Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 6 1
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
• መጽሐፍ ቅዱሳዊው የሻሎም አካላት የጤናና ደህንነት እና ጥበቃን፤ በጎረቤት መካከል ያለን መልካም ግንኙነት፤ ብቃትን፤ ብልጽግና እና የቁሳዊ ፍላጎት መሟላትን እና የክፋትና የግጭትን አለመኖር፤ እውነተኛ ሰላምን ጨምሮ ያሉትን ልምምዶች ያካትታሉ፡፡ ይህም ሰላምን እንደ እግዚአብሔር ቸርነት የተደረገ ስጦታን ይመለከታል፤ የሰላም ንጉስ ከሆነው ከመሲሁ መምጣት ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ • ድህነት የእግዚአብሔርን ሻሎም መካድ ሲሆን የእርሱ በረከት ድህነትን ለመከላከል እንደሆነ፤ ለኪዳኑ ህዝብ የተሰጡት ትዕዛዝ በያህዌ ህዝብ ዘንድ ፍትህንና ጽድቅን ለማረጋገጥ የተቀየሱ መሆናቸውን እና ለትእዛዛቱ የሚያሳዩት ታማኝነት እንዴት እስራኤላውያን ቃሉን እሰከታዘዙትና ፍቃዱን እስከተከተሉ ድረስ መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ • እግዚአብሔር ከድሃ አደጎች ጋር ይቆማል ማለትም የሚጨቁናቸው ይቀጣ ዘንድ ድሆችን ከመሬት አንስቶ መባረኩን እና ለእርሱ የተጨቆኑት፣ የተጠቁትና ለድሆች ግድ እንደሚለው እንዲሁ እነርሱ ደግሞ ግድ ይላቸው ዘንድ ይፈልጋል፡፡ የዘጸዓቱ ክስተት እንዴት እግዚአብሔር ከድሆችና ከተጨቆኑት ጋር እንደሚቆም ያሳያል፣ የቅድስና ነጸብራቅ፣ የፍትና የምህረት ምሳሌ እና ለአህዛብ መልክት እንዲሆን ለጠራው የኪዳን ህዝብ የፍትህ ልቡን በማሳየት ተገልጧል፡፡ • የተፈጥሮ አደጋና ጥፋት (ለምሳሌ ረሀብ፣ ድርቅ፣ አውሎነፋስ ወ.ዘ.ተ)፣ የግል ስንፍናና ስልቹነት (ለምሳሌ መጥፎ ውሳኔዎች፣ ስለ-ምግባር የጎደለው ባህርይ፣ ስራ ፈትነት፣ ልበ ደንዳናነት፣ ወ.ዘ.ተ) እና ጭቆናና ግፍ (ለምሳሌ በደል፣ ብዝበዛ፣ የደሞዝ ማጭበርበር ወዘተ) ጨምሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የድህነት መንስኤዎች መሆናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። • ደሃ አደግ የሚለው ቃል በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ የተለያየ ትርጓሜ ከሚሰጣቸው ጽንሰ ሀሳቦች ጋር ተያይዞ ይገኛል፡፡ ከነዚህም ውስጥ “መበለት”፣ “ወላጅ አልባ” እና “እንግዳ” የሚሉት ይገኙበታል፡፡ • ድሆችን እንደ ምስክሮች በቸርነትና በፍትህ ከመያዝ አንጻር እግዚአብሔር ለኪዳን ህዝቡ የሰጠው መስፈርት አለ፡፡ ይህም በህግ የተካተተ የፍትህ ጉዳዮችን፣ ለድሆች የሚደረግ ልዩ አቅርቦት፣ ያለ እድሎ የሚደረግ በሃቅና በትክክለኝነት ላይ የተመሰረተ፣ ሁሉም ጉዳዮች መመዘኛዎችና ሽግግሮች በፍትሀዊ መንገድ የሚካሄድበት እንዲሁም ድሆች ከእርሻችና ከወይን ምርቶች በየሰባት አመቱ ድርሻ የሚያገኙበት ነው፡፡ • ለእግዚአብሔር የኪዳን ማህብረሰብ የተቀመጡት መመዘኛዎች አንድምታ ግልፅ ነው፤ የእግዚአብሔር ህዝብ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ከድሃ አደጎች ጎን መቆሙን ማንጸባረቅ ይኖርባቸዋል፤ እግዚአብሔር በዘጸአት ካደረገላቸው ነጻ መውጣት በመነሳት ከሰዎች ሁሉ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ሁሉ የጌታን ሰላም ያሳዩ ዘንድ ነው፡፡
4
Made with FlippingBook - Online catalogs