Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 3

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ስለ ጸሐፊው

ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ የዘ አርባን ሚኒስትሪ ኢንስቲትዩት ሥራ አስፈፃሚ እና የዎርልድ ኢምፓክት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው ፡፡ ትምህርታቸውን በዊተን ኮሌጅ እና በዊተን ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን በቢብሊካል ስተዲስ የቢ.ኤ. (1988) እና በሲስተማቲክ ቲዎሎጂ የኤም.ኤ (1989) ዲግሪዎችን በቅደም ተከተል ማግኘት ችለዋል ፡፡ በተጨማሪም ከአዮዋ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን በሃይማኖት ጥናት (ሥነ-መለኮት እና ሥነ-ምግባር) ፒኤችዲ አግኝተዋል ፡፡ የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር እና የዎርልድ ኢምፓክት ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንደመሆናቸው መጠን የከተማ ሚስዮናውያንን ፣ የቤተ ክርስቲያን ተካዮችን እና የከተማ መጋቢያን ሥልጠናን በበላይነት የሚቆጣጠሩና የሚመሩ ሲሆን ለከተሞች ክርስቲያን ሠራተኞች በስብከተ ወንጌል ፣ በቤተ ክርስቲያን እድገት እና በተቀዳሚ ተልእኮዎች የሥልጠና ዕድሎችን ያስተባብራሉ ፡፡ በተጨማሪም የተቋሙን ሰፊ የርቀት ትምህርት መርሃግብሮች ይመራሉ እንዲሁም እንደ ፕሪዝን ፌሎውሺፕ ፣ ኢቫንጀሊካል ፍሪ ቸርች ኦፍ አሜሪካ ላሉት ድርጅቶች እና ቤተ እምነቶች የአመራር ልማት እድሎችን ያመቻቻሉ ፡፡ የበርካታ የማስተማር እና የአካዳሚክ ሽልማቶች ባለቤቱ ዶ/ር ዴቪስ በበርካታ ዕውቅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሮፌሰር እና የፋኩልቲ አባል ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በሃይማኖት ትምህርቶች፣ ሥነ መለኮት ፣ ፍልስፍና እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች (ቢብሊካል ስተዲስ ) እንደ ዊተን ኮሌጅ ፣ ሴንት አምብሮስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሂዩስተን ድህረ ምረቃ የሥነ-መለኮት ትምህርት ቤት ፣ በአዮዋ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን ፣ በሮበርት ኢ ዌበር ኢንስቲትዩት ኦፍ ዎርሺፕ ስተዲስ ባሉ የትምህርት ተቋማት ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡ የከተማ መሪዎችን ለማስታጠቅ በርካታ መጻሕፍትን ፣ ሥርዓተ-ትምህርቶችን እና የጥናት ጽሑፎችን አዘጋጅተዋል ፣ ከነዚህም ውስጥ የ ‹ካፕስቶን› ሥርዓተ ትምህርት ፣ የ TUMI ፕሪሚየር ሲክስቲን ሞጁል ዲስታንስ ኤጁኬሽን ሴሚናሪ ኢንስትራክሽን፥ የከተሞች አብያተ ክርስቲያናት ታሪካዊቷን የኦርቶዶክስ እምነት እንደገና በማደስ ራሳቸው እንዴት ሊታደሱ እንደሚችሉ የሚያትተው ሴክርድ ሩትስ፡ ኤ ፕሪሚየር ኦን ሪትራይቪንግ ዘ ግሬት ትራዲሽን እና ብላክ ኤንድ ሂዩማን፡ ሪዲስከቨሪንግ ኪንግ አስ ኤ ሪሶርስ ፎር ብላክ ትዎሎጂ ኤንድ ኤቲክስ ተጠቃሾች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ዴቪስ እንደ ስታሊ ሌክቸር ሲሪስ ባሉ ትምህርታዊ ጉባኤዎች፣ እንደ ፕሮሚስ ኪፐርስ ራሊስ ባሉ የተሃድሶ ኮንፈረንሶች እና እንደ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኒያ ሊቭድ ቲዎሎጂ ፕሮጄክት ሲሪስ ባሉ ሥነ-መለኮታዊ ጥምረቶች ተሳትፈዋል ፡፡ ዶ/ር ዴቪስ በ 2009 ከአዮዋ ዩኒቨርስቲ የሊበራል አርትስ እና ሳይንስ ኮሌጅ የአልሙናይ የክብር ሽልማት ያገኙ ሲሆን በተጨማሪም የዘ ሶሳይቲ ኦፍ ቢብሊካል ሊትሬቸር እና ዘ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ ሪሊጅን አባል ናቸው ፡፡

Made with FlippingBook - Online catalogs