Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

1 9 4 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

የተፈጥሮ አደጋና ጥፋት (ለምሳሌ ረሀብ፣ድርቅ፣አውሎነፋስ ወ.ዘ.ተ)፣ የግል ስንፍናና ስልቹነት (ለምሳሌ መጥፎ ውሳኔዎች፣ ስለ-ምግባር የጎደለው ባህርይ፣ ስራ ፈትነት፣ ልበ ደንዳናነት፣ ወ.ዘ.ተ) እና ጭቆናና ግፍ (ለምሳሌ በደል፣ ብዝበዛ፣ የደሞዝ ማጭበርበር ወዘተ) እነዚህን ጨምሮ የድህነት መንስኤዎች መሆናቸውን መጽሀፍ ቅዱስ ይነግረናል። ድሀ አደግ የሚለው ቃል በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ የተለያየ ትርጓሜ ከሚሰጣቸው ጽንሰ ሀሳቦች ጋር ተያይዞ ይገኛል፡፡ ከነዚህም መበለት ወላጅ አልባ እና እንግዳ ይገኙበታል፡፡ ድሆችን እንደ ምስክሮች በቸርነትና በፍትህ ከመያዝ አንጻር እግዚአብሄር ለኪዳን ህዝቡ የሰጠውን መስፈርት አለ፤ ይህም በህግ የተካተተ የፍትህ ጉዳዮችን፣ልድሆች የሚደረግ ልዩ አቅርቦት፣ያለ እድሎ የሚደረግ በሀቅና በትክክለኝነት ላይ የተመሰረተ፣ሁሉም ጉዳዮች መመዘኛዎችና ሽግግሮች በፍትሀዊ መንገድ የሚካሄድበት እንዲሁም ድሆች ከእርሻችና ከወይን ምርቶች በየሰባት አመቱ ድርሻ የሚያገኙበት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ህዝብ በሚደርጉት ነገር ሁሉ እግዚአብሄር ከድሃ አደጎች ጎን መቆሙን ማንጸባረቅ ይኖርባቸዋል፤ እግዚአብሄር በዘጸአት ከደረገላቸው ነጻ መውጣት በመነሳት ከሰዎች ሁሉ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ሁሉ የጌታን ሻሎም ያሳዩ ዘንድ ነው፡፡ የኢየሱስ ቤተክርስትያንን ማግኘት በእግዚአብሄር ህዝቦች መካከል ይህን ሰላም ለማሳየት የተጠራው አዲሱ የእግዚአብሄር የኪዳን ማህረበሰብ ነው፡፡ የኢየሱስ መሲህነት በርሱ ትኩረት፣ጥሪ፣አገልግሎትናአላማ ውስጥ ለሚገኙና ለተጨቆኑ ፈውስን ለድሆች ወንጌልን በመስበክ ውስጥ ጀምሯል ፤ ይህም ለድሆች ወንጌልን በመስበክና ፍትህን በማድረግ በመጥምቁ ዮሀንስ በኩል መሲህነቱ ተረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም ድሆችን ከተንከባከቡበት መንገድ በመነሳት እነዴት ለሌሎች መዳን እንደሆነና ከሁሉ ከሚያንሱት(ከተራቡት፣ከተጠሙት፣ከአመጸኞች፣ከታረዙት፣ከታ መሙትና ከታሰሩት)ጋር ያለመከልከል እንዴት እንደሆነ ማየት እንችላለን፡፡ የክርስቶስ የመንግስቱ ማህበረሰብ በሆነችው በቤተክርስትያንና በዚህ የመንግስቲ ማህበረሰብ ውስጥ ስላለች ምህረትንና ፍትህን የመግለጥ ድረሻ ያላቸውን ግንኙነት ማየት ይቻላል፡፡ ይህም ማለት የተጠራቸው በአለም ውስጥ የክርስቶስ አካል ለድሆች ወንጌልን ለመስበክ እና ለድሆች በሚደረግ ፍትህ አማካኝነት ስለሚመጣው ዘመን አዲስ ህይወት ማሰያ ለመሆን ነው፡፡ በተጨማሪም በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በታጠቀ ችወ የቤተክርስትያን ህይወት እና ተልዕኮ አማካኝነት የእግዚአብሄር ብሉይ ኪዳናዊው የኪዳን ማህበረሰብ ዘንድ ይህ ሰላም(ሻሎም) ታይቷል እንዲሁም ተተግብሯል፡፡ አዲሱ ማህበረሰብ ውስጥ ላሉት ችግሮች በተለይ ለመበለቶች፣ላጅ አልባዎችና ድሆች እንዲሁም በመከራ እና በችግር ጊዜያት ለሌሎች አብያተ ክርስትያናት ስለሚያደርገው ስር ነቀል የሆነ ልግስናና እንከብካቤ ማሳየት አለበት፡፡ ቤተክርስትን እግዚአብሔር ድሆችን በመረጣቸው መሰረት ተቀብላ መንከባከብ አለባት የሚለውን ጨምሪ ሌሎችንም የኢህ ምልከታ አንድታዎች ጠቅለል እድርገህ ማቅረብ እንችላለን፡፡ (ማለትም ጉዳያቸውን መከላከል፣ መብታቸውን ማስጠበቅ፣ ለእነርሱ ጥብቅና መቆምና በቤተክርስጥያን ውስጥ አድሎ አለማሳየት)፤ የድሆችን ፍላጎት ለማሟላት ያለንን በማካፈል፣ መጻተኞችን እስረኞችን በመቀበል እና እኛም የተካፈልነውን ፍቅር ለሌሎች በማካፈል ለጋስና እንግዳ ተቀባይ ልንሆን ያስፈልገናል፡፡) ቤተክርስትያን በእኛና በአለም ውስጥ ፍትህና እኩልነትን መሻት ይኖርባታል፡፡ መሰረታዊ ፍላጎታችን ለመማሟላት ብቻ ሳይሆን ወደ ፍትሀዊነት የሚወስዱን መዋቅሮችና ግንኙነቶች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እንተጋለን፡፡ በብሉይ ኪዳን ጌታ የኪዳኑን ማህበረሰብ ለድሆች ሀብት እንዲሰጥ እንደተጠበቀበት እንዲሁ ደግሞ ቤተክርስትያን በሁሉም ግንኙነቶች እና ጉዳዮች ውስጥ በድሆች ስም ፍትህና እኩልነት በመፈለግ እውነተኛውን የብልጽግና ወንጌል መኖር አለበት፡፡

4

Made with FlippingBook - Online catalogs