል ትዕይንት - ከመሞቱ በፊት የያዕቆብ በረከት በልጆቹ ላይ ፣ ዘፍ 49
2. የይሁዳ ነገድ ገዢው እንደሚመጣበት የዘር ሐረግ ተለይቶ ታወቀ (ማለትም “በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም”)
1
3. በረከቱ ፥ በትረ መንግሥት (የመግዛት መብት) የእርሱ ይሆናል ፣ ለእርሱም የሕዝቦች ሁሉ መታዘዝ ይሆናል (ሁሉን አቀፍ ድነት)
መ / የተስፋው ቃል ተብራራ - የዳዊት ኪዳን
2ኛሳሙኤል7፡ 8-16 “አሁንምዳዊትንባሪያዬንእንዲህበለው፦የሠራዊትጌታእግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ መንጋውን ስትከተል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰድሁህ፤ በሄድህበትም ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ፤ በምድርም ላይ እንዳሉ እንደ ታላላቆቹ ስም ታላቅ ስም አደርግልሃለሁ። ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርግለታለሁ፥ እተክለውማለሁ፤ በስፍራውም ይቀመጣል፥ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ እንደ ቀድሞው ዘመንና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፈራጆች እንዳስነሣሁበት ጊዜ ግፈኞች ተመልሰው አያስጨንቁትም፤ ከጠላቶችህም አሳርፍሃለሁ። እግዚአብሔርም ደግሞ፦ ቤት እሠራልሃለሁ ብሎ ይነግርሃል። ዕድሜህም በተፈጸመ ጊዜ ከአባቶችህም ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ፥ ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፥ መንግሥቱንም አጸናለሁ። እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፤ የመንግሥቱንም ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ። እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ ሰው በሚቀጣበት በትርና በሰው ልጆች መቀጫ እገሥጸዋለሁ፤ ከፊቴም ከጣልሁት ከሳኦል እንዳራቅሁ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም። ቤትህና መንግሥትህም በፊቴ ለዘላለም ይጠነክራል፥ ዙፋንህም ለዘላለም ይጸናል።
1. የአብርሃም በረከት የሚመጣበትን መስመር በትክክልና በግልፅ ያሳያል
4 0 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
2. የአብርሃም በረከት ንጉሣዊ ዘር በዳዊት ቤት በኩል ይመጣል ፡፡
ሀ. 2 ሳሙ. 7.12
ለ. 2 ሳሙ. 22.51 እ.ኤ.አ.
ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን መካከል እንደተስፋው ማዕከላዊ ስፍራ የብሉይ ኪዳን ተስፋዎች (ለአብርሃም ፣ ለሙሴ ፣ ለዳዊት እና ለአባቶች በነቢያት) የመገናኛ ነጥቡ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የእግዚአብሔር ተስፋዎች ሁሉ በእርሱ የተረጋገጡ ናቸው ፣ በእርሱም በኩል ቤተክርስቲያን በአምልኮቷ ‘አሜን’ ታረጋግጣለች (2 ቆሮ. 1.20) ፡፡ በወንጌላት ትረካዎችም ውስጥ የብሉይ ኪዳን ጥቅሶች እና ምሳሌአዊ ንግግሮች ይህንን ፍጻሜ ያመለክታሉ ፡፡ እግዚአብሔር ቃሉን በመጠበቁ ታላቅ ደስታና በረከት ሆኗል ፡፡ የተገባው ቃል ሥጋ ሆነ ፡፡ አዲሱ ቃል ኪዳን ተከፍቷል - በኤርምያስ በተተነበዩት ‘የተሻሉ ተስፋዎች’ (ኤር. 31 ፤ ዕብ. 8.6-13) ፡፡ ኢየሱስ የዚያ ዋስትና ነው (ዕብ. 7.22) ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የተስፋው መያዣ ነው (ኤፌ. 1.13-14) ፡፡ ~ J. W. L Hoad. “Promise.” The New Bible Dictionary. D. R. W. Wood, ed. (3rd ed., electronic ed.). Downers Grove: InterVarsity Press, 1996. p. 963.
3. በዚህ በተስፋው አምላክ አማካይነት እግዚአብሔር በእስራኤል ቤት ላይ እንደገና ንግሥናውን በመመለስ አሕዛብን ሁሉ ይባርካል ፡፡
1
ሀ. ኢሳ. 9.6-7
ለ. መዝ. 72.8-11
ሐ. መዝ. 89.35-37
መ. ኤር. 33.15-18
ሠ. ዳን. 7.13-14
4. እግዚአብሔር ለዳዊት በሰጠው ተስፋ ፍጻሜ ውስጥ አሕዛብ ሁሉ ይሳተፋሉ ፣ ሐዋ ሥራ 15.15-18 (አሞጽ 9.11-12)
ሠ / የተስፋው ቃል ተፈጽሟል - በናዝሬቱ በኢየሱስ ሰውነት እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዳዊት የሰጠው ተስፋ ተፈጽሟል
1. ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት ተስፋ እንደተገባለት ንጉሳዊ ዘር ከዳዊት ጋር ስላለው ግንኙነት ተብራርቷል ፣ ሉቃስ 1.32-33 ፡፡
Made with FlippingBook - Online catalogs