Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 0 1

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ASSIGNMENTS

ኤፌሶን 5:25-27 እና ኤፌሶን 6:10-13

የቃል ጥናት ትውስታ

ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።

የንባብ የቤት ስራ

ከላይ የተሰጡትን የቤት ስራዎች በሚገባ ካነበብክ በኋላ ልክ እንደ ባለፈው ሳምንት አጠር ያለ ማጠቃለያ በመጻፍ በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ይዘህ ቅረብ፡፡ (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ ላይ የሚገኘውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ” ተመልከት)፤ አሁን በቀጣይ ስለምትሰራው ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት የንባብ ክፍል የምትመርጥበትና ስለ ሚኒስትሪ ፕሮጀክትህ የምታስብበት ጊዜ ነው፡፡ እነዚህን ውሳኔዎች ለማድረግ አትዘግይ፤ ቶሎ መወሰንህ ለዝግጅት በቂ ጊዜ እንዲኖርህ ያደርጋል፡፡ በዚህ ትምህርት መለኮታዊ ፍቅርና የሽፍቶች ጦርነት የተሰኙ ሁለት ጭብጦችን በመዳሰስ ዛሬ በቤተክርስቲያን የሚሽንን ሚና በመረዳት ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ተመልክተናል፡፡ ከእርሱ ጋር ለዘላለም ይኖሩ ዘንድ አህዛብን ጨምሮ እግዚአብሔር ለርስቱ ወገን ይሆን ዘንድ አህዛብን ከአለም ሁሉ ለመጥራት ስላለው ፍላጎት ተመልክተናል፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሔር በሞቱ፣ በመቀበሩና በትንሳኤው የክፋትን ኃይላትና የመርገምን ተጽዕኖ ሁሉ አሸንፎ የእግዚአብሔርን መንግስት በናዝሬቱ በኢየሱስ በኩል እንዴት እንዳረጋገጠም ተመልክተናል፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ የእግዚአብሔር አገዛዝ በቤተክርስቲያን ህይወት ውስጥ ህያው ሆኖ አለ፡፡ በቀጣዩ ትምህርታችን ለክርሰቲያን ሚሽን መሰረት ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ ላይ እናተኩራለን - ከተማ፡፡ በቀጣዩ ትምህርታችን ከተማ ያለውን መንፈሳዊ ጠቀሜታ እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ከአመጻና እርኩሰት ምሳሌነት ወደራሱ ማደሪያነት እንደቀየረው ከማየት አንጻር እንዳስሳለን፡፡ በዚህ መረዳት ላይ በመመርኮዝ ደግሞ ዛሬ የከተማ ሚሽን (ኧርባን ሚሽን) ለምን በጣም ወሳኝ እንደሆነ ከሶስት ዋናዋና ምክንያቶች አንጻር እንመለከታለን፡፡ ከተማ በአለም ውስጥ እንደ ተጽዕኖ፣ ሃይልና መንፈሳዊ እንቅስቃሴ መቀመጫ ለተጠቁ፣ ለተጨቆኑና ለድሆች እንደ መጠጊያ በመሆን እንደ መንፈሳዊ መዳረሻችንና ርስታችን ይታያል፡፡ እነዚህ ሶስት ምክንያቶች በአካባቢያችንና በሌላውም አለም ላይ ባሉ ከተሞች ላይ በሙሉ አቅማችን ወንጌልን እንድንሰብክ፣ ደቀመዛሙርት እንድናፈራ እና ቤተክርስቲያንን እንድንተክል አስገራሚ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ይሰጡናል፡፡

ሌሎች የቤት ስራዎች

2

ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት

ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል ፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከአስተማሪህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና Www.tumi.org/license ን ይጎብኙ ፡፡

Made with FlippingBook - Online catalogs