Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
የክርስቲያን ሚሽን መሰረቶች የሚሽን/ተልእኮ ጽንሰ ሃሳብ በከተማ አብያተ ክርስቲያኖቻችን ዘንድ ሊኖረው የሚገባውን ያህል ትኩረት ሲያገኝ አንመለከትም፡፡ ከውቅያኖስ ማዶ ተሻግሮ በሁሉም የዓለም ማዕዘናት ውስጥ እንዳለ ሥራ በስፋት ከተመለከትነው ፣ ለሚሽን የሚገባውን ዓይነት ትንታኔ ለመስጠት አለመቻላችንን እንረዳለን ፡፡ በአንድ በኩል የክርስትና እምነት በጥቅሉ እንደ ተልእኮው ምላሽ ተደርጎ ሊታይ ይችላል፣ ይህም ምላሽ ወደ አሕዛብ ሄዶ የናዝሬቱ የኢየሱስን የእግዚአብሔር መንግሥት ጌትነት እና ንግስና ለማወጅ የተደረገው ጥሪ ምላሽ ተደርጎ ሊታይ ይችላል ፡፡ አዲስ ኪዳን በክርስትና እምነት ውስጥ ፈር ቀዳጅና ዋና ሚስዮናውያን በነበሩ ሐዋርያት ለተመሰረቱት አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠ የሚስዮናዊ ሰነዶች ስብስብ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ራሱ በክርስቶስ በኩል ወደ ዓለም በመምጣትና ዓለምን ከራሱ ጋር በማስታረቅ የመጀመሪያው ሚስዮናዊ ነው (2 ቆሮ. 5፥18-21)፤ በእርግጥም ክርስትና ተልእኮ ነው ፡፡ በመሆኑም በዚህ ሞጁል ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንጻር የሚሽንን ሥነ-መለኮት ለመረዳት ሚሽንን እንደ ትእይንት ፣ ሚሽንን እንደ ፍቅር እና ጦርነት በተለያዩ መነጽሮች እንቃኛለን ፡፡ በእነዚህም መነጽሮች እይታ ሚሽን በታሪክ ውስጥ እና በየዘመናቱ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ለሰው ልጆች ቤዛነትን ለማምጣት የተጠቀመበት መሳሪያ መሆኑን ከቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቀስ እንመለከታለን። በተጨማሪም በተለይ ለከተማ ሚሽን በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሁለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጉዳዮች እንመለከታለን። ከመጀመሪያው ጀምሮ ፣ የእግዚአብሔር ፍትሕ በከተማው ውስጥ ነግሶ እና ድህነት ተወግዶ በጽድቅ ይተካ ዘንድ ለጌታ ቃል ኪዳን እንዲህ ባለው ታማኝነት ውስጥ እንዲኖሩ እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ማህበረሰብ ሾሟል።
ቄስ ዶ/ር ዶን ዴቪስ ፣ (ፒኤችዲ፥ አዮዋ ዩኒቨርሲቲ) የዎርልድ ኢምፓክት አገልግሎት አካል የሆነው የኧርባን ሚኒስትሪ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ናቸው። እንዲሁም የዎርልድ ኢምፓክት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለግላሉ።
TUMI በዓለም ዙሪያ ቤተክርስቲያን የመትከል እንቅስቃሴዎችን በማመቻቸት መንግሥቱን በከተማ ድሆች መካከል ለማስፋፋት መሪዎችን በማስታጠቅ የሚያገለግል አገልግሎት ነው።
ዎርልድ ኢምፓክት የአሜሪካን የከተማ ድሆችን በወንጌል በማስታጠቅ ፣ በማስታጠቅ እና በማጎልበት የቤተክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴዎችን ለማመቻቸት የቆረጠ የክርስቲያን የሚሽን ተቋም ነው። የእኛ ራዕይ አብያተ ክርስቲያናትን የሚተክሉ እና አገር በቀል የቤተክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴዎችን የሚጀምሩ የከተማ መሪዎችን መመልመል ፣ ማስታጠቅ እና ማሰማራት ነው።
መሪዎችን ማስታጠቅ የማስታጠቅ እንቅስቃሴዎች
THE URBAN MINISTRY INSTITUTE • A MINISTRY OF WORLD IMPACT, INC.
Made with FlippingBook - Online catalogs