Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 3 5
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ሐ / ሚሽን ለከተማ ከሆነ እንዲሁ ለድሆችም መሆን አለበት ፣ ምክንያቱም በከተማ ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ሰዎች ድሆች ናቸው ፡፡
ሁሉም የእስራኤል ተስፋዎች እና ቤተክርስቲያን የሚገኙት ከተማ ውስጥ ነው በአጠቃላይ ፣ የእስራኤል ተስፋዎች ፍፃሜ ፣ እግዚአብሔር ለእርሷ የሰጣት ተስፋ እውን መሆን፣ መገለጥ ፣ የእግዚአብሔር ክብር ባለባት ከተማ ውስጥ ፣ አስቀድሞ ሰማያትና ጠፈር ያወጁትን እውነታ እና የምድር ነገሥታት ክብራቸውን በሚያመጡበት ቦታ ላይ ለሚገኙት ሁሉም ውበት ያላቸው ምኞቶች እና ብሔራዊ ጥያቄያቸውን መልስ እናገኛለን። ከዚህች ከተማ ዳግም የተወለዱት ዜጎች ናቸው ፣ ለእርሷም ሁሉም የእምነት ተጓዦች ዝንባሌ አላቸው ፡፡ ከተማዋ ደግሞ የበጉ ሙሽራ ተብላ ተገልፃለች፤ እርሱ የሞተላት የርሱ ቤተክርስቲያን በሌላ ሁኔታ ውስጥ ናት ፣ የሁሉም የሰው ህብረተሰብ ንድፍ እና ግብ ፡፡ በመጨረሻው የቅዱሳት መጻሕፍት ትንታኔ ውስጥ ከተማ ማለት ቅጥር ሳይሆን ሰዎች ናቸው - የሕያው እግዚአብሔር ከተማ የሆኑ ፍጹማን ሰዎች ናቸው፡፡ ~ J. N. Birdsall. “City.” The New Bible Dictionary. 3rd ed. (electronic ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1996. p. 209.
1. እግዚአብሔር በከተሞቻቸው ስለ ነውራቸው እና ድሆችን በመጨቆናቸው ምክንያት በሕዝቡ ላይ ፈረደ ፣ አሞጽ 2.6-8.
2. በውጭ የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ቁጥር እና በሀገር ውስጥ ያሉትም ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱ የሚያሳዩት በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ከተሞቻችን ለድሆች መጠጊያ መሆናቸውን ነው ፡፡
3. ሚሽን ለከተሞች መሆን አለበት ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚወዳቸው ሰዎች በዚያ ይኖራሉ ፡፡
III. ከተማ የመንፈሳዊ መዳረሻችንና ውርሳችን ምስል እና ምልክት ነው
3
ሀ / የቅዱሳን እና የጥበበኞች ተስፋ - ፈጣሪዋ እና ገንቢዋ እግዚአብሔር የሆነች ከተማ
1. የድሮው የኔግሮ የተስፋ መዝሙር ፣ “There’s plenty good room, plenty good room, plenty good room in my Father’s Kingdom ... choose your seat, and sit down!”
2. እኛ መጻተኞች ፣ ተጓዦች ፣ መጻተኞች ፣ እዚህ ምንም ዘላቂ ዜግነት ፣ ቤት ወይም ማንነት የሌለን፤ እኛ በመጪው ዘመን ፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ በአዲስ ስርዓት ፣ ለእኛ በተዘጋጀች ከተማ ውስጥ የምንኖር ነን ፣ 1 ጴጥ. 2.11-12 ፡፡
3. የእምነት ባህርይ በዚህ ዓለም ውስጥ ቋሚ ቦታ ሳይሆን በእግዚአብሔር የተገነባችውን ከተማ መፈለግ ነው ፣ ዕብ. 11.10.
4. እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ ከተማን አዘጋጅቷል ፡፡
Made with FlippingBook - Online catalogs